ddis Ababa, Ethiopia tewhidfirst@gmail.com 0+25191......... seidm1434

ሽብር:

ሽብር:
በሙስሊም ተፈፀመ በክርስቲያን፣ 
ሳውዲ ውስጥ ተፈፀመ ስዊድን፣ 
መስጂድ ውስጥ ሆነ ቤተ ክርስቲያን፣ 
በፈረንጅ ሆነ በዐረብ፣ 
በፂማም ወይም በኒቃብ ለባሽ ሆነ፣ በሌላ፣
በአይሲስ ተፈፀመ፣ በኩኩ ክላስ ክላን፣
በመንግስት ተፈፀመ በግለሰብ፣
በኦባማ ተፈፀመ በኡሳማ፣
.
.
.
ሁሉም ሽብር ነው። እየመረጡ ማውገዝ፣ እየመረጡ ማራገብ፣ እየመረጡ ማለፍ፣ እየመረጡ ስሙን መቀየር፣ ወንጀሉን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ፍሬው እንዲቀል ያደርገዋል።
በአሁኑ ሰዓት የምዕራብ ሃገራት ውስጥ በሙስሊም አሸባሪዎች ከሚደርሰው በላይ በሌሎች የሚደርሰው በብዙ እጥፍ የባሰ ቢሆንም የሚዲያዎች ትኩረት ግን የተገለበጠ ነው። በአሁኑ ሰዓት በምዕራብ ሃገራት ውስጥ ከሚደርሰው ሽብር በላይ በሙስሊም ሃገራት ህዝብ ላይ የሚደርሰው በብዙ እጥፍ የከፋ ቢሆንም የሚዲያዎች ትኩረት ግን የተገለበጠ ነው። በክርስቲያን ምዕራባውያን ወረራ ያለቀው ሙስሊም በሙስሊም አሸባሪዎች ከተገደለው ክርስቲያን በብዙ እጥፍ የላቀ ነው። አላማየ "የዚያ ይበልጣል የዚያ ያንሳል" አይነት ወዝ የሌለው ሙግት መቀስቀስ አይደለም። ይልቁንም የአሸባሪዎችንም ሆነ የሰለባዎችን እምነት፣ ዜግነት፣ የቆዳ ቀለም፣ ውጫዊ ነፀብራቅ መለኪያ እያደረግን ለተመሳሳይ ጥፋት የተለያየ አቋም አናንፀባርቅ ነው። ያለበለዚያ ፍትህ ይዛነፋል። ፍትህ ሲዛነፍ ወንጀለኞች አባል ለመመልመል ይጠቅማቸዋል። ሽብርን በመዋጋት ስም እምነት ማንነቱ አብሮ የሚጠለሽበት ህዝብም ወንጀሉን ከምንጩ ለማድረቅ በሚደረገው ትግል ላይ የሚኖረው ተሳትፎ ይመነምናል።
ባጭሩ እራሳችንም ሚዲያዎቻችንም ሽብርን በመዋጋትም ይሁን በመዘገብ ላይ ከተዘንባይነት የፀዳ ወጥ አቋም ሊኖረን ይገባል። አሁን ላይ በሃገራችን እንኳ ብዙሃኑ ሕዝባችን ብቻ ሳይሆን የተማረውም ክፍል ከተዘንባይነት የፀዳ አይደለም። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን በሌሎች ሃገራት እንደሚደርሰው ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ቢደርስብን ችግሩን ለመጋፈጥ በቂ የሚዛናዊነት ዝግጅት ያለን አይመስልም። አይሲስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያንን ባረደበት ወቅት በከፊልም ቢሆን ሲንፀባረቁ የነበሩ አዝማሚያዎች ጥሩ ማሳያ መሆን ይችላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይሆን ሊቢያ በተፈፀመ ጥቃት ምንም ንክኪ የሌለውን አካል እስከ መነካካት ተደርሷል። ከሰልፎች ፈር የለቀቀ ጩኸት እስከ መንገድ ላይ ትንኮሳ ያለፉት ነገሮች ይህን የሚያሳዩ ናቸው።

ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሄዋን የሚደረሰው መቼ ነው?!


ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሄዋን የሚደረሰው መቼ ነው?!

ብዙ ሰዎች ሸሪዐዊ ሃላፊነት ለመሸከም የሚደረስበትን እድሜ ሲያስቡ 15 አመት መድረስን ብቻ ነው ከግንዛቤ የሚያስገቡት፡፡ እውነታው ግን ሌሎች ተጨማሪ መለኪያዎች መኖራቸው ነው፡፡ በጥቅሉ አንድ ሰው እንደማንኛውም "አዋቂ" ሙስሊም ተቆጥሮ በሚሰራው መልካም ስራ የሚመነዳበት እና በሚሰራው ጥፋት የሚቀጣበት (ባጭሩ ስራዎቹ የሚመዘገቡበት) የእድሜ ክልል የሚደርሰው ከሚከተሉት አራት ምልክቶች ውስጥ ቀድሞ በተከሰተው ነው፡-
1. በህልምም ይሁን በውን የዘር ፈሳሽ መርጨት መጀመር
2. በብልት ዙሪያ ፀጉር መብቀል (መባለቅ)፡-
መጠኑም ፀጉሩ ለመላጨት የደረሰ ብዛት ሲኖረው ነው፡፡ እዚህ ላይ የፂም ወይም የብብት ፀጉር መለኪያ አይሆንም፡፡ የጡት መውጣት፣ የድምፅ መጎርነንና መቅጠን መለኪያ አይደሉም።
3. ለሴት የወር አበባ ማየት፡-
እነዚህ ሶስት ምልክቶች ከታዩ ልጅዎት ለሸሪዐዊ ሃላፊነት ደርሷል ወይም ደርሳለችና ያስገንዝቡ ይከታተሉ፡፡ 15 አመት መድረስን እየጠበቁ ተዘናግተው እንዳያዘናጉ፡፡ ደግሞም ከልጆችዎት ጋር ለጉዳዩ የሚያስፈልገውን ያክል ግልፅ ውይይትና መነጋገር ይኑር፡፡ ጉዳዩን ቀድሞው ካወቁ እራሳቸውን ለሃላፊነት ያዘጋጃሉና፡፡ ካላወቁ ግን እድሜያቸው ደርሶ ላይሰግዱ ላይፆሙ ይችላሉ፡፡ ልክ እንዲሁ ካላወቁ ወይም ደግሞ አጉል መተፋፈር የሚኖር ከሆነ ከነ ጀናባቸው ሊሰግዱ፣ የወር አበባ ላይ ሆነው ሊፆሙና ሊሰግዱ ይችላሉ፡፡ ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። ስለዚህ ለልጆችዎት ወይም ደግሞ ለእህት ወንድሞችዎት በቂ ግንዛቤ ያድርሱ፡፡ መተፋፈሩ ሐቅ እንዳይሸፍንም ይጠንቀቁ፡፡
4. የመጨረሻው ምልክት 15 አመት መድረስ ነው።
ከላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ሶስት የተጠቀሱት ምልክቶች ባይታዩም 15 ከተደረሰ ቀጥታ የልጅነት የእድሜ ክልል ታልፏል ማለት ነው፡፡
ምልክቶቹ ከ 15 አመት ቀድሞ መታየት የጀመሩ ከሆነ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ሸሪዐዊ ህግጋትን በጥብቅ መከታተል ይገባል፡፡ ምልክቶቹ ቀድመው ታይተው ሳለ ሳይፆም የታለፈ የረመዳን ፆም ካለ ቀዷ ማውጣት ግድ ይላል ይላሉ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ ስለጉዳዩ ጭራሽ ግንዛቤ ከሌለ ግን ቀዷ ማውጣቱ ግዴታ እንዳልሆነ ፍንጭ የሰጡበት ፈትዋ አለ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ ዝርዝር መረጃ ወይም ግልፅ እና ቀጥተኛ ፈትዋ ያገኘ ሰው ከስር ቢያሰፍረው ሁላችንንም ይጠቅማል፡፡
በነገራችን ላይ 15 አመት መድረስ ሲባል የሚፈለገው በኢስላማዊው የሂጅራ አቆጣጠር እንጂ በፀሐይ አቆጣጠር አይደለም፡፡ (የሂጅራው አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ሲሆን የኢትዮጵያውና የፈረንጆቹ ግን የፀሐይ አቆጣጠር እንደሚባል ያስተውሉ፡፡) በጨረቃ አቆጣጠር አንድ አመት 354 ቀን ከ 9 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በፀሐይ አቆጣጠር ግን 365 ቀን ከ 6 አካባቢ ነው፡፡ እናም አንድ ልጅ በሂጅራው አቆጣጠር 15 አመት የሚደርሰው ከፀሐዩ አቆጣጠር ቢያንስ ከ 5 ወራት በፊት ቀድሞ ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ልጅ ከ 15 ዓመት በፊት ከላይ ከአንድ እስከ ሶስት ካሉት ምልክቶች አንዱ ከታየበት ወይም ደግሞ እነዚህ ሳይታዩ ቀርተው 15 አመት ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ለሸሪዐዊ ህግጋት ተገዥ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ሴቶችን መጨበጥ፣ መመልከት፣ ከአንዲት ሴት ጋር ለብቻ ተገልሎ መቀመጥ የለበትም፡፡ በቃ ከዚህ በኋላ በደረሱ ወንዶች ላይ የሚከለከሉ ነገሮች ሁሉ ለሱም ክልክል ናቸው፡፡ የደረሱ ወንዶችን የሚመለከቱ ግዴታዎች ሁሉ ይመለከቱታል፡፡ ሴቷንም እንዲሁ፡፡ አለባበስን ጨምሮ ነገሮችን በጥንቃቄ ልትከታተል ይገባታል፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 2/2009)

