Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቅንድብ መቀንደብና ዊግ መቀጠል

'‎ትምህርት ቁጥር 20
#ቅንድብ መቀንደብና #ዊግ መቀጠል 
የካቲት 19/6/2006 ረቢዓሳኒ 25/4/1435 
ቅንድብ መቀንደብና ዊግ መቀጠል
ቅንድብ መቀንደብና ዊግ መቀጠል ለሴት ልጅ በኢስላም የተከለከሉ ነገሮች ናቸው:: እነዚህ ነገሮች በተለይ በዘመናችን ልክ የሴትነት መገለጫ ይመስል ብዙዎቹ ሴቶች ተቌድሰውታል:: ፋሽን ተብለው የመጡ የተለያዩ ስሪቶችም ያለ ዊግ አትንኩኝ ባዮች ናቸው:: ከስሬትም ውጪ ያሉ እንደ መፈሸን የመሳሰሉ ሁሉ ያለእርሱ ደሃዎች ሆነዋል:: ሆኖም ግን መቀንደብና ዊግ መቀጠል ፍፁም ክልክል ነው፡፡ እዚህ ጋር አንዳንድ ሴቶች “አላህ ይምራቸውና” ከምራቸው ይሁን ለመቀለድ ፈልገው ባይገባኝም ቅንድባቸውን ተቀንድበው ሲያበቁ “ነጭቼው ወይም ላጭቼው አይደለም ነገር ግን በክሬም ነው ያነሳሁት” የሚሉና እንዲሁም ዊግንም “ጸጉርን ሳይሆን ክርን ነው ያደረግኩት” እያሉ እራሳቸውን የሚያሞኙ በጣም ተበራክተዋል፡፡ ይህ ተላላነት በእውነቱ ከአንዲት የነቃች አማኝ የሚጠበቅ አይደለም:: እራሷን እንዲህ በዋዛ ፈዛዛ ለእርግማንና ቅጣት ፈጽሞ አትዳርግም:: ከአቡ ዳውድና ከሌሎችም በመጣውና ከኢብኑ መስዑድ (ረድየላሁ አንሁ) በተወራው ሐዲስ እንዲህ ብለዋል :-
የአላህ መልክተኛ(ﷺ) ዊግ ቀጣያንና ተቀጣዩን ቀንዳቢዋንና ተቀንዳቢዋንም ተራግመዋል:: የአላህን ተፈጥሮ ቀያሪዎችንም::´ 

አንቺ ውዲቷ እህቴ! ታዲያ እንዴት ነው ለአላህ ሰግደሽ በሰላትሽ ውስጥም አላህን “ጌታዬ ማረኝ እዘንልኝ” እያልሽ እየለመንሽው በሌላ በኩል ደግሞ ለእርሱ ቁጣ የሚዳርግሽን ነገር ምትፈጽሚው? ንግግርሽና ተግባርሽ እየተቃረነ ነውና ከዚህ ድርጊት ፍጹም ልትታቀቢ ይገባል አላህ ያግዝሽ ፡፡

#ሊንኩን_በመጫን_ፔጁን_ላይክ(like) _ያድርጉ =====>
--------------------------------
www.facebook.com/tenbihat
--------------------------------
ኢንሻ አላህ ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ይገበዩበታል!!! 

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!
_______

የካቲት 19/6/2006 ረቢዓሳኒ 25/4/1435‎'
ትምህርት ቁጥር 20
‪#‎ቅንድብ‬ መቀንደብና ‪#‎ዊግ‬ መቀጠል
የካቲት 19/6/2006 ረቢዓሳኒ 25/4/1435
ቅንድብ መቀንደብና ዊግ መቀጠል
ቅንድብ መቀንደብና ዊግ መቀጠል ለሴት ልጅ በኢስላም የተከለከሉ ነገሮች ናቸው:: እነዚህ ነገሮች በተለይ በዘመናችን ልክ የሴትነት መገለጫ ይመስል ብዙዎቹ ሴቶች ተቌድሰውታል:: ፋሽን ተብለው የመጡ የተለያዩ ስሪቶችም ያለ ዊግ አትንኩኝ ባዮች ናቸው:: ከስሬትም ውጪ ያሉ እንደ መፈሸን የመሳሰሉ ሁሉ ያለእርሱ ደሃዎች ሆነዋል:: ሆኖም ግን መቀንደብና ዊግ መቀጠል ፍፁም ክልክል ነው፡፡ እዚህ ጋር አንዳንድ ሴቶች “አላህ ይምራቸውና” ከምራቸው ይሁን ለመቀለድ ፈልገው ባይገባኝም ቅንድባቸውን ተቀንድበው ሲያበቁ “ነጭቼው ወይም ላጭቼው አይደለም ነገር ግን በክሬም ነው ያነሳሁት” የሚሉና እንዲሁም ዊግንም “ጸጉርን ሳይሆን ክርን ነው ያደረግኩት” እያሉ እራሳቸውን የሚያሞኙ በጣም ተበራክተዋል፡፡ ይህ ተላላነት በእውነቱ ከአንዲት የነቃች አማኝ የሚጠበቅ አይደለም:: እራሷን እንዲህ በዋዛ ፈዛዛ ለእርግማንና ቅጣት ፈጽሞ አትዳርግም:: ከአቡ ዳውድና ከሌሎችም በመጣውና ከኢብኑ መስዑድ (ረድየላሁ አንሁ) በተወራው ሐዲስ እንዲህ ብለዋል :-
የአላህ መልክተኛ(ﷺ) ዊግ ቀጣያንና ተቀጣዩን ቀንዳቢዋንና ተቀንዳቢዋንም ተራግመዋል:: የአላህን ተፈጥሮ ቀያሪዎችንም::´

አንቺ ውዲቷ እህቴ! ታዲያ እንዴት ነው ለአላህ ሰግደሽ በሰላትሽ ውስጥም አላህን “ጌታዬ ማረኝ እዘንልኝ” እያልሽ እየለመንሽው በሌላ በኩል ደግሞ ለእርሱ ቁጣ የሚዳርግሽን ነገር ምትፈጽሚው? ንግግርሽና ተግባርሽ እየተቃረነ ነውና ከዚህ ድርጊት ፍጹም ልትታቀቢ ይገባል አላህ ያግዝሽ ፡፡
‪#‎ሊንኩን_በመጫን_ፔጁን_ላይክ‬(like) _ያድርጉ =====>
--------------------------------
www.facebook.com/tenbihat
--------------------------------
ኢንሻ አላህ ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ይገበዩበታል!!!
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!
_______
የካቲት 19/6/2006 ረቢዓሳኒ 25/4/1435