Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡለማዎች ስለ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን አብዱልወሀብና ስለ ዳዕዋቸው ምን አሉ?


ኡለማዎች ስለ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን አብዱልወሀብና ስለ ዳዕዋቸው ምን አሉ?

ዝግጅት፤ ኡስታዝ ሱለይማን አብደላ

ለኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ እና ለተውሂድ ዳእዋቸው አድናቆታቸውን ከቸሩ የተለያዩ ሀገራት አሊሞች ንግግሮች በጥቂቱ ፦

(1) ሸይኽ ዓብዱል ወሃብ ኢብኑ ሱለይማን (ወላጅ አባታቸው)

“ የኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ ወንድም ሱለይማን ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ እንደተናገረው ሸይኽዓብዱል ወሃብ ገና ከ ሙሃመድ ልጅነት ጀምሮ በልጃቸው ብልህነት እና አዋቂነት ይደነቁበት ነበር :: ከልጄ ሙሃመድ አንዳንድ ፈዋኢዶችን (ሸሪዓዊእውቀቶችን) ቀስሜአለሁ በማለት ለወንድሞቻቸው በጻፏቸው መልእክቶች ውስጥ ስለ ልጃቸው ታላቅነት ጠቅሰዋል::” (ሲያነቱል ኢንሳን) (ዑንዋኑል መጅድ)

(2)አል ኢማም ሙሃመድ ኢብን ዓሊይ አሽሸውካኒይ (የመን)

*** قال العلامة محمد بن علي الشوكانى
"وفى سنة 1215 وصل من صاحب نجد المذكور (عبد العزيز بن سعود) مجلدان لطيفان أرسل بهما إلى حضرة مولانا الإمام حفظه الله أحدهما يشتمل على رسائل لمحمد بن عبد الوهاب كلها فى الإرشاد إلى إخلاص التوحيد والتنفير من الشرك الذى يفعله المعتقدون في القبور وهى رسائل جيدة مشحونة بأدلة الكتاب والسنة والمجلد الآخر يتضمن الرد على جماعة من المقصرين من فقهاء صنعاء وصعدة ذاكروه فى مسائل متعلقة بأصول الدين وبجماعة من الصحابة فأجاب عليهم جوابات محررة مقررة محققة تدل على أن المجيب من العلماء المحققين العارفين بالكتاب والسنة وقد هدم عليهم جميع ما بنوه وأبطل جميع ما دونوه لأنهم مقصرون متعصبون"

وقال أيضا "فوصل إليه الشيخ العلامة محمد بن عبد الوهاب الداعى إلى التوحيد المنكر على المعتقدين فى الأموات فأجابه وقام بنصره وما زال يجاهد من يخالفه وكانت تلك البلاد قد غلبت عليها أمور الجاهلية وصار الاسلام فيها غريبا "

البدر الطالع بمحاسن من بعد القرن السابع

« ወደ እኛ ሀገር (የመን ) አል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ ያዘጋጃቸው ሁለት መጽሃፎች ደርሰው ነበር ፦ በአንደኛው ውስጥ በቁርአን እና በሀዲስ ማስረጃዎች የታገዙ ዒባዳን(አምኮትን )ለአሏህ ብቻ መዋል እንዳለባቸው የሚያስተምሩ እና ሰዎች በሙታን ላይ ተገቢ ያልሆነ እምነትን በመያዝን የሚፈጽሟቸውን የሽርክ ተግባራትን የሚያወግዙ እና የሚቃወሙ፤ በሁለተኛው መጽሀፉ ውስጥ ደግሞ በአንዳንድ በሰንዓህ እና ሰዕዳህ የሚገኙ ፉቀሃዎች (የፊቅ ሂምሁራን) በተወሰኑ ሶሃቦች ላይ እና በአንዳንድ እምነት ነክ ጉዳዮች ላይ እርምትን የሚሰጡ በሚገባ የተስተካከሉ እና በጥናት ላይ የተመረኮዙ ጸሀፊው ቁርአንን እና ሱናን ጠንቅቆ ማወቁን የሚያሳዩ እና ከታላላቅ ዑለሞች ተርታ የሚያስመድበው ሆኖ አግኝቼዋለሁ።” (አል በድሩጧሊዕ)

በሌላም ቦታ ላይ እንዲህ ብለዋል፤
«አሸይኹል ዓልላማህ ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ የተውሂድ መምህር እና ባእድ አምልኮን ተቃዋሚ ...” (አል በድሩጧሊዕ)

(3) አስ–ሰይድ መህሙድ ሹክሪ አል ኣሉሲይ (ዒራቅ)

*** قال السيد محمود شكري الألوسي
"إني قد وقفت على رسالة صغيرة الحجم كثيرة الفوائد تشتمل على نحو مائة مسألة من المسائل التي خالف فيها رسول الله صلى الله عليه وسلم أهل الجاهلية من الأميين والكتابيين، وهي أمور ابتدعوها ما أنزل اللهبها من سلطان ولا أخذت عن نبي من النبيين، ألفها الإمام محيي السنة، ومجدد الشريعة النبوية، أبو عبد الله محمد بن عبد الوهاب النجدي الحنبلي، تغمده الله تعالى برحمته." (مقدمة شرح مسائل الجاهلية)

መሳኢሉል ጃሂሊያህ የሚባለውን የአል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ መጽሃፍን እንዲህ ይገልጹታል፤

