👉 ((ወንድምን አስቦ እርሱ በሌለበት ዱዓ ማድረግ ያለው ትሩፋት))
▪️ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
“አንድ ሙስሊም የአላህ ባሪያ ወንድሙ በሌለበት(አስታውሶ) በሩቅ ዱዓእ ያደረገለት እንደሆነ መላኢካው “ላንተም ተመሣሣዩን።”ይለዋል።"
📚ሙስሊም (በሐዲስ ቁጥር 2732) ዘግበውታል።
ሸይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
🔘"ወንድምህ አደራ ሳይልህ አስታውሰህ በሌለበት ዱዓ ማድረግህ ልቦናህ ውስጥ እውነተኛ እምነት እንዳለ አመላካች ነው።
ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ፦"ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ የማናችሁም እምነት(ኢማን) የተሟላ አይደለም።" ብለዋልና።
ስለዚህም እሱን አስበህ ዱኣ አድርግልኝ ብሎ ሳያዝህ ለርሱ ዱዓ ማድረግህ እሱን መውደድህና ብሎም ለራስህ የምትወደውን ለወንድምህ መውደድህ ጠቋሚ ነው።"
📗📙( ሸርሑ ሪያዱ ሷሊሒን 4/20―21)
0 Comments