Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቶች በወር አበባ ጊዜ ሊያውቋቸው የሚገቡ ጥቂት ድንጋጌዎች


እህቶች በወር አበባ ጊዜ ሊያውቋቸው የሚገቡ ጥቂት ድንጋጌዎች
ከሴት እህቶቻችን በተፈጥሮ አማካኝነት ከእነሱ የሚፈሱ የደም አይነቶች ሶስት ሲሆኑ እነሱም፦
1: የወር አበባ ደም (ሃይድ)
2: የወሊድ ደም (ኒፋስ)
3: የህመም(ጉዳት) ደም (ኢስቲሃዳ) ሲሆኑ

☞ የወር አበባ ደም (ሃይድ)፦ ከለሩ ጥቁር ሲሆን ወፍራምና ጥሩ ያልሆነ ሽታ ያለው ከታወቀ ቦታና በተወሰነለት ጊዜ የሚፈስ የደም አይነት ነው። የወር አበባ ደምን አላህ በሴት ልጆች ላይ በተፈጥሮ ያደረገው የደም አይነት ሲሆን ነብዩ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ «ይህ የወር አበባ ደም አላህ በሴት ልጆች ላይ የፃፈው ነገር ነው» ብለዋል።
☞ የወር አበባ ደም መነሻና መጨረሻውን በተመለከተ ከነብዩ አንደበት ትክክለኛ የሆነ ሀዲስ አልተገኘም። እናም የወር አበባ ጊዜ መነሻና መጨረሻ እንደ ሴቶቹ ፀባይ ይወሰናል። ነገር ግን ለመለያ የተቀመጡ ምልክቶች አሉ።
የወር አበባ ደም መጀመሩንና ማቆሙን የምናውቅባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።
1) የወር አበባ መምጣቱን የምናውቀው፦
ከመልኩ ሽታውና ውፍረቱ አኳያ የወር አበባ ደም መሆኑ የሚታመን ደም ሲፈስ የወር አበባ መጥቷል ይባላል።
2) የወር አበባ ለመቆሙ ሁለት ምልክቶች ያሉ ሲሆን እነሱም ፦
2:1) ሙሉ ለሙሉ ደሙ መፍሰሱን ማቆሙ ሲሆን ይህንንም ለማረጋገጥ ንፁህ ጨርቅ፣ ጥጥ ወይም የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያን በመጠቀምና ንፁህ ሆኖ መቆየቱን በማረጋገጥ መቆሙን ማረጋገጥ ይቻላል።
2:2) ነጭ ፈሳሽ ከብልት መፍሰሱ ሲሆን ይህም የወር አበባ ደም በሚቆምበት ጊዜ ከማህፀናቸው የሚፈስ ንፁህ ፈሳሽ ነው ።
☞ በወር አበባ ደም ጊዜ የሚከለከሉ ነገሮች፤
1) ሶላት (ስግደት) ዓሊሞች በአጠቃላይ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በእሷ ላይ ሶላት ሃራም መሆኑን ተስማምተዋል። ይህ ፈርድ(የግዴታ) እና የሱና ሶላቶችን ያጠቃልላል። ይሁንና በወር አበባ ደም ምክንያት ያለፋትን ሶላትም ቀዷ አታወጣም።
2: ፆም (ሲያም) ፦ የወር አበባ ደም ላይ ያለች ሴት ፆም መፆም በእሷ ላይ ክልክል ሲሆን ስትፀዳ ግን ቀዷ ማውጣት ይኖርባታል። እናታችን አዒሻ ሙስሊምና አቡ ዳውድ በዘገቡት ሃዲስ ላይ (የወር አበባችን ሲመጣ ፆምን ቀዷ እንድናወጣ ስንታዘዝ፤ ሶላትን ግን ቀዷ እንድናወጣ አንታዘዝም ነበር) ብለዋል።
3: የግብረ ስጋ ግንኙነት ፦ አንድ ሴት የወር አበባ ላይ በምትሆንበት ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ክልክል (ሃራም) ይሆንባታል።
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል፦
فَاعْتَزِلُوا النِّسَاءَ فِي الْمَحِيضِ ۖ
«ሴቶችን በወር አበባ ጊዜ ራቁ» አል በቀራ 222
ነብዩም፦ «በወር አበባ ጊዜ ከኒካህ (ግብረ ስጋ ግንኙነት) በቀር ሁሉንም ነገር መፈፀም ትችላላችሁ» በማለት ነግረውናል። ሀዲሱ ሙስሊም የዘገቡት ነው።
4 ፡ ጠዋፍ (ካዕባን መዞር) ፦ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ካዕባን መዞር (ጠዋፍ) ክልክል ነው። ቡኻሪ በዘገቡት ሃዲስ ላይ ነብዩ አዒሻን ሃጅ ላይ የወር አበባሽ ሲመጣባት፤ ጠዋፍ ብቻ ሲቀር ሁጃጆች የሚሰሩትን በሙሉ ፈፅሚ) ብለዋታል ።
ከዚህ ውጭ ያሉት ነገሮች በዓሊሞች መካከል የሃሳብ ልዩነት ያለባቸው ሲሆኑ ወደ ፊት በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን ኢንሻ አላህ። ወላሁ አዕለም!!
© ተንቢሀት