Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ አብዱልቃድር ጀይላኒ - رحمه الله - የሰይጣንን ተንኮል እንዴት ተከላከሉ?



ሸይኽ አብዱልቃድር ጀይላኒ - رحمه الله - የሰይጣንን ተንኮል እንዴት ተከላከሉ?

ሸይኽ አብዱልቃድር ጀይላኒ رحمه الله በስፋት በሚታወቀው ታሪካቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

((ከእለታት አንድ ቀን በኢባዳ ውስጥ ነበርሁ፡፡ በዚህ መካከል ከላይ በኩል በብርሃን የተከበበ ታላቅ ዙፋን ተመለከትሁ፡፡ ከዚያም “አብዱልቃድር ሆይ! እኔ ጌታህ ነኝ በሌሎች ላይ ሀራም ያደረግሁትን ለአንተ ፈቅጀልሃለሁ፡፡” አለኝ፡፡ እኔም “ከአንተ በስተቀር በእውነት የምትመለከው አላህ ነህ?” አልኩት፡፡ “አንተ የአላህ ጠላት ወራዳ ዘወር በል!!!” አልኩት፡፡ የነበረው ብርሃን ተበጣጥሶ በጨለማ ተተካ፡፡ ከዚያም “አብዱልቃድር ሆይ! በተሰጠህ ዲንና እውቀት ነጻ ወጣህ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ሰባ ግለሰቦችን ፈትኛለሁ፡፡” አለኝ፡፡
ከዚያም “ሰይጣን መሆኑን እንዴት አወቅህ?” የሚል ጥያቄ ለሸይኽ አብዱልቃድር ጀይላኒ ቀረበላቸው፡- “በሌሎች ላይ ሀራም ያደረግሁትን ለአንተ ፈቅጃለሁ፡፡” ባለችው ንግግሩ ብቻ የእርሱን ማንነት በቀጥታ ተገነዘብኩ፡፡
 የነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ሸሪዓ እንደማይሰረዝና እንደማይቀየር በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡፡ ይህ ሆኖ እያለ “ከእኔ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለብኝ አላህ ነኝ ሳይል እኔ ጌታህ ነኝ  በማለት በቀጥታ ተናገረ፡፡))

قاعدة الجليلة في التوسل والوسيلة  ص/44

https://t.me/alateriqilhaq

Post a Comment

0 Comments