Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምንድን ነው መውሊድ አደጋ ነው ብለን የምንጫጫው?

ለምንድን ነው መውሊድ አደጋ ነው ብለን የምንጫጫው?
መውሊድ የሽርክ መናሃርያ ስለሆነ ነው::
ይህን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን መውሊድ ላይ የሚባሉ የሽርክና ቢድዓ ስንኞች እስቲ ልብ በሉ፣ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ
1. በዝቶብኛልና አያሌ ነገር
አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር
ቀሌቤን ወዳሳቸው አድርጌ ሰንዘር
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር
ከሙስጠፋ ይዤ እስከ አቡል በሸር
አምቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር
2. በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር
ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም ያለናንተ ሁለም አያምር
በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር
ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር፡፡
3. አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ገፋር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር
ሊለግስ ነው መሰሌ ዳመናው ዟዟረ
የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ፡፡
4. ሁለም ባንድ ሆነው ከሙስጠፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር
5. አንተል ቁረይሺዩ አንተ ነብዩና
ቢሲሪ ሲሪከ ዘይን ባጢነና
6. የቦረናው ደግዬ
እርዱኝ አባብዬ
7. ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር
በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር
ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኝል ነውር
እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር
መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር
አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር
በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር
አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፡፡
ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር
8. የአበራ ሙዝ አባት የማይደፈር
አቤት ይታይልኝ ምነው የኔም ዱር
ዙሩልኝ ጌቶቼ በአውን በነስር
ከጃችሁ ከጅዬ ቆሜያለሁ ከበር፡፡
በናንተ የሸሸ ምን ጊዜም አያፍር
ሀጃዬን አውጡልኝ በዟሂር በሲር
9. ሺሊላህ ያሰይድ አብዱል ቃድር
እርዳታው አይውል አያድር
10. ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ
ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፡፡
እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር
ይላል እንዘይር ቀልቡን ሳያጠራ
የማያውቁ መስሎት የቀልቡን የሰድሩን
11. መጀን በኑር ሁሴን በአሩሲው ኑር
የአውሉያዎቹ ሻምበል የበርም የባህር
ከራማው ይፋ ነው አይደለም መስቱር
እጣው እንደ ነቢይ በርዳዳው ገበር፡፡
የሪጀልች አባት የነዚያ ያብራር
የነአህመድ ኑረላህ ዚልፈይዲል ሚድራር
ተብል አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር
ጌታዬ ኑር ሁሴን በለኝ እንጂ አጀብ
በለኝ የኔ አሽከር በዱንያ በአኸይራም እንዳልቸገር
በናንተ የሸሸ እንዲሁም አይቀር
አላህ ሰጥቷቸኋል ሳይሰፍር ሳይቆጥር፡፡
12. ጌታችን ቃዲር እኩሉንም አለው አብሽር አጋፍር
አልብስም አጉርስም አመኩስ አክብር
ኢንስም ጂን ቢሆን በጫማህ ይደር
ይፍራህም ይወቅህ አውሪ እንኳ በዱር
አውቆና ለጥቆ ሰልቶ ባንተ አምር
ለኸልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፡፡
የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር
ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር
ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር
13. የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር
ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር
ተምኪን የተሰጠው ዞሂር ወባጢን
እኔ ያለሁበት እክጀላ በር
ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር
ስንቱን አሳደገው ገና በነዝር
ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ የአጀብ ነበር
እንኳን ሰው መላኢካ ያዳምጠው ነበር፡፡
14. ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር
ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር
ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ
አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር
ቢያለብስም ቢገፋም ቢያደኸይ ቢያከብር
ይግባኝ የለበትም በፈረደው አምር
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር
15. ጌታው ሸረፈዲን የደግየው ኑር
አላህ ትላቅ እጣ አድሎት ነበር
ሰውም ጂንም ቢሆን አውሬውም የዱር
ሁለም አቤት ብሎ ተገዝቶ ነበር
ጥላው የሚበቃው በሁለት አገር
በሱ ይወሰላል እስላምም ካፊር
ሴትም ወንድ ቢሆን
አብድ ቢሆንም ሁር
በሱ ተወስል የለውም ችጋር
16. ይመነጥቁታሌ ያወጡታሌ ከጭንቅ
17. እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው
እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው
አመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፡፡
እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው
ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፡፡
አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ
በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ
ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር
18. ደግሞ ጌታ ሰይድ የማይባሩ ኑሩ
ረህመት አድርጎ አላህ አዝልቆት ነበረ
ለኸልቁ ነበረ በልግና መህር
ሰውም ጂንም መላኢካም ተገዝቶ ነበር
19. አልዩ ሀይደር ነበረ
ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር
ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር፡፡
20. ሙሀመዱ ሰማን
ገፍታሪው ቀደር
21. ሸህ ሙሳ ሰገራት ውስጡ ላዩ ኑር
የከሽፋን መነጥር ታድል ነበር፡፡
22. ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ የርጎየው ገበር
ሲሞድህ ሙስጠፋን እያየ ነበር፡፡
23. ሰይድ ቡሽራ ገታ ቀምጣላው ገበር
ከልካይ የለበትም ሲዘልቅኝ እልፍኝ በር
ጨወታው ነበር ቀዷ ቀደር ጋር
ከሙስጠፋ ጋራ የሚነጋር
ማሂሩ ወጌሻ ለዟሂር ለሲር
ስንቱ በሽተኛ ዛቱን አይቶ ሻረ
ሰውም ጂንም ለሱ ታጠቀ ገበረ
ከራማ በበጠልሻ ነዳፊ ነበረ
ሙቶም በሀያቱ ጠቃሚ ገበር፡፡
24. መጂት ሀጅ ቡሽራ የራቀው ገበር
አገላባጭ ነበር የቀዷ ደብተር
ለውሀል መህፉዝ አይቶ ነበር ሲናገር፡፡
25. እነሀጅ አረቦ የሳልመኔው ኑር
ሀለዋውን ያደረገው ከነብዩ ጋር
26. ሸህ መሀመድ ፈቂህ ባለመነጽር
የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር
27. ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር
ሲፈቱ መለኪያ ዛቱ በበሽር
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሽር ወአንዙር
ጎራ የማይጋርደው ይዟል መነጸር
ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር
ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ኸጢር
28. እንደ ሁሴን ጂብሪል ደግሞ ማን ነበረ
የከሽፉን መነጸር አይኑ ላይ ነበር
የፊቱን የኋላን ይናገር ነበር
ሁለም ተገላልጦ ይታየው ነበር፡፡
29. እነ ሸህ ሀቢቡ ጉደኛው ገበር
ከአርሽ እስከ ሰራ ይታየው ነበር
አላህ እድርጎት ነበር የሚስጥር ሰፈር
30. ቁንዲ ሸህ አብደላ ወልዩ ገበር
ከአላህ ጋር የፈጀው ሚስጥሩን በሲር
ይናገረው ነበር አሟቱ በቀብር
31. አላሁ መሰሊ አላ ሙሀመዴ
መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ
32. የቃጥባሪው ጌታ ኢሳ የአላህ ኑር
ከሚን ኢንደላሂ የተባለ አብሽር
33. ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር
እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር
ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር
34. ጌታው አባ ረህማ የአውልያ መምህር
ጨዋታው ነበረ ሰይድ ከድር ጋር
ሁሉም ከሀድራው ይቀስም ነበር፡፡
35. ኢስማኢል ጀበርቲ ጉድ ያለው ነበር
ከራማው እንደ ባህር የሞላው ገበር
ሰውንም ጂንም ጨልጦ የሚያስቀር
እሱነው ይባላል የቃማቴ ሲር
36. እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት
እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት
37. ሰለላሁ አለይከ፤
ነቢ አለኝታዬ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ባለ ውለታዬ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ሳሎኔ ጋዳዬ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
እጣዬ ፋንታዬ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
የሚሰትሩ (የሚደብቁ) የኔን ገመና፡፡››ይላል፡፡
38. ሰለላሁ አለይከ፤
አንቱን የሚጠራ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
እሱ ልቡ ጠራ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
የለበት መከራ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
አኸይራ ሲጠራ፤››ይላል
39. ሰለላሁ አለይከ፤
የእኔ ፍላጎት፤
ሰለላሁ አለይከ፤
አይደለም ጀነት፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ቢያሳየኝ ሙሚት፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ያንቱን ፊት ማየት፤
ሰለላሁ አለይከ፤
አንቱ ኖት ለኔ የጀነት ጀና›› ይላል፡፡
40. ሰለላሁ አለይከ፤
እንዳንቱ የሚሆነኝ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
መቼም አላገኝ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ዘይኔ ቅረቡኝ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ጣል አታድርጉኝ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ካንቱማ እርቄ አልችልም እና፤
ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
41. ሰለላሁ አለይከ፤
ካንቱ ጋር የዋለ፤
ምንኛ ታደለ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
ነቢ ነቢ እያለ፤
ጭንቀቱ ቀለለ፤
ሰለላሁ አለይከ፤
እኔም ልጥራዎት ጨንቆኛል እና፤
ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
42. መሻር ባንቱ ነው ያደዋኡና፤
ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
43. የጀሊል ባለሟል የሆኑት ሃቀኛ፤
ምነው ብታሽረው ያንን በሽተኛ፤
ሙሃባው ተነጥቆ የሆነ ደመኛ፤
ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ›› ይላል፡፡
44. ‹‹ያ ረሱለላህ አል መደድ››
ብለው ይጠራሉ፡፡
45. ‹‹ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ
ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ
መዲና ና ይበሉኝ››
46. ‹‹አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ፤
ማነው ያፈረው ያነቢ ብሎ››
47. ‹‹አንቱን ጠርቼ ምን አጥቼ፤
ልሙት ፈንድቼ ልዬትና፤
አህመድ ሙሽራ የመዲና››
48. ‹‹የፍቅር ነጋሪ ዝም ብዬ ልምጣ፤
ባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፤
ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)››
49. ‹‹አገር የጀበል፤ ግዜው የጀበል፤
ደውላው የጀበል፤
እባክህ ጀበል በል፤
በፍቅሩ ታጠብ ጠጣ ወተቱ››
50. ‹‹ጥንትም እሱ ነው፤
አሁንም እሱ፤
ዛሬም ወደፊት እሱ ነው እሱ፤
ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ››
51. ‹‹እባኮት ሙሂዬ፤
ሁኑልኝ ሸፈአዬ››
52. ‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ››፤
‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ››፤
‹‹ግቡልን የተንቢ››፤
‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ››
53. ‹‹ሰላሜ አላ ገውሰል ኢባዲ፤
ዳኢመን ቢላ አደዲ››፡፡
ይላል መንዙማው
54. ‹‹አንተ የጠይባው ነጋዴ፤
ሰላም በልልኝ አህመዴን፤
አንቱ የጅብሪል ጋደኛ
አትርሱን ቀብር ስንተኛ››
55. ‹‹አለሁልህ በሉኝ፤
ዘይኔ አይራቁኝ፤
ምግብ ውሃ አይለኝ፤
አንቱን ካገኘ ሁዴ፤
ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
56. ‹‹ነቢ አንቱን እያለ፤
ቀልቤ ጥሎኝ ዋለለ፤
ወዳሉበት ደወለ፤
ሄሎ በሉት አህመዴ›› ይላል
57. ‹‹ቀልቤ እኮ አንቱ ጋር ነው፤
ፍላጎቱ ረውዳ ነው፤
ዘይኔ ና በሉት ፈጥነው፤
የቀረውን ጀሰዴን›› ይላል
58. ‹‹በሙስጠፋ እጅ ነው፤
የጀነት ቁልፍ ያለው፤
አላህ ነው ያስረከበው፤
ለዚ እኮ ነው መውደዴ›› ይላል
59. ‹‹አንቱ ኖት ረሃቤ ጥሜ፤
ልንገሮት አስቀድሜ፤
ያላንቱ አይሞቅም ደሜ፤
ግቡልኝ በጀሰዴ›› ይላል
60. ‹‹ና በሉት ኸይረል ወራ፤
ሳልሞት ሳልሄድ አኸይራ፤
ያቺን ረውዳ ዚያራ፤
የጀነትዋን አርዴ›› ይላል
61. ‹‹የሰለዋት አንበሳ፤
እንዳይመስልህ ኮሳሳ፤
ጀሰዱማ ቢከሳ፤
አለው ካሳ ከአህመዴ፤
ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
62. ‹‹ካልመጣሁኝ መዲና፤
እኔስ የለኝም ጤና፤
እንድሆንሎት ደህና፤
ቶሎ ጥሩኝ አህመዴ፤
ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
63. ‹‹ያረሱለላሂ ሸፈዐ ይሁኑና
የቢላል እኮ ነን በዲኑ የፀና››ይላል
64. ‹‹ዘይኔ ይበቃናል ኑ በሉን መዲና
ሀይ እንድናደርገው ሁሌ የርሶን ሱና›› ይላል
65. ‹‹ሰብርም የለኝም አለሁኝ ታምሜ
መንገዱ ጠፍቶብኝ አልቻለም አቅሜ
ጉልበቴ ብርታቴም ባንቱ ነው መቆሜ›› ይላል
66. ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ
ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ
67. አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
መገን ነቢ (በጣም ይገርማሉ ነቢ)የሁሉ ቀላቢ
68. ለካም አንቱ ነሁ ያነቢ
ለመላው ኸልቅ ቀላቢ
ብትን ያለውን ሰብሳቢ
በሶፋ ቡራቅ ጋላቢ
69. ያሙሀመዲ ያሀቢቢ
ያሙሀመዱ ኩን ጠቢቢ (ዶክተሪ ሁኑ)
ወአጂርኒ ሚን ለሂዲ(ከእሳት ጠብቁኝ)
ኢነ አውዛሪ ሲቃል(ወንጀሌ ከባድ ነው)
70. ‹‹ጀማሉል አለም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
ወደ ጀይላኔ ቢወረውረው
ለውሀል መህፉዝን አስመረመረው
በአለም ተሹሞ ብዙ ጉድ እያስወገዱ
በባግዳድ ምድር ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
እሳት ነው ፍቅር››
71. ‹‹ሺሊላህ ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን
ሙሃመድ ነው ዋናው
እስቲ ላነሳሳው የኔ አቡል ጀበል (ሰልማን የሸይኽ ኢሳ ቃጥባሬ ልጅ)
ፍቅሩ በልቤ ውስጥ እንደ እሳት ይቃጠል
ጠበሉን ገብቼ ታጥቤ ልወልወል
የቀረውን ትቼ የእርሱን ቃል ልከተል››
72. ‹‹የፍቅርህን ጥም አይበርድም በውሃ
አንተን የወደደ አይባልም ደሃ
ትረዳ የለም ወይ ከየትስ በረሃ
ሊጋባ ነህ አሉ ያረሱል ያጣሃ››
73. ‹‹ቁጥርም የለውም የከራማዉ አይነት
ይጎበኛል አሉ ልጆቹን በእውቀት
ብርቱ ነው መሳሪያው ጠላትን ለማጥፋት
ርህራሄው በዛና ቻለ እስከዚህ ወቅት››
74. ‹‹ሳዳቴ አደራ አሁን ለምነናል
ሁላችን በጅምላ አድሉን ብለናል
ዱስቱር ዱስቱር ብለን እዛው አፍጠናል
አትጨክኑብን እርሶን ለምነናል
ይሀው ደውለናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን
ይሀው ለምነናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን››