ቀብር ላይ ሱረቱል ፋቲሃ እና ሌላን ሱራ መቅራት?

ቀብር ላይ ሱረቱል ፋቲሃ እና ሌላን ሱራ መቅራት?
የቱን ይከተላሉ አላህ ያወረደውን ወይንስ “የአባቶቻችን መንገድ” ብለው የሚጠሩትን?
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
መቼም እስልምናችን ውብ እና ሙሉ፣ ለየትኛውም ዘመን እና ቦታ ከበቂ በላይ የሆነ ነው፡፡ ታማኙ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአላህ የተላኩበትን ማንኛውም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ቀብር ስንዘይር ምን ማለት እንዳለብንም አስተምረዋል፡፡ የሚከተለው ሀዲስ ላይ እንደተዘገበው
وعن بريدة رضي الله عنه قال‏:‏ كان النبي صلى الله عليه وسلم يعلمهم إذا خرجوا إلى المقابر أن يقول قائلهم‏:‏ “السلام عليكم أهل الديار من المؤمنين والمسلمين وإنا إن شاء الله بكم للاحقون، أسأل الله لنا ولكم العافية” ‏(‏‏(‏رواه مسلم‏)‏‏)‏‏.‏
የአላህ ሰላም በናንተ የዚህ መኖሪያ (ቀብር) ባለቤቶች ላይ ይሁን፡፡ ከአማኞች እና ከሙስሊሞች፡፡ እኛ በአላህ ፍቃድ ወደ እናንተ የምንከተል (ሟቾች) ነን፡፡ አላህን ለእኛም ለእናንተ አፊያን እንዲያደርግ እንጠይቀዋለን፡፡
ከዚህ ሀዲስ የምንወስደው ዋና ቁምነገር
- በህይወት ያለ ሰው ነው ለሙታን ዱዓ የሚያደርገው፣
- ሙታን ዱዓ ይደረግላቸዋል እንጂ እነሱ አይለመኑም፣
- ዛሬ ሺርክ ላይ የወደቁ ሰዎች ህያው የሆነውን፣ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነውን፣ የማይሞት አላህ ትተው ስራቸው የተቋረጠባቸውን፣ ምንም ማድረግ የማይችሉ፣ ቢጠሩ የማይሰሙ፣ ቢሰሙም ኖሮ መልስ መስጠት የማይችሉ ሙታኖችን እርዳታ ይለምናሉ፣ ቀብራቸው ላይ ሄደው ያርዳሉ፣ ቀብራቸው ላይ ጠዋፍ ያደርጋሉ፡፡
በዚህ ሀዲስ መሰረት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያስተማሩን ወንድ ልጅ ቀብር ሲሄድ ይህንን ዱኣ እንዲል ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሱረቱል ፋቲሃንም ይሁን ሌሎች ሱራዎችን በተለይ አገራችን ላይ በጀመዓ ቁርኣንን እየጮሁ የሚቀሩት ቢድዓ (በዲን ላይ የተጨመረ ፈጠራ) ነው፡፡ ከአላህ ቀጥሎ ለማንም በላይ እንወዳቸዋለን እያልን የምንጠራቸው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይሉናል “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው፡፡” (ስራው ተቀባይነት የለውም)፡፡ ቀብር ላይ ሄዶ ሱረቱል ፋቲሃንም ይሁን ሌላን ሱና በጀመዓም ይሁን በነጠላ መቅራት የታለ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙበት? መልሱም አላዘዙበትም፡፡ ስለዚህ ቀብር ላይ እሳቸው ያስተማሩትን ብቻ እንበል፡፡
እኛ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዬች ነን ካልን በሁሉ ነገር ልንከተላቸው እና እሳቸው ያልሰሩትን ልንርቅ ይገባናል፡፡ ከዛ ውጭ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ ለሸሁም፣ ለኡስታዙም፣ ለአባቶቹም ሲል የተወ ሰው ከባድ አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ ምክንያቱም ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከማንም በላይ እኛ ዘንድ እስካልተወደዱ (እስካልተከተልናቸው እና በዲን ላይ ከሚደረግ ፈጠራ እስካልራቅን) ድረስ እውነተኛ አማኞች አልሆንም፡፡
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት ሱና እንዲህ ሁሉን ነገር ገላልፆ ሲያበቃ የአባቶቻችን መንገድ ብሎ ሱናን መቃረን ለከባድ አደጋ ይዳርጋል፡፡
