ድሃ ማነው⁉
የአላህ መልክተኛ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
“ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?” በማለት ይጠይቃሉ።
ሰሐቦችም ፦
“እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው።” በማለት ይመልሳሉ።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ግን፦
“ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ግና ይህ ሰው
※ አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣
※ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣
※ የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣
※ የሌላውን ደም አፍስሷል፣
※ አንዱን መትቷል፣
※ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣
ያኔም (የትንሳኤ ምርመራ ቀን ) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ ጥሩ ሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል። ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል።” በማለት መለሱላቸው።
(ሙስሊም ሐዲሥ ቁ.6531)
ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ
0 Comments