ሃላፊነት ያስጠይቃል
•••••°°°!❓!°°°•••••
ـ من الذي يَخُشَىٰ أن تُحَرم عَلَيهم
رَائِحةُ الجَنَّة !؟
ለእነማን ነው የጀነት ሽታ ይነፈጋል
ተብሎ የሚፈራው?
አንድ ሰው የጀነትን ሽታ እንኳን አያገኛትም ተብሎ ሲገለፅ ለዚያ ያበቃው ጉዳይን ክብደትና የጀነትን ሽታ ማጣት ማለት እንኳን ጀነት ሊገባ በአቅራቢያዋም ዝር አይልም የሚል የቅጣት መልእክት መሆኑን እንረዳለን።
መዕቂል ቢን የሳር አል ሙዘኒይ ረዲየላሁ ዐንሁ ከአላህ መልእክተኛﷺ ሰማሁ ብሎ እንዳስተላለፈልን፤ ነቢዩ ﷺ
"مَا مِنْ عَبْدٍ يَسْتَرْعِيهِ اللَّهُ رَعِيَّةً يَمُوتُ يَوْمَ يَمُوتُ وَهُوَ غَاشٌّ لِرَعِيَّتِهِ إِلا حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ"
“ ሃላፊ የሚሆንባቸውን ሰዎች በጥላው ስር አላህ ያደረገለት ማንኛውም ባርያ (ግለሰብ) በሞተበት እለት የሚያስተዳድራቸውን እንዳታለለ ሆኖ ከሞተ አላህ በሱ ላይ ጀነትን ሃራም ያደርግበታል። ” ብለዋል። (ቡኻሪና በ7151 ሙስሊም በ142 ላይ አስፍረዋል)
ይህንኑ መነሻ በማድረግ አል አልላማ ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት በአንዲት ምሽት ለሀገሪቱ መሪ መመርያ ይሆነው ዘንድ ስለ ኢስላማዊ መንግስት አስተዳደር በሚያስገርም መልኩ የደረሱትን የ"ሸሪዓዊ ሲያሳ" ኪታብን ሲያብራሩ በ1/35 ላይ እንደሰፈረው ባለስልጣናትን እንዲሁም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎችን፣ ባሎችን፣ አባቶችን በተመለከተ አስጊ ነገር እንዳለ ገልፀዋል።
« الرَجُـلُ فِـي بَيتِـهِ إذَا مـَات وهُـوَ غـَاشٌ لأهلِـهِ
⇐فـَإنَّ اللَّـه يُحـَرِمُ عَلَيـهِ رَائِحَـةُ الجَنَّـة، والذِيـنَ يَدَعـُونَ عِنـدَ أهلِيهـم آلاتِ الَلهـوِ المُفسـِدة للأخـلاقِ المُدَمـِرَةِ للعَقَائِـد هَـؤلاءِ لا شـَكَ أنَّهُـم غَاشـُون لأهلِهِـم، فـَإذا مَاتُـوا عَلَـى هَـذِهِ الحـَال - والعِيَـاذُ باللَّـهِ - فَيَخُشَـىٰ أن تُحَـرم عَلَيهـم رَائِحـةُ الجَنـَّة، نَسألُ الله العَافِيةَ والسَلامة ».