የአባቶቻችን መንገድ የተባለው ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ከገጠመ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ከአባት ከእናታችን በላይ ውድና በላጭ የሆኑትን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ከተቃረን አሽቀንጥረን እንወረውረዋለን፡፡ ምክንያቱም የሰይጣን መንገድ ነውና፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
[2:170] وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَآ أَلْفَيْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ ۗ أَوَلَوْ كَانَ ءَابَآؤُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ شَيْـًٔا وَلَا يَهْتَدُونَ
ለእነርሱም “አላህ ያወረደውን ተከተሉ” በተባሉ ጊዜ “አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን” ይላሉ፡፡ አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?)
[31:21] وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ ۚ أَوَلَوْ كَانَ ٱلشَّيْطَٰنُ يَدْعُوهُمْ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
ለእነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን ይላሉ፡፡ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን?)
ይሀው እነዚህ ሁለት አንቀፆች በግልፅ እንዳስቀመጡት “የአባቶቻችን መንገድ” እየተባለ አገራችን ላይ የሚነሳው የጥንቶቹም የሚያነሱት ብዥታ ነበር፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና እሳቸውን በየዘመኑ የሚከተሉ ኡለማዎች እና ተጣሪዎች የሚያዙት “አላህ ያወረደውን ተከተሉ (እንከተል)” ሲሉ ነው፡፡ የነብያትን መንገድ የሚቃረኑ ሰዎች ደግሞ በየዘመኑ መልሳቸው “አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን” የሚል ነው፡፡
አላህ ግን እንዲህ ሲል ጠየቀ
- “አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?)”
- “ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን?)”
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ አንዳንዴ የአባቶቻችን መንገድ የሚሉትን ልክ አይደለም ሲባሉ እና በማስረጃ መልስ ሲሰጠው “እናንተ ከእነ ሸህ እከሌ በላይ ታውቃላችሁን?” ሲሉም ይደመጣል፡፡ ጥያቄው እነዚህ ሸህ ተብየዎች ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ከሰሃባዎቻቸው በላይ ያውቃሉን? በፍፁም፡፡ እኛ አላህ እና መልክተኛው በእውቀታቸው፣ በአማኝነታቸው፣ በእውነተኝነታቸው፣ በታጋሽነታቸው፣ በቁርጠኝነታቸው የመሰከሩላቸውን መልክተኛውን እና ሰሃባዎቻቸውን መንገድ ነው የምንከተለው፡፡
አላህ ያወረደውን የማይከተል ሰይጣን ወደ እሳት የሚጣራበትን መንገድ እየተከተለ ነው፡፡
አገራችን ላይ አብዛኛውን ጥፋት “የአባቶቻችን መንገድ” እየተባለ ይፈፀማል፡፡ አባቶቻችንን ሳይሆን አላህ ያወረደውን እንድንከተል ነው የታዘዝነው፡፡ መልካም ማለት እኛ መልካም ያለነው አይደለም፡፡ መልካም ማለት ዲን መልካም ያለው ነው፡፡
አምነው ለሞቱ አባቶቻችን በጠቅላላ አላህ ወንጀላቸውን እንዲምር ደረጃቸውን ከፍ እንዲያደርግ ቀብራቸውን እንዲያሰፋ እለምነዋለሁ፡፡ አላህ እኛንም ሙስሊም አድርጎ እንዲገድለን እለምነዋለሁ፡፡
አላህ እሱ ባወረደው፣ በነብዩ ሱና ከሚብቃቁት፣ ከሺርክና ከቢድኣ ከሚርቁት ያድርገን፡፡ በአላህ ቢሆን እንጂ ሀይልም ብልሀትም የለም፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

