Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ህልምና ቅዠት በኢስላም እይታ

🍃ህልምና ቅዠት በኢስላም እይታ🍃

💥ዲነል-ኢስላም ህይወታችን ላይ ሊገጥሙን ለሚችሉ ነገሮች በሙሉ ህግና ስርዓት አስቀምጧል፣ይህን አውቀን መኖር፥ በዲናችን እንድንተማመንና ህይወትን ከሚረብሹ ነገሮችም ሰላም ለማግኘት ይረዳል

▪️ብዙ ሰዎች በየጊዜው የሚያስጨንቅ/የሚያሳስብ ህልም አየሁ እያሉ ያወራሉ በርካቶችም የህልምን ፍቺ እንደፈትዋ ይጠይቃሉ! የምናየውን ሁሉ ህልም ፍቺ ለማወቅ መጣር ተገቢና አስፈላጊ አይደለም
 ▪️የህልም ህግ በኢስላም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው፥

🔸((ጥሩ ህልም ያየ ሰው ይደሰት ጥሩ ነገርም ይጠብቅ፣መጥፎ ህልም ያየ ሰው ደግሞ ቀጥሎ የሚገለጹ ነገሮችን ከማድረግ ጋር ችላ ብሎ ይተወው)) የሚል ነው

▪️ይህ በእንዲህ እንዳለ፥
 ነቢያችን صلى الله عليه وسلم ጥሩ ህልም ከአላህ እንደሆነና እንዲህ ዓይነቱን የሚያስደስት ህልም ያየ ሰውም፥
1/ አል-ሐምዱ ሊላህ الحمد لله
በማለት ጌታውን እንዲያመሰግን
2/ ለሚወዳቸው ሰዎችም እንዲናገር ሲመክሩ፤

🔹መጥፎ ወይም አስፈሪ ህልም (ቅዠት) ከሸይጣን እንደሆነ ገልጸው በዚህ የተጠቃ ሰውም፥
1/ ሶስት(3)ጊዜ
أعوذ بالله من الشيطان الرجيم
 "አዑዙ-ቢላህ ሚነሽ'ሸይጣኒ'ርረጂም" በማለት  ከህልሙ/ከቅዠቱ ክፋት በአላህ እንዲጠበቅ
2/ ሶስት ጊዜ ወደ ግራ "እትፍ- እትፍ" እንዲል
3/ ለማንም እንዳይናገር
4/ ህልሙን ሲያይ (ሲቃዥ) ተኝቶበት ከነበረው ጎኑ ወደሌላ ጎኑ ዞሮ እንዲተኛ
5/ ተነስቶም እንዲሰግድ መክረው፤
6/ ይህን ካደረገም ያየው መጥፎ ህልም ምንም እንደማይጎዳው ገልጸዋል

▪️እነዚህ ምክሮች፥ ቡኻሪ፣ ሙስሊምና አቡ ዳውድ ከዘገቧቸው ሰሒሕ ሐዲሦች ተወሰደው የተቀናበሩ ናቸውና
ህልም ባዩ ቁጥር ትርጉሙን ለማወቅ ወይም ደግሞ አደጋ ሊደርስብኝ ነው ብሎ ከመጨነቅ በመታቀብ የአዛኙን ነቢይ ምክር ተቀብሎ የተረጋጋ ህይወት መኖር ይበጃል::

اللهم إنا نسألك رؤيا صادقة غير كاذبة ونافعة غير ضارة.

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
22/12/1439ዓሂ@ዛዱል መዓድ

Post a Comment

0 Comments