Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሀይድ እና የኢስቲሃዷ ሸሪዓዊ ብይን


የሀይድ እና የኢስቲሃዷ ሸሪዓዊ ብይን

የሀይድና የኢስቲሃዷ የትምህርት ክፍል ከፊቅህ የትምህርት ክፍሎች አስቸጋሪውና ውስብስቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ፉቀሀዎች በርካታ ነገሮች የተናገሩ ቢሆንም የሀዲስ ድጋፋቸው ግን ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም እውቀት ፈላጊ የእነዚህን ፉቀሃዎች ንግግር አንብቦ ሙሉ በሙሉ መቀበል ሳይሆን በቁርዓንና በሐዲስ ሊመዝነው ይገባል፡፡ ከቁርዓንና ከሐዲስ ጋር ከገጠመ እንቀበለዋለን፡፡ ካልገጠመ ደግሞ እንተወዋለን፡፡ ስህተት ለፈጸመው አካል ለስህተቱ አላህ እንዲምረው ዱዓ እናደርጋለን፡፡

ሐይድ (የወር አበባ) ፡ በአረበኛ ቋንቋ ሲተረጎም መፍሰስ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ወንዙ በሸለቆው መካከል ሲፈስ “ሃዶል ዋዲ” በሚል በአረብኛ ቋንቋ ይገለጻል፡፡

በሸሪዓ ደግሞ ለአቅመ አዳም የደረሰች ሴት የሚደርስባት ተፈጥሯዊ ደም ነው፡፡ ሐይድ ከእናቲቱ እምብርት ጋር በተያያዘው ትቦ አማካኝነት ወደ ጽንሱ በመተላለፍ ለጽንሱ ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት እንደሚሰጥ የህክምና ባለሙያወች ይናገራሉ፡፡ ይህም የአላህ ጥበብ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ ለዚህ ነው እርጉዝ የሆነች ሴት ባብዛኛው የወር አበባ የማታየው፡፡
ሐይድ፡ ድንገት የሚከሰት ጉዳይ ሳይሆን በሴቶች ላይ አላህ የፈጠረው ተፈጥሯዊ ባህሪ ለመሆኑ አኢሻ ያስተላለፈችው የረሱል ﷺ ሐዲስ ያስረዳል፡፡

"إن هذا أمر كتبه الله على بنات آدم" ( البخاري\٣٠٥، مسلم\١٢١١)
“ይህ (ሐይድ) አላህ በሴቶች ላይ የጻፈው (የወሰነው) ነገር ነው፡፡”
(ቡኻሪ/305 ሙስሊም/1211)

ኢስቲሃዷ (የበሽታ ደም) ፡ ደግሞ ከሐይድ የተለየ ፈሳሽ ነው፡፡ ማለትም ልክ እንደ ሀይድ ተፈጥሯዊ ሳይሆን ከደም ስር ፈንድቶ የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
የኢስቲሃዷን ምንነት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በሚከተለው ሐዲሳቸው ገልጸውታል፡-

"إنها دم عرق" ( البخاري\٢٢٨، مسلم\٣٣٣)
“እንሆ (ኢስቲሃዷ) የጅማት ደም ነው፡፡” (ቡኻሪ/228 ሙስሊም/333)