የአብሬት ሸህ እና ደርግየአብሬት ሸህ እና ደርግ
አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው የሁሉ ፈጣሪ፣ ህያው፣የማይሞተው፣ አሸናፊ ለሆነው አላህ ብቻ ነው፡፡ ሰሞኑን ጉዞ ወደ አብሬት ብለው ሰዎች የሚሄዱለት የአብሬት ሸይኽ በመባል ይታወቃሉ፡፡ አገራችን ላይ በጣም ድንበር ከሚታለፍባቸው ግለሰቦች ውስጥ ከቶፕ 5 ውስጥ ናቸው፡፡ 
እዚህ ትምህርት ላይ ማንሳት የፈለግኩት ምን አይነት ሰው ነበሩ? የሚለውን አይደለም፡፡ ነገር ግን መጥቀስ የምፈልገው ምን ያህል ድንበር እንደታለፈባቸው ነው፡፡
የአብሬት ሸይኽ አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ ወረድ ብሎ ያለ አካባቢጠቅላይ ቢሮየሚባል ቦታ ውስጥ እራሳቸውን አሟቸው በተኙበት ከሳቸውሙሪዶችአንዱ ቤቱን 7 ጊዜ ዞሮ ፊዳ ልሁን እኔ ብሎ እራሱን በቢላዋ አርዶ ገድሏል፡፡
ሌላው የአብሬት ሸይኽን በጣም ብዙ ሰዎች ለአላህ ብቻ የሚገባውን አምልኮ ሲፈፅሙላቸው ይታያል፡፡ አሳዛኙ ግን የአብሬት ሸይኽም ይሁን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለራሳቸውም ይሁን ለጠየቃቸው ጥቅምን ማምጣት፣ መስጠት አይችሉም፡፡ ከጉዳትም እራሳቸውንም ሆነ ጠብቀኝ ያላቸውን መከላከል አይችሉም፡፡
የአብሬት ሸይኽ ደርግ ወስዷቸው እርምጃ እንደወሰደባቸው ቤተሰቦቻቸውም የእሳቸውን ሞት ሁሉ ተቀብለው ተቀምጠው ሳለ፣ ተከታዬቻቸውአባባ ይመጣሉአባባ አልሞቱምእያሉ ብዙ ችግር ውስጥ ገብተዋል፡፡
አምልኮ ከደርግ እራሳቸውን ማስጣል ለማይችሉት ለደካማው አብሬት አይገባም፡፡ ይሄ ሺርክ ነው፡፡
አምልኮ ሃያል፣ ህያው፣ የማይሞት፣ አሸናፊ ለሆነው አላህ ብቻ እና ብቻ ነው የሚገባው፡፡

ጥያቄ፦ጂኖች አጋንንት በሰዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላሉን? ከነሱ የምንጠበቅበት መንገድስ ምንድነው?
ጥያቄ፦ጂኖች አጋንንት በሰዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላሉን? ከነሱ የምንጠበቅበት መንገድስ ምንድነው?

መልስ፦ ጂኖች እስከመግደል ድረስ በሰዎች ላይ የተለያዩ አደጋዎችን እንደሚያደርሱ ጥርጥር የለውም። ድንጋይ ሊወረውሩበት ይችላሉ። ሊያስፈራሩት ይችላሉ። ሌሎች ችግሮችንም ሊያደርሱበት እንደሚችሉ በሀዲስም በተጨባጭ ተረጋግጧል። ነቢዩ (‏ﷺ) በአንድ ዘመቻ ላይ እያሉ (በኽንደቅ ዘመቻ ይመስለኛል) ለአንድ ሰሃባቸው ወደ ሚስቱ እንዲሄድ ፈቀዱለት። ወጣትና ሙሽራ ነበርና። እቤቱ ሲደርስ ሚስቱ ደጃፍ ላይ ቆማ ነበር። ደጃፍ ላይ በመቆሟ ተቆጣት። ግባና ታያለህ አለችው። ወደ ውስጥ ሲገባ እባብ ተጠቅልሎ ፍራሹ ላይ ተቀምጧል። ጦር በእጁ ይዞ ነበርና በጦሩ ወጋው። እባቡ ሞተ። ወዲያው ሰውየውም ሞተ። ማን ቀድሞ እንደሞተ እባቡ ወይስ ሰውየው አይታወቅም። ጉዳዩ ለነቢዩ (‏ﷺ) ሲነገራቸው አብተርና ዙጡፈተይን የተባሉ እባቦች ሲቀሩ በቤት ውስጥ የሚቀመጡ ጂንናን (የጂን እባቦች) እንዳይገደሉ ከለከሉ። [ቡኻሪ]

ጂኖች በሰዎች ላይ ድንበር እንደሚያልፉና አደጋ እንደሚያደርሱባቸው ይህ ማስረጃ ይሆናል። ተጨባጩ ሁኔታም ይህንኑ ያረጋግጣል። ሰው ወና ወደ ሆነ ቦታ ሄዶ ምንም ሰው ሳይኖር ድንጋይ እንደሚወረወርበት በሰፊው ይነገራል። እሱን የሚያስፈራራ ድምፅና ኳኳታም ይሰማል። እንደዚሁም ጂን ወደ ሰው አካልም ይገባል። አንድም አፍቅሮት ወይም ደግሞ ሊያሰቃየው ወይም በሌላ ምክንያት። የሚከተለው የአላህ ቃል ይህንኑ ያመለክታል፦

الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسَِّ

“እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ነክቶት የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጅ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡”
[አል-በቀራህ - 275]

ወደ ሰው አካል የገባው ጂን ከሰውየው ውስጥ ይናገራል። ሰውየው ላይ ቁርአን የሚቀራበትን ሰው ያናግራል። ቁርአን የሚቀራው ሰው ጂኑ ወደ ሰውየው እንዳይመለስም ቃል ያስገባዋል። እነዚህ ሁኔታዎች በሰዎች ዘንድ በስፋት ታውቀዋል። ስለዚህ እንደ አየተል ኩርሲ ያሉና በሐዲስ የተዘገቡ ዚክሮችን በመቅራት ሰው ከጂን ክፋት ሊጠበቅ ይችላል። አየተልኩርሲን በማታ የቀራን ሰው አላህ ጠባቂ ያደርግለታል። እስከሚነጋ ድረስም ሸይጣን አይቀርበውም አላህ ይጠብቀን።

[ሸይኽ መሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ]
ታላቁ ነብዪ


ታላቁ ነብዪ
ጆርጅን ከፒተር ጋር ፈቅዶ ከሚያጋባ
ሴት ልጁን ለዝሙት ላገር ከሚጀባ
ከምዕራቡ መንደር ከዚያ ከገለባ
ነብዩን በመስደብ ሲደርስህ ዘገባ
ወንድሜ አይግረምህ እንድያ ነው ነገሩ
ሚስክ አይጠበቅም ከገማ መንደሩ።
አከባቢ ገምቶ ከተጨማለቀ
ክፉ ላይ ውሎ አድሮ በዛው ከዘለቀ
ያማረውን ነብዪ ልቡ እንዴት ይወዳል?!
የረከሰ አእምሮ ውብን መች ይረዳል ?!
ያንን ታላቅ ረሱል ላይ ውስጡ ያማረ 
ስስትን የማያቅ ያለውን የቸረ
ውሸት አልጎበኘው ከልጅ እስከ እውቀቱ
የሰው ሓቅ አልነካ እስከለተ ሞቱ።

