Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መካሪም ተመካሪም ምንኛ ያ ማሩ ድንቅ ስብእናዎች ናቸው?!


መካሪም ተመካሪም ምንኛ ያ ማሩ ድንቅ ስብእናዎች ናቸው?!
ታላቁ የኢስላም ሸይኸ ኢብኑ ተይምያህ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ሲሉ ተማሪያቸውን ኢብኑል ቀይምን አላህ ይዘንላቸውና መከሩት።
የተለያዩ ሹብሃዎችን እየሰማሁ ለሸይኻችን ሳቀርብላቸው፦"ልብህን እንደ እስፖንጅ አታድርገው ለውዥንብሮችና ላገኘው ነገር ሁሉ የሚመጥ እና የሚተፋ ። ነገር ግን እንደ ጠንካራ መስታወት ከላዩ እንዲያልፍ ብቻ አድርገው። ይህ ከሆነ በጥንካሬው የምትቀስማቸውን ጥሩ ነገሮች መያዝና መፅናት ሲያስችልህ በወለሉ ደግሞ መጥፎን ነገሮች አብጠርጥሮ ስለሚያሳይህ ለይተህ እንድታውቅና ወደ ውስጥ እንዳታስገባ ያደርግሃል ማለት ነው።【"ሚፍታሁ ዳሩ አሰዓዳህ"(1/443)】
ታዲያ ኢብኑል ቀይም እንደዚህ የጠቀመኝ ምክር የለም ይላሉ !
በዚህም የተነሳ ከብዙ ሹብሃ መረብ በአላህ ፍቃድ መዳን ችለዋል። እኛም በዚህ ምክር ተጠቃሚ ያድርገን።

نعم الناصح والمنصوح!.
يقول ابن القيم في عرضه لهذه الوصية: (قال لي شيخ الإسلام – رضي الله عنه – وقد جعلت أورد عليه إيراد بعد إيراد: لا تجعل قلبك للإيرادات والشبهات مثل السفنجة، فيتشربها؛ فلا ينضح إلا بها ولكن اجعله كالزجاجة المصمتة، تمر الشبهات بظاهرها ولا تستقر فيها؛ فيراها بصفائه ويدفعها بصلابته، وإلا فإذا أَشربت قلبك كل شبهة تمر عليها صار مقراً للشبهات، أو كما قال) ((مفتاح دار السعادة)) (1/ 443)
https://telegram.me/sultan_54