የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች “ሸርጦች”
1. ዕውቀት ‘ዒልም’ ፡- ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት ዉድቅ የሚያደርጋቸዉንና እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ማወቅ ማለት ነው፡፡ ምስክርነት እውቀትን መሰረት ካላደረገ ተቀባይነት አይኖረዉም። ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡
وَلَا يَمْلِكُ الَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنْ شَهِدَ بِالْحَقِّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ - الزخرف 86
“እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም” አል-ዙኸሩፍ 86
2. እርግጠኛነት ‘የቂን’ ፡- በአላህ ብቸኛ አምላክነት ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን ነው፡፡ ጥርጣሬ ላይ ያለ ሰው ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረዉም። አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آَمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنْفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ﴾ الحجرات 15
({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም ያልተጠረጠሩት ናቸው) አል-ሑጁራት 15
فمن لقيت من وراء هذا الحائط يشهد أن لا إله إلا الله مستيقنا بها قلبه فبشره بالجنة
رواه مسلم
የአላህ መልእክተኛም ለአቡ ሑረይራ እንዲህ ብለውታል፡-
‹‹ከዚህ አጥር በስተጀርባ የአላህን ብቸኛ አምላክነት ከልቡ በእርግጠኝነት የሚመሰክር ሰው ብታገኝ በጀነት አበስረው፡፡››
3. መቀበል ‘ቀቡል’ ፡- የላኢላሀ ኢለላህን መልእክት ማለትም «አላህን በብቸኝነት ማምለክን» ከልብ መቀበልና ለሌላ አካል የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው ነው፡፡ ይህንን ያልተቀበለ እና አምልኮዉን ለፍጡራን ያዋለ ሰው አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸው እንዲህ በማለት ከገለፃቸው ሙሽሪኮች ይመደባል።
إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ (35) وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوا آَلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَجْنُونٍ الصافات 35-36
“እነርሱ፤ ‹ከአላህ በቀር አምልኮ የሚገባው ሆኖ የሚመለክ የለም› በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፤ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን ይሉም ነበር” አልሷፋት 35-36
4. መታዘዝ ‘ኢንቂያድ’ ፡- ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል ለሚያመላክታቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሁሉ ታዛዥ፣ ተከታይና ተናናሽ መሆን፤ ከቸልተኝነት እና ካለመተግበር መራቅ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَمَنْ يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَ - لقمان 22
“እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ) ወደ አላህ የሚሰጥ ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ...” ሉቅማን 22
5. እውነተኝነት ‘ሲድቅ’ ፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ እውነተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ع እንዲህ ብለዋል፤
مَا مِنْ أَحَدٍ يَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ صِدْقًا مِنْ قَلْبِهِ إِلَّا حَرَّمَهُ اللَّهُ عَلَى النَّارِ رواه البخاري
‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድ ع መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርም ይለዋል››
6. መውደድ ‘ሙሀባህ’ ፡- ይህ ማለት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል ፡-
وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَتَّخِذُ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَنْدَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ وَالَّذِينَ آَمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِلَّهِ
البقرة 165
“ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡” አል በቀራህ 165
7. ማጥራት ‘ኢክላስ’ ፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፡፡ ይህ የምስክርነት ቃል ትክክል እንዲሆን በስራዉ የዱንያ ጥቅማጥቅሞችን ከመከጀል፣ ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ ማጥራት አለበት፡፡ የአምልኮ ዘርፎችን በሙሉ ለአላህ ብቻ ሊያዉል ይገባል። የአላህ መልዕክተኛ ع እንዲህ ብለዋል፤
روى البخاري عن أبي هريرة أن النبي ع قال له »أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ« .
‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ በማግኘት ዕድለኛ የሚሆነው ‘ላ ኢላሀ ኢለላህ’ን ከልቡ ያለ ሰው ነው፡፡›› ቡኻሪ ዘግበዉታል

0 Comments