አሰላሙ ዐለይኩም
ይዘጋጁ ከፊት ፍተሻ (ኬላ) አለ




ዓላማ ለማሳካት ሌት ከቀን ደፋ ቀና የሚል ነው


ስናውቅ ከምንጠነቀቀውና ከምንዘጋጀው በላይ አሏህ ዘንድ ለሚጠብቀን ፍተሻና ምርመራ እንዘጋጅ !



በዘመናችን ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች ዘንድ የአላህ ፍራቻ (ከልባቸው) እየጠፋ ነው።
ሁሉን አዋቂ ከሆነው ጌታቸው ይልቅም ልክ እንደራሳቸው ደካማ የሆኑ ፍጡሮችንና ድህነትን መፍራት መለያቸው ሆኗል።

በገሃድ አላህን የሚፈሩ የሚመስሉና በምላሳቸውም አላህን እፈራለሁ ከማለት አልፈው ሌሎችን ጌታቸውን እንዲፈሩ የሚመክሩ ከመሆናቸው ጋር ጌታውን ከሚፈራ ሰው በፍፁም የማይጠበቅን ስራ የሚሰሩ ሰዎች በዝተዋል ዲኑን
እያሰደቡ መጥፎ ተምሳሌት ሆነዋል

🗯 አላህ ይታገሳል እንጂ፣ አይረሳም! የምናደርገውን ሁልም ጠንቅቆ ያውቃል!
✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም