በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙሪያ አስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ ህጎች!
1ኛው መሰረታዊ ህግ
ስለ አላህ ባህሪዎች መናገር ስለ ተቀደሰው የአላህ “ዛት” እንደመናገር ነው።(አንድ አይነት ናቸው)
ዛት የሚለው ቃል « ጥቅል ቃላት» “አልፋዝ ሙጅመላህ” ከሚባሉት ይመደባል። ከዚህ በላይ ሀድ፣ ጂሀ፣ መካን፣ ጂስም እና መሰል ቃላትን አህሉሱና እንዴት እንደሚያስተናግዷቸው ተገልጿል። ዛት የሚለው ቃል በቁርአን እና በሱና ባይመጣም ሰዎች በማጽደቁ ላይ አይወዛገቡምና የቢድዓ ሰዎችን ለመወያየት እና ለማሳመን እንጠቀምበታለን።
ይህም ማለት፤ ሁሉም እንደሚስማማው አላህ ከማንም “ዛት” ጋር የማይመሳሰል “ዛት” አለው። ልክ እንደዚሁ በቁርአንና ሀዲስ የፀደቁ ባህሪያዎቹ የፍጡራን ባህሪዎችን አይመሳሰሉም፡፡ በመሆኑም የአላህ ዛትንና የአላህ ባህሪን ከፍጡራን ዛትና ባህሪ ጋር አለመመሳሰልን ይጋራሉ፡፡
ይህ መሠረት ዛትን እያፀደቁ ባህሪን የሚቃወሙ ሰዎችን ለማሳመን ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ዛትን ማፅደቅ ሁሉም የሚስማማበት እና ውዝግብ የሌለበት ጉዳይ ነው። ይሁንና ማንም ሰው፤ “ፍጡራን ዛት ስላላቸው ‘አላህ ዛት አለው’ ማለት ማመሳሰል ‘ተሽቢህ’ ነው” ብሎ አያውቅም፡፡ ምክኒያቱም ዛት የሚለዉን ደካማ ወደ ሆነው ሰው የተባለ ፍጡር ስናስጠጋዉና ወደ ሀያሉና የነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ወደሆነው አላህ ስናስጠጋው ፍጹም የተለየ መልዕክት እንዳለው ሁሉም ሰው ይገነዘባል።
ይህ አይነቱን ሰው በዚህ መልኩ ለማስረዳት እንዲህ ብለን እንጠይቀዋለን፤
-“አንተ አላህ ዛት እንዳለውና ፍጡራንም ዛት እንዳላቸው ታምናለህ፡፡ ይህ ታዲያ ማመሳሰል አይደልን?” በእርግጠኝነት የእርሱ ምላሽ የሚሆነው፦ -“እኔ ለአላህ የማጸድቀው ዛት ከፍጡራን ዛት ጋር የማይመሳሰል ነው” የሚለው ነው። ከዚህ ውጭም መልስ አይኖረውም።
እንዲህም እንለዋለን፦
-“ከፍጡራን ዛት ጋር የማይመሳሰል ዛት ለአላህ እንዳጸደቅከው ሁሉ፤ ከፍጡራን ባህሪዎች “ሲፋት” ጋር የማይመሳስሉ ባህሪዎችን ብታፀድቅለትስ?” ምክንያቱም የተቀደሰው የአላህ ዛት የፍጡራንን ዛት የማይመስል ከሆነ ባህሪውም እንደዚሁ የፍጡር ባህሪዎችን አይመሳሰልም፡፡
በውይይቱ ሊገፋ አይችልም፤ ምናልባት ግን፤ -“እንዴት ምንነቱን እና ዝርዝር ሁኔታዉን “ከይፊያውን” የማላውቀውን ባህሪ ለአላህ አረጋግጣለሁ”? ሊል ይችላል።
ምላሹም፤
-ምንነቱን እና ዝርዝር ሁኔታዉን “ከይፊያውን” የማታውቀውን ዛት እንዳፀደቅክ ሁሉ “ከይፊያውን” የማታውቃቸውን ባህሪዎችም ማጽደቅ ይገባሀል” የሚል ይሆናል፡፡
2ተኛው መሰረታዊ ህግ
ስለተወሰኑ የአላህ ባህሪዎች መናገር ስለሌሎቹ ባህሪዎች እንደመናገር ነው!
