Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዑዝር ቢል ጀህል እና ኢብኑ ተይሚያ || ኢብኑ ሙነወር

 



ዑዝር ቢል ጀህል እና ኢብኑ ተይሚያ

~~~~~~~~~~~~~~

ቅድመ ነገር፡- ልክ እንደ ወትሮዬ የዛሬውም ፅሑፌ ለአብዛኛው አንባቢ ረጅም በመሆኑ እየተሳቀቅኩ ነው። ግን ደግሞ ወኔ ኖሯቸው ለቁም ነገር ባይታክቱ ብዬ በእጅጉ እመኛለሁ። እህት ወንድሞቼ! በርግጠኝነት እኔ ለመፃፍ የፈጀብኝን ጊዜ ያክል አይወስድባችሁምና በትእግስት እንድታነቡት እጠይቃለሁ። እውነት ለመናገር ርእሱ ብዙ ብዥታ የሚነዛበት በመሆኑ ከዚህ የተሻለ ሰፊ ዳሰሳ የሚፈልግ ነው። ቢሆንም ለጊዜው በዚህ መጠን ለመብቃቃት ወስኛለሁ።

አላዋቂ ሰዎች ሺርክ ላይ ቢወድቁ ከኢስላም ይወጣሉ ወይ? የሚለውን በተመለከተ ውዝግብ መኖሩ የሚታወቅ ነው። አንዳንድ የተክፊር አመለካከት የያዙ ሰዎች ለአላዋቂ ሰው ዑዝር የሚሰጡ ሰዎች ላይ በጅምላ የክህደት ብይን ሲሰጡ ይታያሉ። ትልልቅ ዑለማኦችን ያለምንም ሐያእ በክህደት መፈረጅን እንደ ጀብድ ሲይዙት ማየት እጅጉን ያሸማቅቃል። ቁርኣንና ሐዲሦችን አጣመው በመተርጎም “እኛ አላህ ያከፈረውን ነው ያከፈርነው” የሚል አጉል ሙግት ይሞግታሉ። ለጠማማ አካሄዳቸው በሰፊው ከሚያጣቅሷቸው ዑለማኦች ውስጥ አንዱ ታዲያ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ናቸው፣ ረሒመሁላህ። ለዚህ ብልሹ አስተሳሰብ ኢብኑ ተይሚያን ያለ አግባብ ማጣቀስ እሳቸውን በኸዋሪጅነት ለሚከሱ ፅንፈኛ ሱፍዮች መንጠላጠያ ሆኗል። ኢብኑ ተይሚያ ግን ፈፅሞ ከዚህ አይነት አመለካከት የፀዱ ናቸው። ልክ ዛሬ ላይ ተክፊሮች ላይ እንደምናየው ለመሃይማን ዑዝር ሰጥችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት የተውሒድ ሰዎችን ከኢስላም ሊያስወጡ ቀርቶ ሺርክ ላይ የወደቁትን መሃይማኖች እንኳ ከኢስላም የሚስወጡ አልነበሩም። 

ንግግሮቻቸውን ከነ ምንጮቻቸው ከማስፈሬ በፊት አንድ ማሳሰቢያ ላስቀድም። የዘመናችን ኸዋሪጆች የኢብኑ ተይሚያን ንግግር ዋጋ ለማሳጣት “እሳቸው ዑዝር የሚሰጡት በስውር ነገሮች ብቻ እንጂ እንደ ኢስቲጋሣ ባሉ ግልፅ ሺርኮች ላይ አይደለም” የሚል ማምታቻ ይነዛሉ። አንባቢ ሆይ! በዚህ ፅሑፌ ያቀረብኳቸው የኢብኑ ተይሚያ ንግግሮች በሙሉ የዛሬዎቹ ተክፊሮች ዑዝር የማይሰጡባቸውንና አልፎም “ያላከፈረ ይከፍራል” በማለት ሰንሰለታማ የተክፊር ዘመቻ የሚከፍቱባቸውን ግልፅ ሺርክ ጋር የሚያያዙ ነጥቦችን ነው። ወደ ንግግሮቻቸው፡-

قال تعالى: (وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُمْ بِاللَّهِ إِلَّا وَهُمْ مُشْرِكُونَ ((يوسف: 106) قال طائفة من السلف: يسألهم مَن خلق السماوات والأرض؟ فيقولون: الله، وهم يعبدون غيره.وإنما كانت عبادتهم إيَّاهم أنهم يدعونهم ويتخذونهم وسائطَ ووسائلَ وشُفعاءَ لهم، فمن سلكَ هذا السبيلَ فهو مشرك بحسب ما فيه من الشرك.

