Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አጥር አለ! (የመጀመሪያ ክፍል)



አጥር አለ!
(የመጀመሪያ ክፍል)
.
አጥር አለ!
አዎን አጥር አለ - የማይነቀንቁት፤ ግንብም አለ የማይንዱት!!!
.
የት?
በነማን መሀል?
ለምን?
እስከምን?
.
.
መቼም የሰሞኑ ሙቀት ያላተራመሰው ጉድ የለም። የፓለቲካው ውዝዋዜ ያልነቀነቀው ርእስ ጥቂት ነው። ታዲያ በዚህ የምርቃና ሰሞን ከነፈሰ የሚነፍሰውም ሆነ አቋም አለኝ ባዩ ሲንገዳገድ አይተናል። እንኳንስ ዘንቦብሽ የሆነው ይቅርና ወትሮ ቀጥ ያለ የሚመስለው ሳይቀር ተዘርሯል። ጥቂት ሲቀር!
.
የግምቡ መፍረስና የድልድዩ መገንባት ለፓለቲካ ሽብሸባ ብቻ ካልሆነ እና በዘር የተናቆረውን ካስታረቀ እሰየው የሚያስብል ነበር። ዳሩ ዶማው የዘረኝነትን ድልብ ከማፍረስ ይልቅ ወደእኛ ግንብ ፊቱን ማዞሩ ነው! (ይህ ከማህበረሰቡ ምላሽ አንፃር ነው)
.
እኛ ማን ነን? .... ሙስሊሞች!
ግንባችን ምንድን ነው ..... እምነታችን!
.
.
#እንዴት ነው ነገሩ?
.
ኢስላም ከውድቅ ሀይማኖቶች የሚለየው እምነቱን በጠራ ሰማያዊ ማስረጃ ላይ ማስደገፉ ነው። ሰው ለምን እንደተፈጠረ አውቆ በፈጠረውም ጌታው ላይ ጥርት ያለ እምነት ይዞ ዘልአለማዊ ደስታ የሚገኝበትን ጀነት ይሸለም ዘንድ አጭር የዱኒያ እድሜውን ለጌታው ፍላጎት የሚሰጥበት ሀይማኖት ነው።
.
እናም ሁሉ ነገር ጠፊ በሆነባት አለም ሙስሊም ወደዚያኛው ሀገር ይዞት የሚሄደው ብቸኛ አንጡራ ሀብቱ ኢማኑ ነው። በጠራ ዕውቀት፣ በትክክለኛ ግንዛቤ እና በሚችለው ተግባር የመሰረተው እንደሆነ ከጀሀነም እሳት መጠበቂያ ጋሻው ነው።
.
ሆኖም ያለፈተና ሽልማት ያለትግል ስኬት የለምና ሙስሊም በመንገዱ ላይ የሚያሳስቱት፣ አቅጣጫ ለማስቀየርና ለመቀልበስ የሚሞክሩት ብዙ ናቸው።
.
አላህ የሰው ልጅ በርሱ አምኖና እርሱን ተገዝቶ ቃል የገባለትን ጀነት ይሸልመው ዘንድ ከአሳሳቾች ራሱን እንዲጠብቅ የኢማኑን መጠበቂያ አጥር አበጅቶለታል።
.
ማንም ሰው የአንድን ሙስሊም አጥር ሳይሻገር እምነቱን አያስቀይረውም ወይም ከእምነቱ አያንሸራትተውም፣ ከጌታውም አያጣላውም። እናም ሙስሊም እምነቱን ለመጠበቅ አጥሩን ሊጠብቅ ይገባዋል!
.
.
#አጥሩ ምንድን ነው?
.
አጥሩ የአንድን ሙስሊም እምነት ከከሀድያን ሰርጎ ገብ ጥቃት የሚታደግ፣ ሙስሊሙ ህልውና አስጠብቆ፣ ማንነቱን አስከብሮ፣ የበላይነትን ተጎናፅፎ የሞራል ልእልና ኖሮት እንዲዘልቅ የሚያደርገው ነው። በርግጥ አጥሩ በራሱ ከእምነት መሰረቶች አንዱ ነው። 'ወላእ ወልበራእ' ይባላል በዓረብኛው ... (ለአላህ ሲባል) መውደድ እና መጥላት ... በሉት በግርድፉ!
.
.
#ለመሆኑ 'ወላእ እና በራእ' ምንድን ነው?
.
የ'ወላእ' ጥሬ ትርጉሙ ... ውዴታ፣ ቅርበት ድጋፍ እንደማለት ነው።
.
ወላእ ... በሸሪዓችን ሙእሚኖችን ለእምነታቸው ሲባል መውደድ፣ መምከር፣ መደገፍ፣ ማዘን፣ ማገዝ እና ከዚህ ጋር የሚያያዙ የአማኞችን መብት ማሟላት ይመለከታል።
.
'በራእ' ... ስንል ደግሞ አንድን ነገር መለየት እና መራቅ ይመለከታል። ሸሪዓችን በ'በራእ' የሚፈልግበት ኢ-አማንያንን (ካፊሮችንና ሙናፊቆችን) በጥቅሉ መጥላትና ከእነርሱ መራቅን ነው።
.
.
#ታዲያ ወላእ እና በራእ አጥርነቱ ምኑ ላይ ነው?
.
እንዲህ ነው ... አንተ የምትወደውን ትመስላለህ፣ የምትጠላውን ትቃረናለህ። ይህ ሰውኛ ባህሪ ነው። የምትወደውን ከመሰልክ ዘንዳ ወዳጅህ ያንተን ማንነት ቀራጭ ይሆናልና እምነትህን በተዛባ መሰረት ላይ አስቀምጦ ከጌታህ እንዳያጣላህ ፈጣሪህ የመረጠልህን እምነት በትክክለኛው መስመር የሚከተል ቀናኢ ሰው ለወዳጅነት መምረጥ አለብህ።
.
የመረጥከውን ሙእሚን ስትወዳጅ ያንተን እምነት እንደምታጠነክረው ሁሉ የእሱንም ታበረታለህ፤ ለተመልካችም ጥሩ ምሳሌ ትሆናለህ። ይህም እርስበርስ መዋደድን ያመጣልሀል፤ ይህን ተከትሎ መደጋገፍ፣ መረዳዳትና መመካከርህ አንድነትን ይመሰርታል።
.
ካፊር በወዳጅነት ተከልሎ ከእምነትህ ሊያስጥልህ ስለማይቻለው በጉልበት ቢመጣ አንድነትህ መከታ ይሆናል - ሰበቡን አድርሰሀልና በጌታህ ጥበቃ ስር ትሆናለህ!
.
ያን በጌታው የካደን ሰው መጥላትህ ደግሞ ለእምነቱ ስትል ነውና ከሰውየው በመወዳጀት ከሚመጣብህ የእምነት መበከል ትድናለህ። ለጌታህ ያልተመለሰ ላንተ አይተኛምና ሴራውንና ተንኮሉን ነቅተህ እንድትጠብቅ ይረዳሀል። እሱን ለመቀናቀን በምታደርገው ትግል የበላይነትን እንድትጎናፀፍም ያደርግሀል።
.
በአላህ የካደን ሰው ስትርቀው በመገፋቱ ተከፍቶ፣ በበታችነቱ ተቆጭቶ፣ ያጣውን ለማግኘት ሲባዝን ሙስሊሞች እርስበርስ ባላቸው መዋደድ ተስቦ እስልምናን እንዲቀበል እና ፍቅሩ እንዲደርሰው እንዲመኝ ታደርገዋለህ።
.
አንተም ለተመልካች መልካም ምሳሌን በመሆን መወገንህ ከማን ጋር መሆን እንዳለበት ታሳይበታለህ። አላዋቂዎች በከሀድያን እንዳይጠለፉ ሞዴል ትሆናቸዋለህ።
.
ይህን ስታደርግ ላንተም ሆነ ለሌላው ዲንህን ከቀማኛ የምትጠብቅበት ብርቱ አጥር ይኖራል። አጥርህ የተነቀነቀ ቀን እንደተደፈርክ ግንቡ የተናደ እንደሁ እምነትህን ለጠላት አሳልፈህ እንደሰጠህ ቁጠረው ... ይኸው ነው!
.
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ...
.
" المرء على دين خليله ، فلينظر أحدكم من يخالل " أخرجه أحمد
.
"ሰውየው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። አንደኛችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ያስተውል" አህመድ ዘግበውታል
.
.
#ይህን ነገር በሸሪዓ ምን ያክል ደረጃ አለው? ፤ ማንን እና እንዴት እንወዳጅ? ማንንስ እንዴት እንጥላ? .... የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን ... ኢንሻ አላህ በቀጣይ ክፍሎች እናያቸዋለን!
.
Share ማድረግ አይዘንጉ

Mohammed Ibrahim Ali

Post a Comment

0 Comments