ዘካህ
ዘካህ ከኢስላማዊ ግዴታዎች መካከል አንዱ ግዴታ ነው። ከሁለቱ ምስክርነቶች (ሸሀደተይን) እና ሰላት በኋላ አንዱ እና ዋነኛው የኢስላም ማዕዘን (ሩክን) ነው፡፡ ዘካን ማውጣት ግዴታ ስለመሆኑ ቁርአን፣ ሐዲስ እና የአጠቃላዩ ሙስሊም ማህበረሰብ ስምምነት ያመላክታል።
ግዴታነቱን ያስተባበለ ከኢስላም በኋላ ወደ ክህደት የተመለሰ (ሙርተድ) ይሆናል። ከዚህ አቋሙ እንዲመለስ (ተውበት እንዲያደርግ) ይጠየቃል እሺ ብሎ ከተመለሰ ይተዋል እምቢ ካለ (በኢስላማዊ ህግ ስርአት በሚተዳደሩ ሀገሮች ውስጥ በህግ ፊት) በሞት ይቀጣል::
ዘካን ከመስጠት የሰሰተ ወይም መስጠት ካለበት መጠን የተወሰነውን የቀነሰ እርሱ የአላህ ቅጣት ከሚገባቸው በደለኞች መካከል ነው። አላህ(ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
وَلَا يَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَآ ءَاتَىهُمُ ٱللَّـهُ مِن فَضْلِهِۦ هُوَ خَيْرًا لَّهُم بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا۟ بِهِۦ يَوْمَ ٱلْقِيَـمَةِ وَلِلَّـهِ مِيرَثُ ٱلسَّمَـوَتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّـهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ( سورة آل عمران:180)
ትርጉሙም፦ «እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለነሱ ደግ አይምሰላቸው፤ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው፤ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሳኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ። የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው፤ አላህም በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው።» (አል-ዒምራን፡ 180)ቡኻሪ ሰሂህ በተሰኘው ኪታባቸው ከአቡ ሁረይራ(ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ ገንዘብ ሰጥቶት የእሱን ዘካህ ያላወጣ የቂያማ ቀን ገንዘቡ እንደ ሁለት አይኖቹ ላይ ጥቁር ነጥቦች የተጣሉበት ወንድ መላጣ እባብ ተመስሎ ይመጣና መንጋጭላውን አጥብቆ በመያዝ እኔ ገንዘብህ ነኝ እኔ ድልብህ ነኝ ይለዋል።» (ቡኻሪ ዘግበውታል) በዚህ ሐዲስ አገባብ መሰረት (ሹጃዕ) ማለት ወንድ እባብ ሲሆን (ዓቅረእ) የሚለው ደግሞ ከመርዛማነቱ የተነሳ የአናቱ ፀጉር የተመለጠ ማለት ነው።
አላህ(ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ብሏል፦
يَـٓأَيُّهَا
ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْأَحْبَارِ وَٱلرُّهْبَانِ
لَيَأْكُلُونَ أَمْوَلَ ٱلنَّاسِ بِٱلْبَـطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ
ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ يَكْنِزُونَ ٱلذَّهَبَ وَٱلْفِضَّةَ وَلَا
يُنفِقُونَهَا فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
﴿٣٤﴾
يَوْمَ
يُحْمَى عَلَيْهَا فِى نَارِ جَهَنَّمَ فَتُكْوَى بِهَا جِبَاهُهُمْ
وَجُنُوبُهُمْ وَظُهُورُهُمْ هَـذَا مَا كَنَزْتُمْ لِأَنفُسِكُمْ
فَذُوقُوا۟ مَا كُنتُمْ تَكْنِزُونَ
﴿٣٥
ትርጉሙም፦ «እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው። በርሷ ላይ በገሀነም ሳት ውስጥ በሚጋልባትና ግንባሮቻቸውም ጎኖቻቸውም ጀርባዎቻቸውም በርሷ በሚተኮሱ ቀን(አሳማሚ በኾነ ቅጣት አብስራቸው) ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው። ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ (ይባላሉ)» (አት-ተውባህ፡ 34-35)በሌላው ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ(ረድየላሁ ዓንሁ) ባስተላለፉት ሐዲስ ነብዩ(ሰለላሁ ዓለይሁ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «ማንኛውም የወርቅም ይሁን የብር ባለቤት በርሱ ላይ ግዴታ የሆነበትን (የገንዘቡን) ሃቅ ለሚገባው ወገን ያልሰጠ ከሆነ የቂያማ እለት እንደ ዝርግ ሰሃን ባለ ከእሳት በሆነ ብረት ጎኑ፣ግንባሩና ጀርባው ሳይቶከስ አይቀርም። በበረደም ቁጥር እንደ ገና እንዲግል እየተደረገ አላህ በባሮቹ መካከል ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ የሃምሳ ሺህ ዓመት ያህል መጠን ባለው ቀን ውስጥ (በዚህ መልኩ ይቀጣል)።
ጣሃ አህመድ
0 Comments