وهذا الشركُ إذا قامت على الإنسان الحجةُ فيه ولم يَنتهِ، وَجَبَ قتلُه كقتلِ أمثالِه من المشركين، ولم يُدفَنْ في مقابرِ المسلمين، ولم يُصَلَّ عليه. وإمَّا إذا كان جاهلاً لم يَبلُغْه العلمُ، ولم يَعرِف حقيقةَ الشرك الذي قاتلَ عليه النبي – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ – المشركين، فإنه لا يُحكَم بكُفْرِه، ولاسِيَّما وقد كَثُر هذا الشركُ في المنتسبين إلى الإسلام، ومن اعتقدَ مثلَ هذا قُربةً وطاعةً فإنه ضَالٌّ باتفاقِ المسلمين، وهو بعد قيامِ الحجة كافر.

“የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‘አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ አያምኑም።’ [ዩሱፍ፡ 106] ከፊል ቀደምቶች ይህንን ሲተነትኑ እንዳሉት ‘ሰማያትና ምድርን ማን እንደፈጠረ ሲጠይቃቸው አላህ ነው ይላሉ። ከመሆኑም ጋር ግን ሌሎችንም ያመልካሉ።’ ታዲያ እነዚያ ያመልኩ የነበረው እነሱን በመማፀን፣ አገናኞችና አማላጆቻቸው አድርገው በመያዝ ነው። ይህንን መንገድ የተከተለ ሰው ባለበት የሺርክ መጠን ሙሽሪክ ነው።

ይሄ ሺርክ በአንድ ሰው ላይ ማስረጃ ደርሶት ካልታቀበ የሱ አምሳያ አጋሪዎች እንደሚገደሉት ይገደላል። በሙስሊሞች መቃብርም አይቀበርም። አይሰገድበትምም። እውቀት ያልደረሰው መሃይም ከሆነና ነቢዩ ﷺ አጋሪዎችን የተዋጉበትን ሺርክ ተጨባጭ ያላወቀ ከሆነ ግን ክህደት አይበየንበትም። በተለይ ደግሞ ይሄ ሺርክ ወደ ኢስላም በሚጠጉ ሰዎች ላይ በርግጥም ተንሰራፍቷል። እንዲህ አይነቱን (ሺርክ) መቃረቢያና ፅድቅ አድርጎ ያመነ ሰው በሙስሊሞች ስምምነት ጠማማ ነው። ማስረጃ ከቆመበት በኋላም ከሃዲ ነው።” [ጃሚዑል መሳኢል፡ 3/150-51]

ልብ በሉ! ብዥታን መግፈፍ በሚችል መልኩ ማስረጃ እስከሚደርስ ድረስ ግን ከነ ጥመቱ ሙስሊም ነው እያሉ ነው። የቀረበው ትልቁ ሺርክ መሆኑ ይስተዋል።

 وقد ذهب كثير من مبتدعة المسلمين من الرافضة والجهمية وغيرهم إلى بلاد الكفار فأسلم على يديه خلق كثير، وانتفعوا بذلك وصاروا مسلمين مبتدعين، وهو خير من أن يكونوا كفارًا

“ከራፊዷ፣ ጀህሚያና ሌሎችም የሆኑ በርካታ ሙብተዲዐ ሙስሊሞች ወደ ክህደት ሃገር በመሄድ በነሱ አማካኝነት ሰፊ ህዝብ ሰልሟል። በዚህም (የሰለሙት ሰዎች) በመጠቀማቸው ሙብተዲዐ ሙስሊሞች ሆነዋል። ከሃዲዎች ከሚሆኑ ይሄ ይሻላል።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 13/96]