በጌታው እርዳታ እየገሰገሰ
የጣኦት አምልኮን እየገነደሰ
አምልኮን ላንድ አምላክ ብቻ ያነገሰ
ያንን ታላቅ ነብዪ …
ርካሹ ቢጠላው ስሙንም ቢያጎድፈው
በለመደው ቅጥፈት ዛሬም ቢወርፈው
እህቴ አይግረምሽ እንዲህ ነው ነገሩ
ካፉ ሚስክ አይወጣም - ከገማ ምግባሩ

ግን ልንገርህ ወንድም -ልንገርሽ እህቴ …
የምዕራብ ከሃዲ ነብዩን ሲዘልፉ
በስብእናቸው ላይ ባፋቸው ሰቀጥፉ
ሰምተህ እያየኸው የነሱን ጎደና
ዞረህ እንዳትገባ ወደነሱ ሱና 
ምድራቸው አይናፍቅሽ ይቅርብሽ ልብሳቸው
ሱናቸውን ራቂ እንደጠላሻቸው።
ከ 2 (3) አመታት በፊተወ የተፃፈ


Muhammedsirage MuhammedNur Gidey


ነት" ማውራት የፈለገ ዳዒ ጉዳዩን ሳያብራራ ቢያልፈው " አጎደለ" ወይም " አላስረዳም" መባሉ ሊገርም አይገባም! ! እንደውም ተገቢ ነው!!
የዳዒ አላማም ማደናገርና ታዳሚውን ወዥንብር ውስጥ መንከር ወይም በነበረበት ውዥንብር ላይ ማቆየት ሳይሆን ማስረዳትና ጭብጥን ማስጨበጥ ነውና " አስረጂ" መሆኑ "የጥራት ደረጃውን" ከፍ ያረገዋል! !
አድማጭና አንባቢውም ማብራሪያው በጠፋ ግዜ ማብራሪያ እና ቅጥያ መፈለጉ እጅግ ጤናማ አካሄድ ነው— ሊያሰወቅስ ይቅርና! !
በርግጥ በዚህ ጉዳይ "ብቻ" ሰዎችን በኢኽዋንነት መፈረጅ ተገቢ አይደለም።
ቀደምት ኢማሞቻችን አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ሲገልፁ "በዛቱ " የሚለውን ቅጥያ ጨምረዋል—ብልሹ የሆኑ የጀህሚያ አቋሞችን ለማስወገድና ጉዳዩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ። እንጂ ቁርአንና ሓዲስ ላይ "በዛቱ" የሚል ቅጥያ አይገኝም!!
በተጨማሪም ቁርአንን غير مخلوق
(ፍጡር ( የተፈጠረ)አይደለም)
ብለው ቁርአንና ሓዲስ ላይ በማይገኝ ጭማሪና ቅጥያ ገልፀዋል — مخلوق
(ፍጡር ነው) የሚሉ ጠማሞች በወቀቱ በመገኘታቸው ......
غير مخلوق
የሚለው ንግግር ራሱ ቢድዓ መሆኑን ግልፅ ያረጉ ኢማሞች ከመኖራቸው ጋር! !
እናም ፣ ቁርአንና ሓዲስ ላይ የመጡ ነገሮችን መጀመሪያ በመጡበት መልኩ መረዳት በደበዘዘበት ወቅት ቅጥያዎችን ( ሸሪዐው በሚፈቅደው መልኩ) ጨማምሮ ማብራራቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህንን ቅጥያ መጠበቅና መጠየቅ ደግሞ ጤናማ አመለካከት ሊነፈገው የሚገባ አይደለም! !

Muhammedsirage MuhammedNur Gidey

Blog Archive

Tewhidfirst.blogspot.com. Powered by Blogger.

Followers

Total Pageviews

Follow by Email

Blogger Tips and TricksLatest Tips And TricksBlogger Tricks

Follow me In Facebook

Time