Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወገኔ ሆይ! አሕመድን መሆን ቢያቅትህ አቡል ሀይሠምን መሆን አያቅትህ!!

 
====== ወገኔ ሆይ! አሕመድን መሆን ቢያቅትህ አቡል ሀይሠምን መሆን አያቅትህ!! =====

የኢማሙ አሕመድ ልጅ የሆኑት ዐብደላህ እንዲህ ይላሉ:–
አባቴን ብዙ ጊዜ "አላህ ሆይ! አቡል ሀይሠምን ማረው" ሲሉ እሰማቸው ነበር። "አባቴ ሆይ! አቡል ሀይሠም ማነው?" ስላቸው እንዲህ አሉኝ:– "አንድ ከዘላኖች የሆነ ሰው ነው። ፊቱን አላየሁትም። ከተገረፍኩበት ቀን ቀድሞ በነበረው ሌሊት በጠባብ ጨለማ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ። የሆነ ሰው በእጁ ነረተኝና "አህመድ ኢብኑ ሐንበል ነህ አንተ?" አለኝ።
"አዎ" አልኩት።
"ታውቀኛለህ?" አለኝ።
"አይ" አልኩት።
"እኔ ሌባው፣ አስካሪ መጠጥ ጠጪው፣ ሽፍታው አቡል ሀይሠም ነኝ። በተለያየ ጊዜ 18,000 አለንጋ እንደተገረፍኩ ከአሚረል ሙእሚኒን መዝገብ ላይ ተመዝግቧል። እኔ በሸይጧን መንገድ ላይ ሆኜ ይህን ሁሉ ችያለሁ። ስለዚህ አሕመድ አንተ በአላህ መንገድ ላይ ነህና ታገስ!!" አለኝ።

·
አስረውኝ ግርፋቱ በተጀመረ ጊዜ አለንጋው ጀርባየ ላይ ባረፈ ቁጥር የአቡል ሀይሠምን ንግግር እያስታወስኩ ለራሴ "አሕመድ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ ታገስ!" እለው ነበር።

★ (አሕመድ) ኢብን ሐንበል መሆን ካልቻልክ አቡል ሀይሠምን ሁን!!
★ ጥፋት ላይ የሰመጥክ ብትሆን እንኳን ሐቅን ውደድ!!
★ ወንጀል ላይ የተነከርክ ብትሆን እንኳን ለጌታቸው ታዛዥ የሆኑትን ውደድ!!
★ ሸይጧን የፈለገ ካንተ ቢያገኝ ለአላህ ሁን!!

[መናቂቡል ኢማም አሕመድ: 450–451]
[አስሶፍዋ: 1/485]

ከዐረብኛ የተመለሰ
 

Post a Comment

0 Comments