ልብ በሉ! ራፊዷ ማለት ከሺዐ ቡድኖች ውስጥ ጥመታቸው ከፍ ያሉት ናቸው። ራፊዷና ጀህሚያ ከሱፍያ በጣም የባሱ ናቸው። ከመሆኑም ጋር ኢብኑ ተይሚያህ - ረሒመሁላህ - በራፊዷ፣ ጀህሚያና መሰሎቻቸው የሰለሙ ሰዎችን ከነ ጥመታቸው ሙስሊሞች አድርገው ነው የቆጠሯቸው። 

من يعتقد أن شيخه يرزقه، أو ينصره، أو يهديه، أو يغيثه، أو يعينه، أو كان يعبد شيخه، أو يدعوه ويسجد له، أو كان يفضله على النبي – صلى الله عليه وسلم–  تفضيلا مطلقا أو مقيدا في شيء من الفضل الذي يقرب إلى الله تعالى، أو كان يرى أنه هو أو شيخه مستغن عن متابعة الرسول؛ فكل هؤلاء كفار إن أظهروا ذلك، ومنافقون إن لم يظهروه. وهؤلاء الأجناس؛ وإن كانوا قد كثروا في هذا الزمان؛ فلقلة دعاة العلم والإيمان وفتور آثار الرسالة في أكثر البلدان. وأكثر هؤلاء ليس عندهم من آثار الرسالة وميراث النبوة ما يعرفون به الهدى وكثير منهم لم يبلغهم ذلك. وفي أوقات الفترات وأمكنة الفترات: يثاب الرجل على ما معه من الإيمان القليل ويغفر الله فيه لمن لم تقم الحجة عليه. … وأصل ذلك أن المقالة التي هي كفر بالكتاب والسنة والإجماع؛ يقال: هي كفر قولا يطلق…، ولا يجب أن يحكم في كل شخص قال ذلك بأنه كافر حتى يثبت في حقه شروط التكفير وتنتفي موانعه اهـ. “


“ሸይኹ እንደሚረዝቀው ወይም እንደሚያግዘው ወይም እንደሚመራው ወይም እንደሚያግዘው የሚያምን፤ ወይ ደግሞ ሸይኹን የሚያመልክ፣ ወይ ደግሞ የሚማፀነውና ሱጁድ የሚወርድለት፣ ወይ ደግሞ በሆነ ወደላቀው አላህ በሚያቃርብ ክብር - በደፈናውም ሆነ በተገደበ መልኩ - ከነቢዩﷺ  የሚያስበልጥ፣ ወይ ደግሞ እርሱ እራሱ ወይም ሸይኹ መልእክተኛውን ከመከተል የተብቃቃ እንደሆነ የሚያምን የሆነ ሰው እነዚህ በሙሉ ይህንን ግልፅ ካወጡ ከሃዲዎች ናቸው። ግልፅ ካላደረጉ ደግሞ ሙናፊቆች ናቸው። እንዲህ አይነቶቹ ምንም እንኳን በዚህ ዘመን የበዙ ቢሆንም ወደ እውቀትና ኢማን የሚጣሩ አካላት በመቅለላቸውና በአብዛኞቹ ሃገራት ነብያዊ ትውፊቶች በመደብዘዛቸው የተነሳ አብዛኞቹ እነዚህ ሰዎች ቅኑን ጎዳና የሚያውቁባቸው ኢስላማዊ ፋናዎችና ነቢያዊ ውርሶች የሏቸውም። ብዙዎቻቸው ይህ አልደረሳውም። በጨለማ ዘመናትና በጨለማ አካባቢዎች አንድ ሰው ማስረጃ ካልቆመበት ባለችው ጥቂት ኢማን ይመነዳል፤ በሱም ይምረዋል። … የዚህ መሰረቱ አንድ በቁርኣን፣ በሱናና በኢጅማዕ ክህደት የሆነ አቋም ክህደት ነው ተብሎ ቢገለፅም፣… ግና ይህንን ባለ ሰው ሁሉ ላይ ከሃዲ ተብሎ ክህደት መበየን አይገባም። ይህ የሚሆነውም ሰውየው ላይ ክህደት ለመበየን መስፈርቶች እስከሚሟሉ እና ከልካይ ነገሮች እስከሚወገዱ ድረስ ነው።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 35/164]

من دعا غير الله، وحج إلى غير الله هو أيضاً مشرك، والذي فعله كفر، لكن قد لا يكون عالماً بأن هذا شرك محرم، كما أن كثيراً من الناس دخلوا في الإسلام من التتار وغيرهم، وعندهم أصنام لهم، صغار من لبد وغيره، وهم يتقربون إليها ويعظمونها، ولا يعلمون أن ذلك محرم في دين الإسلام، ويتقربون إلى النار أيضاً، ولا يعلمون أن ذلك محرم، فكثير من أنواع الشرك قد يخفى على بعض من دخل في الإسلام ولا يعلم أنه شرك، فهذا ضال، وعمله الذي أشرك فيه باطل، لكن لا يستحق العقوبة حتى تقوم عليه الحجة 

“ከአላህ ሌላ ያለን የተማፀነና ከአላህ ሌላ ወዳለ ሐጅ ያደረገ ሙሽሪክ ነው። የሰራውም ክህደት ነው። ነገር ግን ይሄ ነገር የተከለከለ ሺርክ እንደሆነ ላያውቅ ይችላል። ልክ በርካታ ተታራውያንና ሌሎችም ከጡብና ከሌላም የተሰሩ ጣኦቶችን ይዘው ወደ ኢስላም እንደገቡት። እነሱ ይቃረቡባቸዋል፣ ያልቋቸዋልም። ይሄ ተግባር በኢስላም ሃይማኖት የተከለከለ እንደሆነ ግን አያውቁም። ወደ እሳትም እንዲሁ ይቃረቡ ነበር። ይሄ ተግባር የተከለከለ እንደሆነ ግን አያውቁም። ብዙ የሺርክ አይነቶች በአንዳንድ ወደ ኢስላም በገባ ሰው ላይ ሊሰወረውና ሺርክ እንደሆነ ላያውቅ ይችላል። ይሄ ጠማማ ነው። ያጋራበት ተግባሩም ከንቱ ነው። ነገር ግን ማስረጃ እስከሚቀርብበት ድረስ ቅጣት የሚገባው አይደለም።” [አልኢኽናኢያህ፡ 205 - 206]

والاستغاثة بمعنى أن يطلب من الرسول ما هو اللائق بمنصبه لا ينازع فيها مسلم، ومن نازع في هذا المعنى فهو إما كافر إن أنكر ما يكفر به، و إما مخطيء ضال، و أما بالمعنى الذي نفاه الرسول – صلى الله عليه وسلم-: فهو أيضاً مما يجب نفيها، ومن أثبت لغير الله ما لا يكون إلا لله فهو أيضاً كافر إذا قامت عليه الحجة التي يكفر تاركها

“እርዳታ መጠየቅ ሲባል ከመልእክተኛው ለደረጃቸው የሚመጥንን ነገር መጠየቅ ከሆነ ሙስሊም የሆነ ሰው አይጨቃጨቅበትም። በዚህ ላይ የሚጨቃጨቅ ሰው የሚያስከፍር ነገር አስተባብሎ ከሆነ ከሃዲ ነው። አለያ ደግሞ ጠማማ ስህተተኛ ነው። መልእክተኛውﷺ  የተቃወሙት (እርዳታ መጠየቅ) ከሆነ ይህም ሊቃወሙት ግድ ይላል። ለአላህ እንጂ የማይገባን ነገር ከአላህ ሌላ ላለ ያፀደቀ ሰው ተገቢው ማስረጃ ቀርቦበት ካልተቀበለ ከሃዲ ይሆናል።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 1/112] [አረድ ዐለል በክሪ፡ 346]

