Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወረርሺኝ እንዲወገድ በማሰብ የሚደረገው ቁኑት ብይን~حكم القنوت لرفع الوباء

ወረርሺኝ እንዲወገድ በማሰብ የሚደረገው ቁኑት ብይን
~

حكم القنوت لرفع الوباء

📜 السؤال:

ماحكم القنوت في صلاة الجماعة لرفع الوباء ؟

الجواب :

الراجح من أقوال العلماء عدم القنوت لرفع الوباء؛ لأنه قد وقع طاعون عمواس زمن الصحابة ولم ينقل أنهم قنتوا لرفعه. لكن يشرع الدعاء برفعه في السجود وسائر الأوقات، كما تجب التوبة والتضرع لله والاستكانة له وكثرة الاستغفار.
وقد قال العلامة ابن مفلح في كتابه الفروع (485/1) : 
 ﻻ ﻳﻘﻨﺖ ﻟﺪﻓﻊ اﻟﻮﺑﺎء ﻓﻲ اﻷﻇﻬﺮ؛ ﻷﻧﻪ ﻟﻢ ﻳﺜﺒﺖ اﻟﻘﻨﻮﺕ ﻓﻲ ﻃﺎﻋﻮﻥ ﻋﻤﻮاﺱ ﻭﻻ ﻓﻲ ﻏﻴﺮه، ﻭﻷﻧﻪ ﺷﻬﺎﺩﺓ للأخيار؛ ﻓﻼ ﻳﺴﺄﻝ ﺭﻓﻌﻪ. انتهى، والله أعلم.

✍🏻 نعمان بن عبدالكريم الوتر
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ

ወረርሺኝ እንዲወገድ በማሰብ የሚደረገው ቁኑት ብይን
~

ጥያቄ:– ወረርሺ እንዲወገድ ታስቦ በጀማዐ ሶላት ውስጥ የሚደረገው ቁኑት ብይኑ ምንድነው?

መልስ:–

"ከኡለማእ ንግግሮች ውስጥ ሚዛን የሚደፋው ወረርሺ እንዲወገድ ታስቦ ቁኑት አለማድረግ ነው። ምክንያቱም በሶሐቦች ዘመን የዐመዋስ ወረርሺኝ ከመከሰቱም ጋር እንዲነሳላቸው ቁኑት ማድረጋቸው አልተላለፈም። ነገር ግን በሱጁድና ሌሎችም ወቅቶች ውስጥ እንዲወገድ ዱዓእ ማድረጉ ይፈቀዳል። 
ልክ እንዲሁ ተውበትና ወደ አላህ መተናነስና ለሱ መዋደቅ ግድ ይላል። ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ሙፍሊሕ ‘አልፉሩዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ብለዋል:–
‘ሚዛን በሚደፋው አቋም ወረርሺኝ ለመከላከል ቁኑት አይደረግም። ምክንያቱም በዐመዋስም ሆነ በሌላ ወረርሺኝ ጊዜ ቁኑት እንደተደረገ ተጨባጭ መረጃ የለምና። በተጨማሪም ለምርጦች መስዋእትነት ነውና። ስለሆነም እንዲነሳ (በቁኑት) አይጠየቅም።’
ይበልጥ የሚያውቀው አላህ ነው።"

ኑዕማን ኢብኑ ዐብዲልከሪም አልወተር
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
📲 ‏https://t.me/alwatarftawa
📌 اضغط على الرابط ثم انضم

Post a Comment

0 Comments