ሽርክ በሶስት ይከፈላል፦
እነሱም፡- ትልቁ ሽርክ፣ ትንሹ ሽርክ ፣ ድብቁ ሽርክ ናቸው።
ትልቁ ሽርክ (ሺርክ አል-አክበር)፡- የሰራውን መልካም ስራ ሁሉ ውድቅ ያደርጋል፣ በዚህ ሽርክ ላይ ሆኖ የሞተ ሰው እሳት ውስጥ ለዘላለም መኖር ምንዳው ይሆናል፤ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር።›› (አል አንዓም 88)
በሌላ አንቀጽም
‹‹ለከሓዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲኾኑ የአላህን መስጊዶች ሊሠሩ አይገባቸውም። እነዚያ ሥራዎቻቸው ተበላሹ። እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።›› (ተውባህ 17)
ሸርክን እየፈፀመ የሞተ ምህረትን አያገኝም ጀነትም በእሱ ላይ እርም ናት።
‹‹አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል።›› (አል ኒሳእ 48)
በሌላ አንቀጽም
‹‹እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ። መኖሪያውም እሳት ናት። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም።›› (አል ማኢዳህ 72)
ከሽርክ አይነቶች ሙታንንና ጣኦታትን መጥራት፣ ድረሱልኝም ማለት፣ ለእነሱ ስለት መግባት ፣ ማረድና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ትንሹ ሽርክ (ሽርክ አል-አስገር)፡- ይህ ደግሞ በቁርአንና በሀዲስ መረጃዎች ሽርክ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሆኖ ግን ከትልቁ ሽርክ የማይመደብ ነው። ለምሳሌ፤ አንዳንድ ስራዎች ላይ ይዩልኝ የሚል ስሜት ማስገባት፣ ከአላህ ውጪ ባለ አካል መማል፣ አላህ እና እገሌ የፈለጉት ተከሰተ ማለትና የመሳሰሉት ናቸው። ይህን ያልንበት ምክንያት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ስለሚሉ ነው።
{أخوف ما أخاف عليكم الشرك الأصغر} فسئل عنه، فقال: {الرياء}
“በእናንተ ላይ ከምፈራው ሁሉ በጣም አስፈሪው ነገር ትንሹ ሽርክ ነው።” ስለሱም ተጠይቁ፤ ነብዩም እንደሚከተለው መለሱ “ይዩልኝ ነው”። ይህንንም ሀዲስ ኢማሙ አህመድ እና በይሀቂይ ከመህሙድ ቢን ለቢድ አልአንሳሪ መልካም በሆኑ ሰነዶች ዘግበውታል። ጠበራኒይም እንዲሁ ከመህሙድ ቢን ለቢድ፣ መህሙድ ደግሞ ከራፊእ ኢብን ኸዲጅ፣ ራፌዕ ከነብዩ መልካም በሆኑ ሰነዶች ዘግበውታል።
{من حلف بشيء دون الله فقد أشرك}
“ከአላህውጭ ባለ አንዳች ነገር የማለ በእርግጥም አጋርቷል።” የሚለውን የአላህ መልዕክተኛ ንግግር ኢማሙ አህመድ በትክክለኛ ሰነድ ከኡመር ኢብኑል ኸጣብط አስተላልፈውታል።
እንዲሁም አቡ ዳውድ እና ቲሚዚይ በትክክለኛ ሰነድ ከአብድላህ ኢብኑ ኡመር ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ፤
{من حلف بغير الله فقد كفر أو أشرك}
“ከአላህ ውጭ ባለ ነገር የማለ በእርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል።”
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
{لا تقولوا: ما شاء الله وشاء فلان، ولكن قولوا: ما شاء الله ثم شاء فلان}
“አላህና እገሌ ከፈለጉ (ይከሰታል) አትበሉ። ነገር ግን አላህ ከሻው ከዚያም በኃላ እገሌ ከሻው በሉ” አቡዳውድ ሁዘይፋ ኢብኑልየማንን ጠቅሰው በትክክለኛ ሰነድ ዘግበውታል። ይህ የሽርክ አይነት (ትንሹ ሽርክ) ከዲን ለመውጣት አይዳርግም፣ በእሳት ዘላለም ለመዘውተር አይዳርግም። ነገር ግን ማመን ግዴታ የሆነውን የተውሂድ ምሉዕነት (ከማል) ልክ ያጓድላል።
ድብቁ ሽርክ ማለት(ሽርክ አልኸፍይ)፡- ሶስተኛው የሽርክ አይነት ሲሆን ማሰረጃውም የሚከተለው የአላህ መልዕክተኛ ንግግር ነው፡-
{ألا أخبركم بما هو أخوف عليكم عندي من المسيح الدجال ؟ قالوا: بلى يا رسول الله، قال: الشرك الخفي، يقوم الرجل فيصلي فيزين صلاته لما يرى من نظر الرجل إليه}
“እኔ ዘንድ ከመሲሀደጃል ይበልጥ የምፈራላችሁን አልነግችሁምን?” “አዎን ይንገሩን የአላህ መልዕክተኛ” አሉ እሳቸውም “ድብቁ ሽርክ ነው (የዚህም ምሳሌው) አንድ ሰው ለሰላት ይቆምና ሰዎች እርሱን የሚመለከቱት መሆኑን ሲያውቅ ሰላቱን ይበልጥ ያሳምራል።” ኢማሙ አህመድ በሙስነዳቸው አቡሰኢድ አልኹድሪይን ጠቅሰው ዘግበውታል።
ሽርክን ትልቁና ትንሹ ብሎ በሁለት መክፈልም ይቻላል፡ ድብቅ ሽርክ የተባለው ሁለቱም የሽርክ አይነቶች ውስጥ ሊካተት ይችላል። ትልቁ ላይ ሊከሰት ይችላል የዚህም ምሳሌው የሙናፊቆች ሽርክ ነው። ምክንያቱም ለይዩልኝና ለነፍሳቸው ፈርተው ከላይ ብቻ ኢስላምን እያንፀባረቁ ባጢል የሆነውን እምነታቸውን ስለሚደብቁ።
ትንሹ ሽርክ ላይም ሊከሰት ይችላል የዚህም ምሳሌው ለይዩልኝ ብሎ መስራት ቀደም ብሎ በተጠቀሰው በመህሙድ ኢብኑ ለቢድ አልአንሳሪይና በአቡሰኢድ አልኹድሪይ ባስተላለፉት ሀዲስ ተገልጿል። መልካምን የሚገጥመው አላህ ብቻ ነው።
·