ልብ በሉ! ፍጡርን እርዳታ መጠየቅን (ኢስቲጋሣን) ነው በቂ ማስረጃ ሳይቀርብ አላዋቂ ሰው እንደማይከፈርበት እየገለፁ ያሉት።

فإنا بعد معرفة ما جاء به الرسول نعلم بالضرورة أنه لم يشرع لأمته أن تدعو أحداً من الأموات لا الأنبياء ولا الصالحين ولا غيرهم لا بلفظ الاستغاثة ولا بغيرها، ولا بلفظ الاستعاذة ولا بغيرها، كما أنه لم يشرع لأمته السجود لميت ولا لغير ميت ونحو ذلك، بل نعلم أنه نهى عن كل هذه الأمور و إن ذلك من الشرك الذي حرمه الله تعالى ورسوله لكن لغلبة الجهل وقلة العلم بآثار الرسالة في كثير من المتأخرين لم يمكن تكفيرهم بذلك حتى يتبين لهم ما جاء به الرسول – صلى الله عليه وسلم–  مما يخالفه

“እኛ መልእክተኛው ይዘውት የመጡትን ስንረዳ ለህዝቦቻቸው ነብያትንም፣ ደጋጎችንም ይሁን ሌሎችንም እርዳታን በመጠየቅ (ኢስቲጋሣህ) ቃልም ይሁን በሌላ ከሙታኖች አንድንም እንዲጣሩ አልደነገጉም። ልክ እንዲሁ ህዝቦቻቸው ለሙትም ይሁን ለሌላ አካል ሱጁድና መሰል (አምልኮቶችን) አልፈቀዱም። ይልቁንም ከነዚህ ነገሮች በሙሉ እንደከለከሉ ነው የምናውቀው። ይልቁንም እነዚህ ነገሮች የላቀው አላህና መልእክተኛው የከለከሏቸው እንደሆኑ እናውቃለን። ነገር ግን ብዙዎቹ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ዘንድ መሀይምነት በመንገሱና በነብያዊ ትውፊቶች ላይ ያለው እውቀት በመሳሳቱ የተነሳ መልእክተኛው ﷺ ያመጡትና ተፃራሪው እስከሚገለፅላቸው ድረስ በዚህ የተነሳ ከኢስላም ማስወጣት (ማክፈር) አይቻልም።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 1/372] [አረድ ዐለል በክሪ፡ 411]

ሸይኾችን ልክ አልፈው በማላቅ በጭንቅና በመከራ ጊዜ እርዳታ የሚጠይቁ፣ እነሱን የሚማፀኑ፣ ቀብሮቻቸውን የሚዘይሩ፣ የሚሳለሙና በአፈሩ በረከትን የሚሹ ሰዎችን በተመለከተ ዑለማኦች ምን እንደሚሉ ሲጠየቁም እንዲህ ብለው መልሰዋል፡-


الحمد لله رب العالمين من استغاث بميت أو غائب من البشر بحيث يدعوه في الشدائد والكربات ويطلب منه قضاء الحوائج فيقول: يا سيدي الشيخ فلان أنا في حسبك وجوارك أو يقول عند هجوم العدو: يا سيدي فلان يستوحيه ويستغيث به أو يقول ذلك عند مرضه وفقره وغير ذلك من حاجاته: فإن هذا ضال جاهل مشرك عاص لله تعالى باتفاق المسلمين فإنهم متفقون على أن الميت لا يدعى ولا يطلب منه شيء سواء كان نبيا أو شيخا أو غير ذلك ..