75. ‹‹ግቡልን በማለት ጠራ መሀይሙ
አንተን በመውደዱ ሄደለት ህመሙ
ልቡ ተሸበረ እንዳየህ በህልሙ
አንተ ነህ ፀሎቱ ስግደትና ፆሙ
መወትወት ጀመረ ቢፈላበት ደሙ››
76. ‹‹ወጣቶች ዘፈኑ በስልት እያዜሙ
እያሉ ይጠሩሃል ሺሊላህ ኢማሙ
ይመጀኑብሃል ቂምሃ እየቃሙ
ማስደሰት አለብህ በኋላ እንዳያሙህ
ባንተ እኮ አያምርም ስትል ዝም ዝም ግቡልን…››
77. ‹‹ሺሊላህ ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን
መተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹ
በወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹ
የረሱል መስለኔ አላጋውን ወራሹ
የልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ››
78. ‹‹የልቅናው እሞ አሁን ልፈስረው፤
የአላህ ሹም እኮ ነው፤
ሸልሞ የፈጠረው፤
በፊት የሰራው ጉድ አሁን ልናገረው፤
የአደም ጭቃ ነው እጁን ያጠቆረው፤
ነበር ያሳመረ ሌሎች ሲያቦኩ፤
አቡል ጀበል ግርማ አለው ለመልኩ››
79. ‹‹ገውሱን (የቃጥባሪ ሸይኽ) ተድራ
ገውስ ወልዳ (አቦል ጀበል) ነገሰች፤
ኑሩን በኑሩ ላይ ደራርባ ለበሰች››
80. ‹‹ሰላም አለይኩም ነቢ ያሰይደል አለሚን
እያዩ መባዘኔ ምነው ጨከኑ በእኔ››
81. ‹‹አብድ ብሎ እስኪሉ ቃድር
እርዳቸው አይውል አያድር››
82. ‹‹የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትንሹን ጠቃሚ ትልቅ አሳዳጊ››
83. ‹‹ይጣራል ይጮሃል የናንተው ለፍላፊ፣
የሊበኖቹ ልጅ ሙሀመድ ሻፊ (እራሱን እያስተዋወቀ መሆኑ ነው)
በዱንያም በአኸይራም ሁኑልን ደጋፊ››
84. ‹‹ያረሱለላሂ መደድ ያረሱለላህ (እርዱን ማለት ነው)፣
85. ..ይሁንቦት በነሰይድ ዳና፣
መደሻችን (መደሰቻችን)
ይሁን ያለንበት ዘመን፣
ቆሞ ቀር ሆነናል ባለንበት ዘመን፣
እኩሉን ሞሽሩን እንዳንቀር ተርበን›› ይላል
86. “ሱናቸውን ይዘን ነቢን ተከትለን፣
ያስያዙንን ይዘን ያዘዙትን ወደን፣
የከለከሉትን እኛም ተከልክለን፣
የዊላዳውን ቀን እናከብረዋለን!!”
87. “የነቢ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?”
88. አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
መህቡቢላሂ (የአላህ ውድ)
ጃሚኢ ሲፋቱላሂ (የአላህን ባህሬ ጠቅልለው የያዙ)
አላህ ግን ስለራሱና ከእርሱ ውጭ ስለሚለመኑት እንዲህ ይላል
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ ۚ وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ
ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡
إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا۟ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا۟ مَا ٱسْتَجَابُوا۟ لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ‹‹ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ ሰው የእሳት ነው፡፡›› ብለዋል
በጣም የሚያሳዝነው ይህን ሁሉ ሽርክ ያቀፈውን ቢድዐ ‹‹ፕሊስ አታንሱት፣ አንድ ነን፣ መውሊድ አይለያየንም፣ መውሊ አቂዳ አይደለም መውሊድ ቅርንጫፍ ነው፣ እና የመሳሰለውን›› እያሉ ኡማውን ጥመት ላይ እንዲተኛ የሚያደርጉት የስሜት ተጣሪዎች አሉ፡፡
ይህን ሽርክ ያለበትን የቢድዐ ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች ሃቅን ተረድተው መመለስ ሲጀምሩ እነዚህ እንቅፋቶች መሃል መንገድ ላይ ተቀምጠው ‹‹መውሊድ አይለያይም›› እያሏቸው መልሰው እንዲያፈገፍጉና ባሉበት ሽርክ ላይ እንዲጨማለቁ ያደርጓቸዋል፡፡ አላህ ዲን አጥፊዎችን ሁሉ ይምራቸው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አላህና መልክተኛው (ሰላለሁ አለይሂ ወሰለም) አለማዘዛቸው፣ ቢድዐ ብቻ መሆኑ ሳይሆን ይሀው ዱንያ አኸይራ የሚያጠፋ ሽርክ አቅፎ ይዟል፡፡ ይህንን ጉዳይ ደግሞ አያገባንም ማለት ይከብደናል፡፡ የሙስሊሞች ጉዳይ ማሳሰብ ማለትም እነሱን ከሽርክና ቢድዐ ማስጠንቀቅን ከምንም በፊት ይይዛል፡፡ አላህ የሱን ፊት ብቻ ፈልገው ከሚሰቱት ያድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