ባህሪዎችን በመቀበልም ይሁን ባለመቀበል ስለከፊል የአላህ ባህሪዎች መናገር ስለሌሎችም እንደመናገር ነው፡፡ ይህ መሰረት ከፊል ባህሪዎችን አፅድቀው ሌሎችን የሚቃወሙ ቡድኖችን ግዴታ ውስጥ ያስገባል፡፡
አንድ ሰው፤ ለአላህ፤ መስማት “ሰምዕ” ፣ መመልከት “በሰር”፣ ህያው መሆን “ሀያት” ፣እውቀት “ዒልም”፣ ችሎታ “ቁድራህ” እና ሌሎችንም ባህሪዎች አፅድቆ በትክክለኛ ትርጉሞቻቸው እየተረጐመ ሌሎች እንደ መውደድ “ሙሀባህ”፣መቆጣት “ገደብ”፣ እዝነት “ረህማህ”፣ ከዓርሽ በላይ መሆን ‘ኢስቲዋዕ’፣ እና የመሳሰሉትን ደግሞ ቀጥተኛ ትርጉሞቻቸውን የማይቀበል እና የማያጸድቃቸው ከሆነ፤ እርስ በእርስ የሚጋጩ ቀመሮችን ተጠቅሟልና ስህተት ውስጥ ነው።
ይህንን ሰው እንዲህ ልናስረዳው እንችላለን፤ “ባፀደቅካቸውና በተቃወምካቸው ባህሪዎች መካከል ምንም ለውጥ የለም፤ ምክንያቱም ስለ አንዱ ባህሪ የምትናገረውን ስለሌላውም ልትናገረው ትችላለህ፡፡
ህይወት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ መስማትና መመልከትን ስታጸድቅ በእነዚህ ባህሪዎች ከሚገለጹ ፍጡራን ባህሪዎች ጋር የማታመሳስል ከሆነ፤ ያስተባበልካቸውንም ባህሪዎች በዚሁ መልኩ ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ሳታመሳስል ማጽደቅ ትችላለህ።
ይህንን የማታደርግ ከሆነ ግን አቋምህ የተምታታ ይሆናል።”
ይህ መሰረታዊ ህግ እጅግ ጠቃሚ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም።
3ተኛው መሰረታዊ ህግ
የስሞችና የቃላት መመሳሰል የይዘት መመሳሰልን ግድ አይልም!
አላህ በቁርዓን ላይ እራሱን ከሰየመባቸው ስሞች አንዳንዶቹን ባርያዎቹንም ገልጿል።ለምሳሌ፤ አላህ እራሱን ህያውነትን የሚያሳየውን “አል-ሀይ” የሚለውን ስያሜ ሰጥቷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ
‹‹አላህ ከእርሱ በቀር በሀቅ የሚያመለክ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው በራሱ የተብቃቃ ነው፡፡››(አል በቀራህ 255)
ባሮቹንም እንዲሁ ህያውነትን በሚያሳየው ተመሳሳይ ቃል ገልጿቸዋል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَمُخْرِجُ الْمَيِّتِ مِنَ الْحَيِّ
‹‹ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው አውጪ ነው፡፡›› (አል አንዓም 95)
ይሁንና ሁለቱ ህያውነቶች ግን ፍጹም ይለያያሉ።
በተመሳሳይ መልኩ አላህ ለጀነት ሰዎች ስለተዘጁ ብዙ ጸጋዎች ነግሮናል። ለምሳሌ፤ ስለ መብሉና መጠጡ፤ በውስጧ ዉሀ፤ ወተት፣ማር፣ስጋ፣ የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ እና ሌሎችም ጸጋዎች ነግሮናል። ስለ ወንዞቿ፣ የመኖሪያ ህንጻዎቿ እና ሌሎችንም ነግሮናል። ነገር ግን ማንኛውም ሰው ይህንን ሲሰማ ዱንያ ላይ ካሉ ጸጋዎች ጋር ስማቸው ስለተመሳሰለ፤ ይህ መመሳሰል ደግሞ ጸጋነታቸውን ስለሚያጠፋ እነዚህን ነገሮች አልቀበልም አይልም። ስማቸው ስለተመሳሰለም ዱንያ ላይ ካሉ ጸጋዎች አይለዩምም አይልም። ታላቁ ሰሀብይ አብዱላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ብለዋል፤
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: "ليس في الجنة شيء مما في الدنيا إلا الأسماء".