وهذا الشرك إذا قامت على الإنسان الحجة فيه ولم ينته وجب قتله كقتل أمثاله من المشركين ولم يدفن في مقابر المسلمين ولم يصلَّ عليه وأما إذا كان جاهلا لم يبلغه العلم ولم يعرف حقيقة الشرك الذي قاتل عليه النبي صلى الله عليه وسلم المشركين فإنه لا يُحكم بكفره ولا سيما وقد كثر هذا الشرك في المنتسبين إلى الإسلام ومن اعتقد مثل هذا قربة وطاعة فإنه ضال باتفاق المسلمين وهو بعد قيام الحجة كافر

“ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁን። በመከራና ጭንቅ ጊዜ በመጣራት ከሞተ ወይም ከሩቅ ሰው እርዳታን የጠየቀ፣ ጉዳዮቹን እንዲፈፅምለት በመከጀል ‘ሰዪዲ ሸይኽ እከሌ ሆይ! እኔ ባንተ ጥበቃና ከለላ ስር ነኝ’ በማለት የለመነ፣ ወይም ደግሞ ጠላት በሚያጠቃ ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ ሆይ!’ በማለት የተማፀነና እርዳታን የጠየቀ፣ ወይ ደግሞ ሲታመም ወይ ሲደኸይ ወይም በሌላ ጉዳዮቹ ላይ ይህንን ያደረገ ሰው ይሄ በሙስሊሞች ኢጅማዕ ጠማማ፣ መሃይም፣ አጋሪና የላቀውን አላህ ያመፀ ነው። … ይሄ ሺርክ በአንድ ሰው ላይ ማስረጃው ከቀረበበትና ካልታቀበ ልክ የሱ አምሳያ አጋሪዎች እንደሚገደሉት ሊገደል ግድ ይላል። በሙስሊሞች መቃብርም መቀበር የለበትም። አይሰገድበትምም። እውቀት ያልደረሰው መሃይም ከሆነና ነቢዩ ﷺ አጋሪዎችን የተጋደሉበትን ሺርክ ተጨባጭ የማያውቅ ከሆነ ግን ይሄ የከሃዲነት ብይን አይወሰንበትም። በተለይ ደግሞ ይሄ ሺርክ ወደ ኢስላም የሚጠጉ ሰዎች ዘንድ በዝቷልና። እንዲህ አይነቱን መቃረቢያና አምልኮት አድርጎ ያመነበት ሰው በሙስሊሞች ስምምነት ጠማማ ነው። ማስረጃ ከቀረበበት በኋላ ከሃዲ ነው።” [ጃሚዑል መሳኢል፡ 3/145 - 151]

 ولهذا كنت أقول للجهمية من الحلولية و النفاة الذين نفوا أن الله تعالى فوق العرش لما وقعت محنتهم أنا لو وافقتكم كنت كافرا لأني أعلم أن قولكم كفر و أنتم عندي لا تكفرون لأنكم جهال وكان هذا خطابا لعلمائهم و قضاتهم و شيوخهم وأمرائهم و أصل جهلهم شبهات عقلية حصلت لرؤوسهم في قصور من معرفة المنقول الصحيح و المعقول الصريح الموافق له وكان هذا خطابنا، فلهذا لم نقابل جهله وافتراءه بالتكفير بمثله

“ለዚህም ነው አላህ ከፍጡራን ላይ ሰፍሯል ለሚሉ ጀህምያዎችና የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆኑን ለሚያስተባብሉ አራቋቾች ፈተናቸው በተከሰተ ጊዜ እንዲህ እላቸው የነበረው፡- ‘እኔ በሃሳባችሁ ብስማማ ከኢስላም እወጣለሁ። ምክንያቱም ንግግራችሁ ክህደት እንደሆነ አውቃለሁና። እናንተ ግን እኔ ዘንድ ከኢስላም አትወጡም። ምክንያቱም መሀይማን ናችሁና።” [ረድ ዐለል በክሪ፡ 253]