የወር አበባን የመነሻ ቀን እና የማጠናቀቂያ ቀን በተመለከተ ፉቀሀዎች የተለያየ አቋም ያላቸው ሲሆን ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ ግን የአብዛኞችን ሴቶች የወር አበባ ቀን መነሻና መድረሻ በማጥናት ግምታዊ ቁጥር ከመናገር ውጭ ትክክለኛውን በማስረጃ መናገር አይቻልም ይላሉ፡፡
የወር አበባ መነሻን አስመልክቶ መገለጫዎች ከታዩ በወር አበባነት የምንወስደው ሲሆን የወር አበባ ምልክቶች ከሌሉ ደግሞ የጡሁር ወቅት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የወር አበባው ደም አልቆ ነጣ ያለ ወይም ደፍረስ ያለ ፈሳሽ ከመጣ ከሐይድ መጥራቷን እናውቃለን ማለት ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ታጥባ ሶላቷን መስገድ ይኖርባታል፡፡
ከእርግዝና ጋር ሀይድ የለም፡፡ ለዚህ ነው በእርግዝና ላይ ሆነው የተፈቱ ሴቶች ኢዳቸው በመውለድ የሚጠናቀቀው፡፡ ከወለዱ በኋላ ባል ማግባት ይችላሉ፡፡
ኢማም አህመድ እንዲህ ይላሉ፡-
“አንዲት ሴት ማርገዟን የምታውቀው የወር አበባ ደም በመቋረጡ ነው፡፡”

ሸይኽ ዑሰይሚን እንዲህ ብለዋል:–
ርጉዝ ሆና ባሏ የሞተባት ሴት በእርግዝናዋ መካከል በየወሩ ሶስት ጊዜ ደም ብታይ ዒዳው የሚያልቀው በመውለዷ እንጅ ደም በማየቷ አይደለም፡፡ የሚፈሳት ደም ግን ሶላት ከመስገድ ጾም ከመጾም ያግዳታል፡፡

የወር አበባ የምታይ ሴት ጾምን ቀዷ የምታወጣ ሲሆን ሶላትን ግን ቀዷ አታወጣም፡፡ ስለዚህ የወር አበባን አስመልክቶ የሚከተሉት ሸሪዓዊ ህግጋቶች ይገኛሉ፡-
አንደኛ፡- የወር አበባ የምታይ ሴት ጾም አትጾምም ሶላትም አትሰግድም፡፡
ሁለተኛ፡- ከወር አበባዋ ከጸዳች ጾምን ቀዷ ታወጣለች ሶላትን ግን ቀዷ አታወጣም፡፡

ሐይድ የምታይን ሴት ግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡ በሀይድ ሰዓት ሳይገደድ ሚስቱን የተገናኘ ሰው ሐጢያተኛ ነው፡፡ ሴት ልጅ በሐይዷ ጊዜ ተገዳ ግንኙነት ከፈጸመች ሀጢያት የለባትም፡፡ ነገር ግን ወዳና ተስማምታ ግንኙነት ከፈጸመች ሐጢያተኛ ትሆናለች፡፡
የወር አበባ በምታይ ሴት ከብልቷ ውጭ ባሉ የሰውነት ክፍሎቿ እርካታን ማግኘት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- ማቀፍ፣ መሳም እና መዳሰስ በሸሪዓችን አይከለከልም፡፡ በዚህ ወቅት ድንገት ከብልቱ የዘር ፈሳሽ ከወጣ ግን ትጥበት ይኖርበታል፡፡

ከወር አበባ ጠርታ እስካልታጠበች ድረስ ከጾም እና ከፍች ውጭ ሌሎች ነገሮች በእርሷ ላይ እርም (ሀራም) ይሆናሉ (ጾም ለመፆምና ፍቺ ለመፈፀም ትጥበቱ የግድ አደለም)፡፡ የወር አበባዋን ጨርሳ ገላዋን ያልታጠበች ሴት ባሏ ሊፈታት ይቻላል፡፡ ጾም መጾምም ትችላለች፡፡
ሴት ልጅ የወር አበባዋን ከጨረሰች በኋላ ገላዋን ሳትታጠብ በቀጥታ ከባሏ ጋር ግንኙነት ማድረግ አትችልም፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡-

﴿وَلاَ تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىَ يَطْهُرْنَ ﴾ (البقرة ٢٢٢)
“ንጹህ እስከሚሆኑም ድረስ አትቅረቧቸው፡፡”
(በቀራህ፡ 222)

