Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሻዕባንን ወር መፆም

✔️ የሻዕባንን ወር መፆም
⬅️ ﻋَﻦْ ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ - ﻗَﺎﻟَﺖْ :
↪️ ዓኢሻህ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና
ስለነብዩﷺ የሻዕባን ወር አፇፇም ተጠይቃ ስትመልስ
 ⬅️‏« ﻛَﺎﻥَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ -ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﻳَﺼُﻮﻡُ ﺣَﺘَّﻰ ﻧَﻘُﻮﻝَ ﻻ ﻳُﻔْﻄِﺮُ، ﻭَﻳُﻔْﻄِﺮُ ﺣَﺘَّﻰ ﻧَﻘُﻮﻝَ ﻻ ﻳَﺼُﻮﻡُ، ﻓَﻤَﺎ ﺭَﺃَﻳْﺖُ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪِ -ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﺍﺳْﺘَﻜْﻤَﻞَ ﺻِﻴَﺎﻡَ ﺷَﻬْﺮٍ ﺇِﻻ ﺭَﻣَﻀَﺎﻥَ، ﻭَﻣَﺎ ﺭَﺃَﻳْﺘُﻪُ ﺃَﻛْﺜَﺮَ ﺻِﻴَﺎﻣًﺎ ﻣِﻨْﻪُ ﻓِﻲ ﺷَﻌْﺒَﺎﻥَ ‏»
📚 ‏( ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ : 2176 ‏) 
↪️《አያቋርጡም እስከምንል ድረስ አከተታለው ይፆማሉ እንዲሁም ከአሁን ቡሀላ አይፆሙም እስከምንል  ድረስ አከታትለው ያፈጥራሉ።
ይሁንና ከረመዷን ውጪ እንደሻዕባን ወር አከታትለው ብዙ ቁጥርን ሲፆሙ አላየውም።》ብላለች።
📚ኢማሙ ነሰኢ(2176)
➡️ ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው ቁምነገር የሻዕባንን ወር ሙሉውን ባይሆንም እንኳን አብዛኛውን በመፆም  ወደ አላህ መቃረብ ከረመዷን በፊት ከአላህ ጋር የነበረንን ጥሩ ያልሆነና ጥሩ ያልነበረን ግንኙነትንና ጥሩ ያልነበረ ማንነታችንን ረመዷን ከመግባቱ በፊት ወደ ጥሩ ማንነት በማምጣት የረመዷን ወር ሲገባ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት እጅግ በጣም ጥሩ ወደሚባል ደረጃ የምናሳድግበት ምቹ አጋጣሚ ነው።
➡️ በመሆኑም የሻዕባንን ወር ስንፆም መፆም ብቻ ሳይሆን ከነበርንበት ጥሩ ያልነበረውን ማንነታችንን ከልብ ወደ አላህ በመመለስ(ተውባህ በማድረግ) እና ቀደም ሲል ለፈፀምነው አመፅና ወንጀል አላሀን ይቅርታ እየጠየቅን(ኢስቲግፋር እያደረግን) መሆን አለበት።
➡️ ሻዕባንን በዚህ መልኩ ልንጠቀምበት ከቻልን የረመዷን ወር ለእኛ ለበለጠ ወደ አላህ መቃረብና ለተሻለ ጀዛእና ለላቀ ደረጃ የምንተጋበት መልካም አጋጣሚ ነው ሚሆንልን።
⬅️﴿أَلَم يَعلَموا أَنَّ اللَّهَ هُوَ يَقبَلُ التَّوبَةَ عَن عِبادِهِ وَيَأخُذُ الصَّدَقاتِ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ التَّوّابُ الرَّحيمُ﴾
التوبة(104)
↪️ ልቅናው የላቀው አላህ《አላህ ወደ እሱ የሚመለሱ(ተውባህ ሚያደርጉ) ሰዎች  እሱ መመለሳቸውን(ተውባቸውን) የሚቀበል፣ሰደቃን የሚቀበልና አላህ ተውባን የሚቀበል አዛኝ መሆኑን አያውቁምን?》ብሎናል።
➡️ ከወንጀሉ ተፀፅቶ የሚመለስ ምንም ወንጀል እንደሌለበት ነው መባሉን ሳንዘነጋ አሁን የጀመርነውን የሻዕባንን ወር አነሰም በዛ ከነበርንበት ደረጃ ለውጥ በማምጣት የአቅማችንን ያህል ተውባን፣ኢስቲግረፋርንና የአላሀን ፍራቻን(ተቅዋን) እንከስብ።
➡️ በመሆኑ ወንድምና እህቶች እኔም እናንተም ከረመዷን በፊት በሻዕባን ወር ኢስላማዊ ለወጥ በማምጣት ከረመዷን በፊት ወደ አላህ በመመለስ(ተውባህ በማድረግ)፣ለሰራነው አመፅና ስህተት ምህረትን በመጠየቅ(ኢስቲግፋር በማድረግ) ተቅዋን(የአላሀን ፍራቻ) ለማግኘት ያላለሳለስ ጥረት እናድርግ።
 ✍ አቡ ኢብራሂም
መጋቢት 18/07/2012 ዓ ል
ሻዕባን 03/07/1441 አ ሂ

Post a Comment

0 Comments