የኢብኑ ተይሚያ “አረድ ዐለል በክሪ” ኪታብ ለዐሊይ ብኑ የዕቁብ አልበክሪ (734 ሂ.) የተሰጠ ምላሽ ነው። በክሪ ማለት ኢብኑ ተይሚያ ከፍጡራን እርዳታ መጠየቅን በመቃወማቸው ተበሳጭቶ በሳቸው ላይ የክህደት ብይን እየሰጠ (እያከፈረ) ኪታብ የፃፈ ነው። ልብ በሉ! በክሪ ከፍጡራን እርዳታን በመጠየቅ ያምናል፡፡ ይህ ከኢስላም የሚያስወጣ ሺርክ ነው፡፡ እሱ ግን ከዚህም አልፎ ወደዚህ ሺርክ የሚጣራ ነው፡፡ እዚህም ላይ አልቆመም፡፡ ይህንን አቋሙን የሚፃረሩትን የሚያከፍር ነው። ለዚያም ነው ኢብኑ ተይሚያን እያከፈረ አንድ ኪታብ ያዘጋጀው፡፡ ኪታቡ ኢብኑ ተይሚያ እንዳሉት በሺርክ የታጨቀ ነው። ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር እሳቸው አላከፈሩትም። በግልፅ ቋንቋ እንዲህ ነበር ያሉት፡- 

 لم نقابل جهله – البكري – وافتراءه بالتكفير بمثله كما لو شهد شخص بالزور على شخص آخر، أو قذفه بالفاحشة كذبا عليه لم يكن له أن يشهد عليه بالزور ولا أن يقذفه بالفاحشة 

“የሱን ዋልጌነትና በቅጥፈት ማክፈሩን በተመሳሳይ አናስተናግድም። ልክ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ በሃሰት ቢመሰክር ወይም ደግሞ በሃሰት በብልግና ቢወነጅለው፤ እሱም በአፀፋ በሃሰት ሊመሰክርበት አለያም በብልግና ሊወነጅለው እንደማይፈቀድለት ማለት ነው።” [ረድ ዐለል በክሪ፡ 254]

እስካሁን ያቀረብኩት ሃሳብ ከጥቂት መግቢያና መሻገሪያ አረፍተ ነገሮች ውጭ እንዳለ የኢብኑ ተይሚያ ንግግር ነው፡፡ እንዳያችሁት አላዋቂ ሰው ሺርክ ላይ ቢወድቅ ከኢስላም እንደማያስወጡ ደግመው ደጋግመው ግልፅ አድርገዋል። ይህንን የኢብኑ ተይሚያን አቋም የሚያራምድ ሰው ተክፊሮች ዘንድ ከሃዲ ነው። ዛሬ ከተራው ሙስሊም ማህበረሰብ እስከ ታላላቅ ዑለማኦች ድረስ በጅምላ በማክፈር ላይ የተጠመዱት ተክፊሮች ግን በሃሰት እራሳቸውን ወደ ኢብኑ ተይሚያ እንደሚለጥፉ ይታወቅ። ከዚህ ፊትና ጋር የተነካካችሁ ሁሉ! ፀፀት በማይጠቅምበት ጊዜ ከመፀፀታችሁ በፊት ከስሜት ነፃ ሆናችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ። ይህንን የማክፈር ጥማታችሁን በጊዜ አስተንፍሱት። ቆማችሁ ተቀምጣችሁ ሁሌ ስለማክፈር ከማብሰልሰል በላይ ሰዎችን ከሺርክ ለማውጣት በማስተማር ላይ ሰፊ ጊዜ ስጡ። ከልብ የሰረፀን ተቅዋ አላህ ያድለን።


(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 09/2013)

የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
https://t.me/IbnuMunewor


አድራሻዎቻችን ይቀላቀሉ

       
 ፌስቡክ    
      



Post a Comment

0 Comments