የወር አበባ ደምን ከኢስቲሃዷው ደም የምንለይበት አራት መንገዶች፡-
1- ከለር (ቀለም) ፡ - የወር አበባ ደም ጠቆር ያለ ሲሆን የኢስቲሃዷ ደም ደግሞ ቀላ ያለ ነው፡፡
2- ውፍረት ፡- የወር አበባ ደም ወፈር ያለ ሲሆን የኢስቲሃዷ ደም ደግሞ ቀጠን ያለ ነው፡፡
3- ሽታ፡- የወር አበባ ደም የሚከረፋ ሽታ ያለው ሲሆን ኢስቲሃዷ ግን መጥፎ ሽታ የለውም፡፡
4- የመርጋት ባህሪ፡- የኢስቲሃዷ ደም የመርጋት ባህሪ ሲኖረው የወር አበባ ደም ግን የመርጋት ባህሪ የለውም፡፡

ከላይ ከገለጽናቸው የወር አበባ ምልክቶች አንዱ ከታየ የወር አበባ መሆኑ ታውቆ ሶላት ከመስገድ ጾም ከመጾም እና ግብረ-ስጋ ግንኙነት ከመፈጸም መታቀብ ይገባታል፡፡ ከነዚህ አራት አይነት የወር አበባ ምልክቶች ውጭ ከሆነ ግን የኢስቲሃዷ ደም በመሆኑ ከላይ የጠቀስናቸውን ክልክል ነገሮች መፈጸም ትችላለች፡፡ ባይሆን በኢስቲሃዷ ጊዜ በየሶላት ወቅቱ ንጽህናዋን መጠበቅ ይኖርባታል፡፡

ልምዷ የጠፋት ወይም የወር አበባ አይታ የማታውቅ ሴት የማያቋርጥ (የኢስቲሃዷ) ደም ብታይ በወሩ መጀመሪያ በእርሷ አቻ የሆኑ ሴቶች የሚቆጥሩትን ቀናት ያክል በመቁጠር ሶላት ከመስገድ ልትቆጠብ ይገባታል፡፡ ሌሎችን ቀናቶች ደግሞ እንደጠራች ታሳቢ አድርጋ ደሙ ሲወጣበት የነበረውን የሰውነት አካሏን ታጥባ ውዱ አድርጋ ብልቷ ውስጥ ጥጥ አስገብታ በማሰር በጥንቃቄ ሶላቷን ልትሰግድ ይገባል፡፡ ከዚህ ጥንቃቄ በኋላ እየሰገደች የሚወጣው ደም ሶላቷን አያበላሽባትም፡፡ ከዚህ በፊት የወር አበባ የማየት ልምድ ያላት ሴት ከሆነች ግን በልምዷ መሰረት የወር አበባውን ቀን ቆጥራ ሶላት ከመስገድ ትቆጠብ፡፡

የወር አበባ የምታይበትን የቀን ቁጥር ታውቃለች ነገር ግን ከወሩ መጀመሪያ ይሁን ወይም መጨረሻ ወይም መካከል አላወቀችውም፡፡ በዚህ ሰዓት ከጥርጣሬዋ አመዛኙን ወስዳ ለወር አባባ ቀናቶች በማድረግ ሶላት ከመስገድ ትቆጠብ፡፡

የለመደችው ሰባት ቀን ነበር አምስት ቀን አይታ ተጦሃራች ታጥባ ሶላቷን ትጀምር፡፡ ምክንያቱም የወር አበባው ሲቆም ባብዛኛው መጥራቷን የሚያመላክት ነጭ የሚመስል ወይም ደፍረስ ያለ ፋሳሽ ይወጣል፡፡ ይህ ከሆነ የወር አበባዋን ጨርሳለች ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሴቶች ይህ ነጭ ፈሳሽ ላይወጣቸው ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ነጭ ጥጥ ይዛ የወር አበባው በወጣበት የሰውነት ክፍል አስገብታ በማውጣት ጥጡ የተለየ ከለር ካላመጣ

