Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትኩረት የነፈግነው የልባችን ህመም

ትኩረት የነፈግነው የልባችን ህመም
~~~~~~~~
አላህ በባዶ አይን የማይታዩ ደቃቅ የቫይረስ ሰራዊት ልኮ አለምን ሲያርበደብደው እያየን ነው። በሃገራችንም ምንም እንኳን አብዛኛው ሰው በቂ ጥንቃቄ ባያደርግም በፍርሃት ነፍሱ ልትወጣ የደረሰው ብዙ ነው። ይሄ ሁሉ ሞትን መፍራት ያመጣው ጣጣ ነው። 
ነገር ግን ስንቶቻችን እኮ ልባችን ሞቷል። ወይም በጠና ታሟል። ነገር ግን የልባችን ህመምና ሞት እያስጨነቀን አይደለም። አዎ በርካታ ልቦችን የሚያጠቁ በሽታዎች ከኮሮና በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጩ ቢሆንም እኛ ግን ደራርበን ተኝተናል። 

* የሹቡሃት ወረርሺኝ ስንቶችን ሺርካሺርክ እና ቢድዐዎች ላይ እየጣለ ነው?!
* የሸሀዋት (የዝንባሌዎች) ወረርሺኝ ስንትና ስንቱን ብልግና፣ አመፅና በደል ላይ እየጣለው ነው?!
* ልጓም አልባ የዱንያ ፍቅር ስንቱን ሰው ወለድ ላይ፣ በንግድ ማጭበርበር፣ ያልተገባ ትርፍ ማለም፣ የሰውን ሐቅ መብላት ላይ እየጣለው ነው?!

ልቦቻችን በነዚህ በሽታዎች ክፉኛ ቢጠቁም ግና ፈቃጅ አጥተዋል። ኢብኑል ቀዪ፞ም ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:–

"የልብ በሽታዎች ከአካል በሽታዎች ይበልጥ ከባድ ናቸው። ምክንያቱም የአካላዊ በሽታ ፍፃሜ ህመምተኛውን ወደ ሞት ማድረስ ነው።  
የልብ ህመም ግን ህመምተኛውን ወደ ዘላለማዊ እድለ–ቢስነት ነው የሚያደርሰው። ለዚህ ህመም በእውቀት ካልሆነ በስተቀር ፈውስ አይገኝም።" [ሚፍታሑ ዳሪ ሰ፞ዓዳህ: 1/306]

Post a Comment

0 Comments