أو كما قَـالـَ العلامةَ ابنُ عُثَيمِين - رَحِمَهُ اللَّه -
في [ التعَلِيق عَلى السِيَاسَة الشَرعِية (١ /٣٥) ]
«በቤቱ ቤተሰቡን አታላይ ሆኖ ሳለ የሞተን ሰው አላህ የጀነትን ሽታ ሀራም ያደርግበታል። እነዚያ ያንን ስነ ምግባርን አጥፊና ዐቂዳን አውዳሚ የሆነውን የሙዚቃ መሳርያ ቤተሰቦቻቸው ዘንድ የተዉላቸው፤ ቤተሰቦቻቸውን አታላይ ለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለበትም። በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነው ከሞቱ አላህ ይጠብቀንና የጀነት ሽታ በነሱ ላይ ሀራም እንዳይሆን ይፈርራል። አላህ ጤንነትና ሰላምን ይለግሰን ዘንድ እንለምነዋለን።»
በማለት በተለይ ልጆቼ ይጫወቱ፣ ይዝናኑ፣ እንደነ እገሌ ልጆች ይሁኑ እያሉ ቤታቸውን ልቅ ለሚያደርጉና ለስነ ምግባራቸውም ሆነ ለእምነታቸው ጠንቅ የሆነን ነገር እቤት ድረስ እስከማምጣት ደርሰው የሚያመቻቹላቸውን የቤተሰብ መሪዎች በማስጠንቀቅ የሃላፊነት ጣጣ ከባድ እንደሆነ ገልፀዋል።
ስለዚህ ልቦናው ሆነ አእምሮው ጤናማ የሆነ፣ ከብዥታም ሆነ ከስሜታዊነት ርቆ ሰላምን ያገኘ የቤተሰብ መሪ የነገዋን ዘላቂ ሃያቱን አይዘነጋም። ለርካሽ ነገርም አይሸጣትም። ለትዳር አጋሩ፣ ለአብራኩ ክፋዮችና በጥላው ስር ላሉት ቤተሰቦቹ ያቅሙን ያህል መልካም መሪ ይሆናል።
ለአካላቸው፣ ለአእምሯቸውና ለመንፈሳቸው የሚፈይዳቸውን ያመቻችላቸዋል። ያቀርብላቸዋል። በትክክል ለመጠቀማቸውም ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል። የሚያፈነግጥ ሆነ መስመር የሚስት ወይም ውጫዊ ተፅዕኖ ያገኘው የቤተሰቡ አባል ካለ በአፋጣኝ የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል። በዚህ አይነት በፍቅርና በርህራሄ ይንከባከባቸዋል። ሚስትም፣ እናትም ልክ እንደዚሁ ሃላፊነት አለባት።
የሃላፊነትና የተጠያቂነት ጉዳይ እንደየደረጃው በተዋረድ ሁሉንም የሚመለከት ጉዳይ ለመሆኑም ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ አንሁማ ባወሩልን ሀዲስ ነቢዩﷺ
" أَلا كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ فَالْأَمِيرُ الَّذِي عَلَى النَّاسِ رَاعٍ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ وَالرَّجُلُ رَاعٍ عَلَى أَهْلِ بَيْتِهِ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْهُمْ وَالْمَرْأَةُ رَاعِيَةٌ عَلَى بَيْتِ بَعْلِهَا وَوَلَدِهِ وَهِيَ مَسْئُولَةٌ عَنْهُمْ وَالْعَبْدُ رَاعٍ عَلَى مَالِ سَيِّدِهِ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْهُ أَلا فَكُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ " رواه البخاري ( 7138 ) ومسلم ( 1829 ) .
“ ንቁ! ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ። በምትጠብቁትም ሁላችሁም ተጠያቂዎች ናችሁ። በሰዎች ላይ አስተዳዳሪ የሆነ ሰው በሚያስተዳድራቸው ላይ ተጠያቂ ነው። አባወራው በቤተሰቦቹ ላይ ሃላፊ ነውና ስለነሱ ተጠያቂ ነው። ሚስትም በባሏ ቤትና በልጆቹ ላይ ሃላፊ ናት። ስለነሱም ተጠያቂ ናት። አገልጋዩም በአለቃው ንብረት ላይ ጠባቂ ነውና በንብረቱ ይጠየቅበታል። ንቁ ! ሁላችሁም ሃላፊዎች ናችሁ። ሁላችሁም በሃላፊነታችሁ ተጠያቂዎች ናችሁ።" በማለት እያንዳንዱ ሰው በሃላፊነቱ እንደሚጠየቅበት ገልፀዋል። (ቡኻሪ 7138 እና ሙስሊም 1829 ዘግበውታል)
ስለዚህ ቀድሞም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ “ እናንተ ሰዎች ሆይ! ራሳችሁን ሆነ ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ።” በማለት አስጠንቅቆናልና ራሳችንንም ቤተሰቦቻችንንም ከጥፋት እንታደግ። አንድ ሰው የጀነትን ሽታ አጣ ማለት ጭራሽ ወደ ጀነት ሰፈር አይቀርብም ነውና ቤተሰቦቻችንን የጠቀምን፣ የወደድን መስሎን ወደሚጎዳቸው ከመራናቸው እያታለልናቸው ነውና ለስነ ምግባራቸውም ሆነ ለኢማናቸውን ጠንቅ የሆነን ነገር ከማመቻቸት እንቆጠብ ዘንድ አላህ ያግዘን። እነሱንም አላህ ያቅናልን።
~~~~~~~~~
✍🏽Abufewzan
06/03/1438
04/12/2016
www.fb.com/tenbihat
© ተ ን ቢ ሃ ት