‹‹ጀነት ውስጥ ዱንያ ላይ ካለው ነገር ምንም የለም፤ ከስም መመሳሰል በስተቀር»
ይህ የስም መመሳሰል ሃሳብን ለመረዳት ከማገልገሉ ያለፈ ብዙ ትርጉም የለውም። በምድር ያሉ እና በጀነት ያሉ ጸጋዎች በስም አንድ ቢሆኑም ፍጹም የማይመሳሰሉ ከሆነ፤ በመካከላቸዉም ያለዉን ልዩነት ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅም። ስለዚህም፤ አላህ ለባሮቹ ያዘጋጀውን ጀነት በአዕምሮ መቅረጽ እንደማይቻል ተከታዩ ሀዲስ ያሳውቀናል።
عن أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم: قَالَ اللهُ: أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ فَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ﮋفَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنِ ﮊ رواه البخاري ومسلم
አቡሁረይራ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፤ አላህ እንዲህ አለ ፦ ለጻድቃን ባሪያዎቼ፤ የማንም አይን ያላየውን፣ የማንም ጆሮ ያልሰማውን፣ በማንም ሰው ልቦና ውል ያላለ (ጸጋ) ነው።
“የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ አሉ”፤ ከፈለጋችሁ ተከታዩን አንቀጽ አንብቡ፡
«فَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُن»ِ
«ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡» አስ-ሰጅዳ
አንድ ፍጡር ከሌላ ፍጡር ጋር ያለው አለመመሳሰል በዚህ ደርጃ ከሆነ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ምንም አይነት መመሳሰል የሚታሰብ አለመሆኑ ግልጽ ነው። በፈጣሪ ባህሪዎችና በፍጡር ባህሪዎች መካከል የስም መመሳሰል ቢኖር እንኳ መመሳሰሉ ከስም እንደማያልፍ ልንረዳ ይገባል።
ይህ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙርያ የሚነሱ ብዥታዎችንና ማምታቻዎችን ሁሉ በአላህ ፍቃድ የሚቀርፍ መሰረታዊ መርሆ ነው። በሚገባ ብናውቀው በቀላሉ ለሌሎች ማስረዳት እንችላለን።
4 ተኛው መሰረታዊ ህግ
ሁሉም የአላህ ስሞች እጅግ ያማሩ ውብ ናቸው
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى
‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ›› (አል አዕራፍ 18ዐ)
በእነዚህ ስሞች የሚሰየመው ያማረውና የላቀው አላህ ስለሆነ፤ ስሞቹ የተሟሉና የተዋቡ፣ በምንም መልኩም ጉድለት የሌለባቸውና ጉድለትን የማይጠቁሙ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፦ “አል ሀይ” (ህያው) ከአላህ ስሞች ውሰጥ አንዱ ሲሆን የሚያመለክተውም ሁልጊዜ ዘውታሪ የሆነውን እና ከዚህ ቀደምም ሆነ ወደፊት መወገድ የማይገጥመውን የተሟላ ህይወት ይጠቁማል፡፡ ህይወት ደግሞ እንደ እውቀት፣ ችሎታ፣ መስማትና መመልከት የመሳሰሉትን የተሟሉ ባህሪዎች ያካትታላል፡፡
ሌላ ምሳሌ፦ “አል ዓሊም” (አዋቂ) የተሰኘው የአላህ ስም፤ ከዚህ በፊት አለማወቅ ያልቀደመው፣ ወደፊት መርሣት የማይገጥመው በሁሉም ነገር ላይ የተሟላ እዉቀት ያለው መሆኑን የሚያስረዳ ስያሜ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
