መውሊድን አስመልክቶ ነብዩ “መቼ ከለከሉ” ለሚሉ?
እኛ ደግሞ መቼ ፈቀዱልህና? ብለን መልስ እንሰጣለን፡፡
መውሊድን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አልሰሩትም፣ አላዘዙበትም ሲባሉ “መቼ ከለከሉ” ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች የሚከተለውን መልስ እና ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡
1) ነብዩ (صلى الله عليه و سلم ) ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት እንዲህ ይላሉ
مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌ
“የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው፣ ስራው (ወደራሱ) ተመላሽ (ውድቅ) ነው፡፡”

2) አንድ ቁጥር ላይ በተጠቀሰው ሀዲስ መሰረት “መቼ አዘዙህ”? ብለን እንጠይቃለን፡፡ አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙበት፣ መልክተኛው ሰርተው ያላሳዩህን፣ ሰሃባዎች ያላስተላለፉልህን ነገር እንዴት ብለህ ነው አምልኮ ልታደርገው የምትሞክረው?
መቼም የአላህ ውድ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
- አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ፣
- የሀጅ ስርዐት አፈፃፀሙን ከእኔ ያዙ፣
- ውዱዕ አደራረጋቸው እንዴት እንደነበር ታላቁ ሰሃባ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁ) አሳይቷል...
- ሲያስነጥሰን ምን ማለት እንዳለብን፣
- ሚስቶቻችን ጋር ግብረስጋ ግንኙነት ስንፈፅም ምን ማለት እንዳለብን፣
- ጀናባችንን እንዴት ብለን ማውረድ እንዳለብን፣
- ከቤታችን ስንወጣ ምን ማለት እንዳለብን፣
- ወደ ቤታችን ስንመለስ ምን ማለት እንዳለብን፣
- መስጂድ ስንገባ ምን ማለት እንዳለብን፣
- ከመስጊድ ስንወጣ ምን ማለት እንዳለብን፣
- መጓጓዣ ላይ ስንወጣ ምን ማለት እንዳለብን፤
- ስናገባ ምን እንደሚባል፣
- ስንሞት ምን እንደሚባል፣
- ቀብር ውስጥ ስንገባ ምን እንደሚባል፣
- አረ ምን አለፋህ ከእናታችን ሆድ ወጥተን አፈር እስክንገባ ምን ማለት፣ ምን መስራት፣ ምን ማመን እንዳለብን የአላህ ውድ ባርያ አሳይተው፣ ተናግረው፣ ተግብረው ሲያበቁ ዛሬ እሳቸው ያላዘዙትን አትስራ ትጠፋለፍ፣ ሸይጧን አይጫወትብህ፣ ነፍስህን አታምልክ ቢድዐን ራቅ ሲባል

“መቼ ከለከሉ” ብሎ ድርቅ ሲል
“መቼ አዘዙህ”፣ “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው፣ ስራው (ወደራሱ) ተመላሽ (ውድቅ) ነው፡፡” ብለዋል ውዱ ነብይ ብለን ይግባኝ የሌለው ፍርድ ብይን በማስረጃነት በማምጣት ድባቅ መታናቸው፡፡ ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለዚህ ውድ ሃቅ ለመራን፡፡ እሱ ባይመራን ኖሮ ከጠማሞች እንሆን ነበር፡፡
3) ሊታወቅ የሚገባው ዙሁርን 4 ረከዓ ስንሰግድ፣ መንገድ ላይ ደግሞ ወደ 2 ስናሳጥር መልክተኛው ሰርተው ስላሳዩን እንጂ እኛ ከራሳችን ተነስተን የተገበርነው አይደለም፡፡ አንድ ሞገደኛ ተነስቶ ለምሳሌ ዙሁርን 6 እናድርገው ቢል፣ ማን አዘዘህና የታዘዘው 4 ለተቀማጭ 2 ለመንገደኛ ብንለው፣ ያ ሞገደኛም “መቼ ከለከሉ” ቢል መልስ ይሆነዋልን?
ይህ ነው ማስረጃን ትቶ ስሜትን የመከተል ውጤቱ፡፡ አላህ ከሸይጧን እና ነፍሳችን ተንኮል ይጠብቀን፡፡

4) አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ተከተሉ እንጂ ያላዘዛችሁን ስሩ አላለንም፡፡ አላህን እወዳለሁ ያለ እሳቸውን መከተል ግድ ይለዋል፡፡ እሳቸውን የተከተለ ደግሞ አላህም ይወደዋል፣ አላህ ወንጀሉን ይምረዋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- “አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤
አላህ ይወዳችኋልና፡፡
ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡”

አላህና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙትን ሰርቶ የአላህ ውዴታ ሳይሆን ቁጣውን፣ ምህረቱን ሳይሆን ቅጣቱን፣ ድል ሳይሆን ውርደት ነው ውጤቱ፡፡
ማጠቃለያ
አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! ለሆዳቸው ያደሩ፣ የንፁሀንን ገንዘብ በሃይማኖት ስም ዘራፊዎች የሚያመጡጥ ብዥታ አያታልህ፡፡ ሰሃባዎች፣ ሰለፎች እና እነሱን በመልካም የሚከተሉ ኡለሞች የቆሙበት ቦታ ቁም፡፡ አላህና መልክተኛውን የታዘዘ በአላህ ፍቃድ ጀነት ይገባል፡፡ እነሱን ያመፀ አላህ እሳት ያስገባዋል፡፡
አላህ በሱና ላይ ይሰብስበን፡፡