Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሽቶ ተቀባብተሽ ከቤትሽ አትውጪ


ሽቶ ተቀባብተሽ ከቤትሽ አትውጪ
🖱🖱🖱🖱🖱🖱🖱🖱

አቡሁረይራ አንዲት ሽቶ የተቀባባች እንስት ጋር ፊትለፊት ተገናኙና "የጀባር (የአላህ) ባርያ ሆይ ወዴት መሄድ ፈልገሽ ነው"? አሏት
"ወደ መስጂድ" አለቻቸው።
"ለሱ ነው ታዲያ ሽቶ የተቀባሽው"? አሏት
እሷም "አዎን" አለቻቸው። በዚህን ግዜ አቡሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ የአላህ መልእክተኛ ﷺ «ማንኛዋም ሴት መስጂድ ለመሄድ ብላ ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ ከወጣች ወደ ቤቷ ተመልሳ ልክ ከጀናባ እንደሚታጠቡት አይነት ከሽቶው ካልታጠበች በስተቀር አላህ ሰላቷን አይቀበላትም።» ብለዋልኮ አሏት።
[أخرجه الامام ﺃﺣﻤﺪ في مسنده].

ይህንን ታሪክ አስመልክተው የዘመናችን የሀዲስ ሊቅ ሙሀመድ ናስር አል አልባኒ ረሂመሁላህ
“ወደ መስጂድ መሄድ ለፈለገቿ ሀራም ከሆነ ወደ ግብይት ቦታዎች ወደ ጠባብ መተላለፊያዎች ሆነ ወደየጎዳናዎች ተቀባብታ ለምትወጣው እንስት ሁክሙ ምን ይሆን? ይህማ የከፋ ሀራምና ወንጀል ለመሆኑ ጥርጥር የለበትም።” በማለት ክብደቱን ገልፀዋል።
[ﻣﺨﺘﺼﺮ ﻛﺘﺎﺏ ﺟﻠﺒﺎﺏ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﺔ. 44]

ስለሆነም ውዷ እህቴ ሆይ ክብርሽን ከሚነካ፣ ኢማንሽን ከሚፈታተን፣ ዒባዳሽን ከሚያስጥል፣ ፈተናን ከሚስብብሽ ነገር ሁሉ ጠንቀቅ በይ። ይህን ሽቶ ስትቀቢ ፀዳሁ አማርኩ ሳቢ ሆንኩ ብለሽ እንደ ቀላል የተዳፈርሽው ነገር ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ ጭራሽ እንደ ጀናባ ትጥበት የሚያስፈልገው እርኩስ ነገር ሆኖብሻልና ከቤትሽ ስትወጪ ወይም እቤትሽም ሆነሽ ባእዳን ወንዶች ጋር የሚያገናኝሽ ቦታ ላይ ሽቶ ከመቀባት ራቅ በይ እልሻለሁ።
አላህ ከዚህ ፈተና ይጠብቅሽ።

°°°°°°°°°°°°°°°°°
✍Abufewzan
08/03/1438
07/12/2016
www.fb.com/tenbihat
© ተ ን ቢ ሃ ት