Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ልብ ሲታወር አደጋ ነው፡፡

ልብ ሲታወር አደጋ ነው፡፡
አንዳንድ መውሊድ አክባሪ አህባሾችና ሱፍዬች የሚከተለውን ልባቸውን የታወሩበትን ግጥም ይገጥማሉ
“ሱናቸውን ይዘን ነቢን ተከትለን፣
ያስያዙንን ይዘን ያዘዙትን ወደን፣
የከለከሉትን እኛም ተከልክለን፣
የዊላዳውን ቀን እናከብረዋለን!!”
እስቲ እነ ሸህ ደፋሩ ልባቸው ታውሮ የሚያቀነቅኑትን ስንኝ መስመር በመስመር እንየው
1) “ሱናቸውን ይዘን ነቢን ተከትለን”
የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ማለት እንግዲህ
- በቃል ያዘዙት፣
- በተግባር የሰሩት፣
- ሰሃባዎቻቸው ሲሰሩ አይተው ዝም ያሉት ነው፡፡
መውሊድ እንግዲህ በቃላቸውም አላዘዙበትም፣ በተግባራቸውም አልሰሩትም፣ እነዛ ስለስርዓት ያላቸው ሰሃባዎችም አልሰሩትም….. ታድያ እንዴት “ሱናቸው ይዘን ነቢን ተከትለን” ይላሉ?
እንዲያውም “ሱናቸውን ትተው ቢድዐን እና ሸይጧንን ተከትለው” የሚለው ነው እነሱ የሚፈፅሙትን የሚገልፀው፡፡
2) “ያስያዙንን ይዘን ያዘዙትን ወደን”
እዚህም ጋር መውሊድን ለማንም አላስያዙትም፡፡ ብሎም ያዘዙትን ወደን ካሉ እሳቸው ያዘዙት ሱናቸውን እንድንይዝ፣ ቢድዐን እንድንርቅ ነው፡፡ ይሀው እነሱ በተገላቢጦሽ ሸይጧን ጥፋታቸውን አሳምሮላቸዋል፡፡
3) “የከለከሉትን እኛም ተከልክለን”
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቢድዐ በዲን ላይ የሚደረግን ፈጠራ ራቁ ብለው አዘው እነዚህ ሰዎች አያፍሩም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ታላላቅ ከከለከሏቸው ነገሮች ውስጥ ቢድዐን ሆኖ ሳለ “የከለከሉትን እኛም ተከልክለን” ብለው ይዋሻሉ፡፡
ላይ ላዩን ቢዋሹ አላህ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) እያመፁ እሳቸውን መከተል የለም፡፡
4) “የዊላዳውን ቀን እናከብረዋለን!!”
ኩራተኛ ሰው እንዲህ ድርቅ ብሎ ሃቅን አልቀበል ብሎ የጀሀነም መንገድ የሆነውን ቢድዐ ዲን አድርጎ ይይዛል፡፡ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ግን ለ23 አመት ነብይ በነበሩበት ጊዜ አንድም ቀን አላከበሩትም፡፡ ታድያ ከዚህ በላይ ጥመት ምን አለ?
ሌላኛው ደፋራቸው ደግሞ እንዲህ ሲል ፃፈ
5) “የነቢ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?”
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እራሱ የማን ባርያ ናቸው?
መልሱም የአላህ ናቸው፡፡
ታድያ እኛን እሳቸው “የአላህ ባርያዎች ሁኑ” እያሉ እንዳላስተማሩን ዛሬ “የነቢ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?”
አንድ ሰው ተነስቶ “የኢሳ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?” ቢል ይጠየፉታል፡፡ ለኢሳ ሲሆን እኛ ለአላህ፣ ለብቸኛው ፈጣሪ ብቻ ነው አሽከር ልንሆን የሚገባን አይነት መልስ ይሰጣሉ፡፡
ታድያ አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምንም) ይሁን ኢሳን (አለይሂ ሰላም) የፈጠረ ብቸኛው አምላክ፣ ለእሱ ብቻ ባርያ ልንሆን የሚገባን ነን ሲባሉ፡፡
“ወሃብዬች” ብለው ፍየል ወድያ ቅዝምዝም ወዲህ ይሆኑብናል፡፡
አደለም እኛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን የአላህ ባርያ ናቸው፡፡ እሳቸው ያስተማሩን እሳቸውን በማወደስ ድንበር እንዳናልፍ እና ስለ እሳቸው ስንናገር “የአላህ ባርያውና መልክተኛው ነው” ብለን እንድንመሰክርልቸው ብቻ ነው ያስተማሩን፡፡ እኛም በአላህ ፍቃድ አደበኞች በመሆን ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መልክተኛውና ባርያው ናቸው እንላለን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤታቸው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