قَالَ عِلْمُهَا عِنْدَ رَبِّي فِي كِتَابٍ لَا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنْسَى
‹‹(ሙሳም) «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡ (ጣሀ 52)
የእሱ እውቀት የፍጡራንን ስራዎችም በጥቅሉና በዝርዝር የሚያጠቃልል ነው፡ ፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
يَعْلَمُ خَائِنَةَ الْأَعْيُنِ وَمَا تُخْفِي الصُّدُورُ
‹‹(አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡›› (ጋፊር 19)
እያንዳንዱ የአላህ ስሞች በነጠላ ሲታዩ ያማሩ ሲሆኑ ሁለት ስሞች አብረው ሲቆራኙ ደግሞ በምሉዕነት ላይ ምሉዕነትንና ውበትን ይደርባሉ፡፡
ለምሳሌ “አልዓዚዙል ሀኪም” (አሸናፊ ጥበበኛ) እነኚህን ሁለት ስሞች አላህ ቁርአን ላይ በብዙ ቦታዎች ላይ አቆራኝቶ ሲገልፃቸው እናገኛለን፡፡
እያንዳንዱ ስም የራሱን ምሉዕነት ያመለክታል፡፡ “አልዓዚዝ” ‘አሸናፊ’ የተሰኘው ስም የማሸነፍ ባህሪን የሚያሳይ ሲሆን፣ “አልሀኪም” ‘ጥበበኛ’ የተሰኘው ስም ደግሞ ፍትሀዊ ማስተዳደር “ሁክም” እና ሁሉን ነገር በተገቢው ቦታ ማድረግን “ሂክማ” የሚያሳይ ነው። ሁለቱ ስሞች ሲቆራኙ ደግሞ የሚጠቁሙት ሌላ ምሉዕነት አለ፡፡ እርሱም፤ የአላህ አሸናፊነት ከጥበብ “ሂክማ” እና ከፍትሀዊ ማስተዳደር “ሁክም” ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በምድር ላይ ያሸነፉ ሀያላን እንደሚፈፅሙት ግፍ፣ በደልና ጭቆና የሌለበት ጌታ ማለት ነው፡፡ እንደዚሁ፤ የአላህ ጥበብ “ሂክማ” እና ፍትሀዊ ማስተዳደር “ሁክም” በሙሉ አሸናፊነት የታጀበ በመሆኑ፣ እንደፍጡር የማስተዳደር ስልጣን ሽንፈትና ውርደት በፍጹም አያገኘውም፡፡
5 ተኛው መሰረታዊ ህግ
የአላህን ስሞችና ባህሪያዎች ያለማስረጃ ማፅደቅ አይፈቀድም
አህሉሱና ወልጀማዓህ፤ አላህ እርሱን የሰየመባቸውን በቁርዓንና በሱና የተረጋገጡ ስያሜዎች እና ባህሪዎች ሁሉ ይቀበላሉ። የአላህን ስሞችና ባህሪዎች “ተውቂፊይ” ናቸውና ያለማስረጃ ማጽደቅ አይፈቀድም። በሰዎች አስተያየት የማይጸድቁና የማይሻሩ በመሆናቸው ምንም ሳይጨመርና ሳይቀነስ በቁርአን ወይም በሀዲስ በተረጋገጡት ስሞችና ባህሪዎች ብቻ ማመን ግዴታ ይሆናል፡፡
ለአላህ የሚገቡ ባህሪዎች በአእምሮ በማሰላሰል የምንደርስባቸው ስላልሆኑ የለአላህን ስሞችንና ባህሪዎች በማፅደቅ ረገድ በቁርዓንና በሐዲስ ጥቅሶች ብቻ መገደብ የግድ ነው፡፡ ማንም ሰው መረጃን ሳይከተል “ይህ የአላህ ስም ነው” ወይም “ይህ የአላህ ስም አይደለም” ማለት አይችልም። ይህ ስለ አላህ የማያውቁትን መናገር አላህ ከሽርክ ጋር አቆራኝቶ የጠቀሰው ከባድ ወንጀል ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَنْ تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَنْ تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ الأعراف:33
«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡» (አል አዕራፍ 33)
በሌላም አንቀጽ እንዲህ ይላል፦
وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا
‹‹(የሰው ልጅ) መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ (ባለቤታቸው) ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፤ ለአንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡›› (አል ኢስራእ 36)
ይህ አቋም የታላላቅ የኢስላም መሪዎች አቋም ነው፡፡ አንድን ነገር አውቀነው ልንገልፀው ይቻለን ዘንድ ሶስት መንገዶች አሉ::
• ያንን ነገር በማየት ስለእርሱ ማወቅ፤
• አምሳያውን በመመልከት ስለእርሱ ማወቅ፤
• እርሱን ከሚያውቀው አካል ትክክለኛ መረጃን በመውሰድ ስለእርሱ ማወቅ፤
ጌታችን አላህን ስላላየነው፤ አምሳያም ስለሌለው፤ ስለ ባህሪዎቹ ያለን እውቀት በሶስተኛው መንገድ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ስለ አላህ ባህሪዎች ከማንም ይበልጥ የሚያውቀው አላህ እራሱ ነው። ከአላህ ቀጥሎ ደግሞ በወህይ ያስተማራቸው የአላህ መልክተኛ ናቸው። ስለዚህም፤ አላህ የሚገለፀባቸዉን ስሞችና ባህሪዎች የምናውቀው ከአላህና ከመልዕክተኛው ንግግር ብቻ ነው።
የአላህን ስሞች ማጽደቅ ምን ምን ነገሮችን ያካትታል?
አህሉሱና ወልጀማዓህ፤ የአላህን ስሞች ተቀብለው ሲያረጋግጡ፤
1- ይህ የአላህ ስያሜ መሆኑን ያምናሉ
2- ይህ ስም የሚያመላክተውን ባህሪ ያምናሉ
3- ይህ ስም በፍጡራን ላይ ያለውን ተጽዕኖ ያምናሉ
ለምሳሌ፤ ከአላህ ስሞች መካከል “አሰሚዕ”"السميع" የሚለውን ስናጸድቅ:
1- “አሰሚዕ” ከአላህ ስሞች መካከል መሆኑን እናምናለን። አላህ በስሞቹ እንድንለምነው አዞናል እና ‘ያ ሰሚዕ’ ብለን ዱዓ እናደርግበታለን።
وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى فَادْعُوهُ بِهَا... الأعراف :180
‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ በእርሷም ጥሩት፡፡ እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፡፡ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ›› (አል-አዕራፍ 180)
ልጆቻንን ‘አብዱሰሚዕ’ ብለን መሰየምም እንችላለን።
2- ይህ ስም የሚያመላክተውን የመስማት ባህሪ ለአላህ እናፀድቃለን። አላህ ማንኛውንም ድምጽ እንደሚሰማ እናምናለን።
3- አላህን በዚህ ስም ውጤት እናመልከዋለን። ለምሳሌ፤ “ሰሚዕ” ስንል አላህ የፍጡራኑን ንግግር እንደሚሰማ እንረዳለን፤ ስለዚህም አላህ ንግግራችንን ሁሉ እንደሚሰማን በማመን መልካምን እንጂ ላለመናገር እንሞክራለን፣ አንደበታችንን ከመጥፎ ንግግር እንቆጥባለ። “በሲር” ስንል አላህ ሁሉንም ነገር እንደሚመለከት፣ “አረሂም” ስንል አላህ ለፍጡጡራኑ እንደሚያዝን… ወዘት እንገነዘባለን። ስሞቹ በውስጣቸው ያዘሉዋቸው ባህሪዎች ለፍጡራን የሚደርሱ፣ ወደ ፍጡራኑ የሚሸጋገሩ ናቸው ማለት ነው። ስለዚህም ወደ ፍጡራን የሚደርሱ የስሞች ውጤቶችን ማስተዋልና አላህንም በዉጤቶቹ መሰረት ማምለክ ተገቢ ነው።
☞ “የአማኞች ጋሻ”
# አስማዕወሲፋት
የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክ ያድርጉ
https://www.facebook.com/asmaewesifat
ሼር ማድረግም እንዳይረሱ