የባህር ዳር አህሉ ሱና መሻይኾች ገፅ, [25.11.19 12:02]
ከወር አበባዋ መጥራቷን የምታውቅበት አንዱ ምልክት ይሆናል ማለት ነው፡፡

በልምድ ስድስት ቀን የወር አበባ የምታይ ሴት አራት ቀን አይታ ተጧሃራች ታጥባ ትስገድ፡፡ ስድስተኛው ቀን ላይ ተመሳሳይ የሆነ ደም ተመልሶ ከመጣ ደሙ እስኪቋረጥ ድረስ ሶላት ከመስገድ ትቆጠብ፡፡(ነገር ግን እንደ ሁለት ሃይድ ታስቦ ኢዳ መቁጠሪያ ሊሆን አይገባም)
ወደ ቢጫ ከለር የሄደ ደፍረስ ያለ ፈሳሽ የወር አበባ ከምታይበት ቀናቶች በፊት ከመጣ እንደወር አበባ ትውሰደው፡፡ የወር አበባዋን ስትጨርስ ከሆነ የመጣው ይህ ፈሳሽ ከወር አበባ አይቆጠርም፡፡
ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው ሀዲስ ነው፡-

" كنا لا نعد الصفرة والكدرة بعد الطهر شيئا"( ابو داود\٣٠٧)
“ከጡህር በኋላ ቢጫማውን እና ደፍረስ ያለውን ከምንም አንቆጥረውም ነበረ፡፡” (አቡ ዳውድ/307)

ኢስቲሃዷ ከወር አበባው እና ከወሊድ ደም የተለየ ደም ነው፡፡ ወይም ከለመደችው የወር አበባ በላይ አንዲት ሴት የምታየው ደም ነው፡፡ የበሽታ ደም ዘወትር የምታይ ሴትና ሽንት ወይም ሰገራ ዘወትር የሚመጣው ሰው ሸሪኣዊ ብይናቸው ተቀራራቢነት አለው፡፡

ሁልጊዜ ደም የምታይ ሴት ደሙ እስኪወገድ ድረስ ብልቷን ታጥባ በፎጣ ካዳረቀች በኋላ በጥጥ ወይም በቅዳጅ ጨርቅ ብልቷን ትሰርና ውዱዕ አድርጋ ትስገድ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚመጣው ደም አይጎዳትም ሶላቷም አይበላሽም፡፡ ውዱዕ ካላፈረሰችና በብልቷ የሚወጣ ነገር ከሌለ ዙሁር በሰገደችበት ውዱዕ አስርንም መስገድ ትችላለች፡፡ ሽንት ዘወትር የሚፈሰው ሰውና ሰገራ የሚወጣውም ሰው ሁክሙ ከኢስቲሃዷ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡
ማስረጃችን የሚከተለው ሀዲስ ነው፡-
قوله ﷺ لفاطمة بنت أبي حبيش : "اغسلي عنك الدم وصلي"البخاري\٢٢٨، مسلم\٣٣٣) 
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ለፋጢማ ቢንት አቢ ሁበይሽ እንዲህ ብለዋታል፡-
“ከአንች ዘንድ የሚገኘውን ደም ታጠቢና ስገጅ፡፡”
(ቡኻሪ/228 ሙስሊም/333)

ኢስቲሃዷ ያለባት ሴት ዙህርን በመጨረሻው ወቅት አሱርን ደግሞ በመጀመሪያው ወቅት በማድረግ ሁለቱንም ሶላቶች በአንድ ውዱዕ መስገድ ትችላለች፡፡ የኢስቲሃዷ ደም ለምታይ ሴት ገላን መታጠብ የተወደደ እንጅ ከሀይድ በኋላ እንዳለው ትጥበት ዋጅብ አይደለም፡፡

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Post a Comment

0 Comments