Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ ያስከብራል






📚ተውሂድ ያስከብራል
≅≅≅≅≅≅≅
☝🏼የአላህን መብት ያወቀ
ከመዳፈር የተጠነቀቀ
ከባዕድ አምልኮ የራቀ
የሽርክ ምንጮችን ያደረቀ
መግቢያውን ዘግቶ የጠበቀ
ጌታውን ያለ አጋር …
በማምለክ ያላቀ
እሱ ነው በእምነቱ ፅኑ …
ለነገው የሰነቀ
ለራህመቱ የታደለ …
ከእሳትም የተጠበቀ።

ሸይኽ ሳሊህ አስስንዲ ሀፊዘሁላህ "ኢዕላም አስሱናህ" የተሰኘውን ድርሳን ባብራሩበት መልእክታቸው ገፅ 25 ላይ እንደሰፈረው ልቡ በተውሂድ ስለታነፀ ሰው ሲያወጉ ከሽርክ ዝባዝንኬዎች መዳንና ለንፁህ ተውሂድ መብቃት ብሎም ተግባራቱን በነቢዩ አለይሂ አሰላቱ ወሰላም ሱና መሰረት መተግበር ከምንም በላይ እንደሚያስከብር፣ ንፁህ ወዳጆችንም እንደሚያስገኝ ከዚህም አልፎ ይህንን ሀቅ ያንፀባረቀ ሰው ከሱ አንፃር ሙስሊሞች ሊጠብቁለት የሚገባው ሀቅና መብት በነሱ ላይ እንዳለው ጠቁመዋል።
በተለይ ወደ ሸሪዓዊ የትምህርት ገበታ የተጠጉ ጡላበል ዒልም ይህንን ሀቅ በግንባር ቀደምትነት ሊጠብቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህም ጋር ግን አሳዛኙንና አሳሳቢውን ተጨባጭ ክስተት ከመጠቆም አልቦዘኑምና የወጣቱ ከአንድነትና ከወዳጅነት ይልቅ በመናቆር ላይ መጠመድ፤ ልክ በተውሂድ እና በሱና እንኳ እንደማይገናኝ ሰው በጠላትነት መፈራረጅ ብሎም መካሰስና ድንበር መተላለፍ ኣንዱ ያንዱን መብት ለመዳፈሩ ማሳያ መሆኑን ሲጠቁሙ ቀጣዩን ጠቅሰዋል።☞
«በተውሂድ ተውቦ በኢስላም ላይ የፀናና በነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፈለግ ላይ የዘወተረ ሰው መብቱ ላቅ ያለ ነው። ምክንያቱም ይህን ታላቅ የሆነ ጉዳይ ይዞ ተገኝቷልና ለአላህ ሲባል እሱን መውደድና መወዳጀት የግድ ነው። የዚህ አይነቱን ሰው መርዳት ግዴታ ነውና ለውርደት ኣለመዳረግም ግድ ይላል።
በዚህ ረገድ ደግሞ ግንባር ቀደም ባለመብት የሆኑት ኢስላማዊ እውቀትን በመገብየት ላይ የተሰማሩ ተማሪዎች ናቸው። እያየነውና እየኖርነው ያለነው ተጨባጭ እውነታ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በአንዳንድ ተማሪዎች መካከል ይህንን መብት በመጠበቁ ረገድ ትልቅ የሆነ ጉድለት መኖሩን ነው የሚያሳየን። ይህ ነጥብ ደግሞ አሻሚ ያልሆኑ አስረጆች ኣሉት።
ስለዚህ ሸሪዓዊ እውቀት በመቅሰም ላይ ያለኸው የሱና ተከታይ ከሆንክ በእውነተኛነት ይህን ነገር መያዝ አለብህ። አንተ እውቀት ፈላጊ ሆይ ይህን የዐይንህን ብሌን ቸል ካልከው በጉዳዩ የጀነትና የእሳት ጉዳይ አለበት።» በማለት መክረዋል።
[ شرح أعلام السنة المنشورة .ص ٥٢ ]
أ.د. صالح بن عبدالعزيز سندي
≅≅≅ا═•═💎═•═ا≅≅≅≅
✍🏽Abufewzan
ዙል ቂዕዳ 07/1439
July 20/2018

Post a Comment

0 Comments