« መጠኑ አነስ ያለ በውስጡ የተካተቱት ፈዋኢዶች የበዛ አዘጋጁም አል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ የሱና ተቆርቋሪ እና ሙጀዲድ (የተሀድሶ መሪ) ነው” (ሙቀዲመቱ ሸርሁ መሳኢሉል ጃሂሊያህ )

(4)ኽይረዲን አዝዘርከሊይ (ሶሪያ)

*** خير الدين بن محمود بن محمد بن علي بن فارس، الزركلي الدمشقي

"...ثم انتقل إلى العيينة، ناهج منهج السلف الصالح، داعياً إلى التوحيد الخالص ونبذ البدع وتحطيم ما علق بالاسلام من أوهام..."(الأعلام)

ስለ አል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ የህይወት ታሪክ ሲያትቱ «ሰለፎችን (ቀደምት ዑለሞችን )አርአያ በማድረግ ጥርት ወዳለው ተውሂድ ተጣሪ እና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማውገዝ ኢስላም ላይ የተንጠለጠሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ተቃዋሚ ነበር» ( አል አዕላም )

(5) ሸይኽ ሙሃመድ ረሺድ ሪዷ (ግብፅ)

*** الشيخ محمد رشيد رضا
"ولقد كان الشيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي ، من هؤلاء العدول المجددين قام يدعون إلى تجريد التوحيد ، وإخلاص العبادة وحده ، بما شرعه في كتابه وعلى لسان رسوله خاتم النبيين صلى الله عليه وسلم . وترك البدع والمعاصي وإقامة شعائر الإسلام المتروكة وتعظيم حرماته المنتهكة المنهوكة " (مقدمة- صيانة الإنسان عن وسوسة الشيخ دحلان)

"وقد كان من حسنات تأثير محمد بن عبد الوهاب المجدد للإسلام في نجد إبطال عبادة الجن وغير الجن منها، ولم يبق فيها إلا أهل تجريد التوحيد وإخلاص العبادة لله..."
(تفسير المنار)

“አል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ ታማኝ ከሆኑ ሙጀዲዶች አንዱ ነው። ወደ ተውሂድ ተጣሪ አምልኮት ለአሏህ ብቻ እንዲደረግ አስተማሪ ነበር " (ሲያነቱል ኢንሳን የተሰኘው መፅሀፍ መቅድም)

(6) ታላቁ ሸይኽ አል ዓላማህ አብዱል ሃሚድ ባዲስ (አልጄሪያ)

*** قال الشيخ العلامة عبد الحميد باديس
" وإنما كانت غاية دعوة ابن عبد الوهاب تطهير الدين من كل ما أحدث فيه المحدثون من البدع ، في الأقوال والأعمال والعقائد والرجوع بالمسلمين إلى الصراط السوي من دينهم القويم بعد انحرافهم الكثير وزيغهم المبين " (موقف علماء الجزائر من الإمام محمد بن عبد الوهاب ودعوته السلفية)

«የ አል ኢማም ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ ዳዕዋ አላማ፦
በዓቂዳ ዘርፍም ሆነ በሌሎችም ርእሶች በኢስላም ስም ከተፈጠሩ እና መጤ ከሆኑ ነገሮች ኢስላምን ማፅዳት ሙስሊሞች የተሳሳተን መንገድ መከተል ትተው ወደ ትክክለኛው ኢስልማዊ ጎዳና መመለስ ነው።»

(7) ሸይኸ ሙሃመድ አገዛሊይ
(ግብፅ)
*** قال الشيخ محمد الغزالي "رفع محمد بن عبد الوهاب شعار التوحيد ، وحق له أن يفعل ! فقد وجد نفسه في بيئة تعبد القبور ، وتطلب من موتاها ما لا يطلب إلا من الله سبحانه ... وقد رأيت بعيني من يقبلون الأعتاب ويتمسحون بالأبواب ويجأرون بدعاء فلان أو فلان ، كي يفعل كذا وكذا ! ما هذا الزيغ ؟ ما الذي أنسى هؤلاء ربهم ؟
وصرفهم عن النطق باسمه والتعلق به ؟ وماذا يرجو العبيد من عبد مثلهم لا يملك لنفسه نفعا ولا ضرا ؟ إنه لو كان حيا ما ملك لهم شيئاً ، فكيف وهو ميت ؟ .. "
(مائة سؤال عن الإسلام )

«ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ በነበረበት አካባቢ የመቃብር አምልኮ ስርአት እጅግ በመስፋፋቱ እንዲሁም ከአሏህ በስተቀር ማንም ሊጠየቅ የማይገባን ነገር ሙታንን በመጠየቃቸው ምክንያት ሙሃመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሃብ የተውሂድን አርማ አንግቦ ተነሳ ያንን ማድረጉ ተገቢ ነበር :: እነዚህን መቃብር አምላኪዎች የቀብር በሮችን ሲሳለሙ(ሲስሙ)በየመቃብር ደጃፎች ሲያጎበድዱ እከሌ ሆይ (ሟቹን) እንዲህ አድርግልን እንዲያ ፈፅምልን እያሉ በመማፀን ሲጣሩ እኔ እራሴ
ተመልክቼአለሁኝ :: ምን አይነት ጥመት ነው ??!! እነዚህን ሰዎች ጌታቸውን ስሙን ከመጥራት እና ወደ እርሱ ጉዳያቸውን ከማቅረብ ያዘናጋቸው ምንድን ነው ??! እንደራሳቸው ደካማ የሆነን ደካማ ፍጡርን ምን ያደርግልናል ብለው ነው የሚማፀኗቸው ??! "
(ሚአቱ ሱኣል አኒል ኢስላም)

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው!