Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አጥር አለ! (ሁለተኛ ክፍል)



አጥር አለ! - 2
(ሁለተኛ ክፍል)
.
.
[በመጀመሪያው ክፍል ስለ እምነታችን አጥር/ወላእ እና በራእ/ ምንነት እና ፋይዳ አይተን ነበር። (ካላነበቡት በዚህ ሊንክ ያገኙታልhttp://bit.do/ewmkz ) በዚህ ክፍል ደግሞ ሸሪዓችን ለወላእና በራእ የሰጠውን ቦታ እንዲሁም ማንን መውደድ እና መጥላት እንዳለብን እናያለን] መልካም ንባብ ....
.
.
.
#ይህ ነገር (ወላእና በራእ) ምን ያክል ደረጃ አለው?
ሑክሙ/ብያኔውስ ምንድን ነው?...
.
ይህ የእምነት አጥር (ወላእና በራእ) ዋጂብ/ግዴታ የሆነ የእምነት መሰረት ነው። እንደውም ዓሊሞች አላህ ከተውሒድ ቀጥሎ እንደዚህ ርእስ ማስረጃዎችን ያዥጎደጎደበት ሑክም የለም ይላሉ።
.
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህ ርእስ ስላለው ከባድ ቦታ ሲናገሩ ይህን ብለው ነበር ...
.
( إِنَّ أَوْثَقَ عُرَى الْإِيمَانِ: أَنْ تُحِبَّ فِي اللهِ، وَتُبْغِضَ فِي اللهِ ) حسنه الألباني في "صحيح الترغيب" (3030)
.
"እጅግ ጠንካራው የእምነት ገመድ ለአላህ ብለህ መውደድህ እና ለአላህ ስትል መጥላትህ ነው"
በሰሒሕ አ'ተርጊብ ላይ አልባኒ ሐሰን ብለውታል
.
.
#ታዲያ ይህ ርእስ ይህን ያህል ከባድ ከሆነ እንዴት እንተግብረው፤ ውዴታና ጥላቻችንን የምናሳርፍበት መለኪያስ ምንድን ነው?
.
ይህን በቀላሉ እንድንረዳው ዓሊሞች የወላእና በራእ ሑክም የሚያርፍባቸውን ሰዎች ለሶስት ይከፍሏቸዋል ...
.
#1ኛ. ሙሉ ውዴታ የሚወደዱ (የማይጠሉ)
#2ኛ. ሙሉ ጥላቻ የሚጠሉ (የማይወደዱ)
#3ኛ. በአንድ ጎን የሚወደዱ በሌላ ጎን ደግሞ የሚጠሉ ናቸው።
በዝርዝር እንያቸው እስኪ ...
.
.
#1ኛ ሙሉ ውዴታ የሚወደዱ (የማይጠሉ)
.
እነኝህ ያለምንም ጥላቻ የምንወዳቸው ንፁህ ሙእሚኖች ናቸው። ከነብያት፣ ከሲዲቆች/እውነተኞች፣ ከሸሂዶች/ሰማእታት እና ከሷሊሆች/ደጋጎች ሲሆኑ፤ ግንባር ቀደሙ ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከዛም የምእመናን እናት የሆኑት ሚስቶቻቸው እና ቤተሰባቸው ናቸው ...
.
እንዲሁም ሶሐቦች በተለይ ኸሊፋዎች፣ ቀሪዎቹ አስሩ ተበሳሪዎች/ዓሽረል ሙበሸራ/፣ ሙሐጂሮች፣ አንሳሮች፣ የበድር ሰዎች፣ የበይዓቱ'ሪድዋን ጓዶች፣ ቀሪዎቹም ሶሐቦች በአጠቃላይ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ይከተላሉ።
.
በመቀጠልም የሶሐባ ተከታይ ትውልዶች (ታቢዒዮች)፣ በላጮቹ የዚህ ኡማ ቀደምት ትውልዶች (ሰለፎች) እና እንደ አራቱ ኢማሞች ያሉ የኡማው መሪዎችም በሙሉ ልብ የሚወደዱ ናቸው።
.
ይህ ውዴታ በነኝህ ላይ ብቻ የሚያጥር ሳይሆን የእነርሱን ፈለግ በተከተለ እና በነርሱ መንገድ ላይ ባለ ሙእሚን ላይ ሁሉ የሚያርፍ ነው።
.
إِنَّمَا وَلِيُّكُمُ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُمْ رَاكِعُونَ () وَمَن يَتَوَلَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا فَإِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْغَالِبُونَ ( المائدة 55-56)
.
"ረዳታችሁ (ወዳጃችሁ) አላህና መልክተኛው፣ እነዚያም ያመኑት ብቻ ናቸው፤ (እነርሱ) እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ፣ እነርሱም ያጎነበሱ ሆነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው (-) አላህንና፣ መልክተኛውን እነዚያንም ያመኑትን የሚወዳጅ ሰው፣ (ከአላህ ጭፍሮች ይሆናል)፤ የአላህም ጭፍሮች እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው። (አል-ማኢዳ 55-56)
.
.
#2ኛ ሙሉ ጥላቻን የሚጠሉ (የማይወደዱ)
.
እነኝህ ያለምንም ውዴታ የምንጠላቸው ካፊሮች ናቸው። ሙሽሪኮች፣ ሙናፊቆች፣ ሙርተዶች (ከእስልምናን የወጡ) እንዲሁም ሀይማኖት የለሾች በሙሉ የትም ዜግነት ምንም ዘር ይሁኑ ሁሉንም ሙሉ ጥላቻን የምንጠላቸው እና የማንወዳጃቸው ናቸው።
.
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَكُمْ هُزُوًا وَلَعِبًا مِّنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ وَالْكُفَّارَ أَوْلِيَاءَ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ (المائدة 57
.
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፍን ከተሰጡት፤ እነዚያን ሃይማኖታችሁን ማላገጫና መጫወቻ አድርገው የያዙትን ከሐዲዎችን ወዳጅ አድርጋችሁ አትያዙ፤ ምእመናንም እንደሆናችሁ አላህን ፍሩ" አል-ማኢዳ 57
.
.
#3ኛ በአንድ ጎን የሚወደዱ በሌላ ጎን የሚጠሉ
.
እነኝህ ውዴታ እና ጥላቻ የሚጣመርባቸው ሃጢአተኛ የሆኑ ምእመናን ናቸው። ባላቸው ኢማን ልክ ይወደዳሉ ከሽርክ በታች ባለባቸው ወንጀል ልክ ይጠላሉ።
.
መወደዳቸው እንዲመከሩ እና ወንጀላቸው እንዲወገዝ ያስደርጋል እንጂ ከነስህተታቸው ዝም እንዲባሉ አያደርግም። ይመከራሉ፣ በመልካምም ይታዘዛሉ እስኪመለሱ ድረስ። ይሁንና ልቅ የሆነ ውዴታም ሆነ ጥላቻ አያርፍባቸውም።
.
እዚህ ጋር ዓሊሞች ስለሙብተዲዖች ያክላሉ። እነኝህ በዲን ላይ ከርሱ ያልሆነውን የጨመሩ አካላትን ይከፋፍሏቸዋል። ቢድዓቸው ከኢስላም የሚያስወጣ ሙከፊራ ከሆነ ሑክማቸው የካፊር ሑክም ነው ይላሉ። (ይህ የሚሆነው ግን ሑጃ ሲቆምባቸው ወይም መዋኒኡ ተነስቶ ሸርጥ ሲሟላ ነው)
.
በሌላ በኩል ቢድዓው ከኩፍር በታች የሆነ ሰው ወደ ቢድዓው የሚጣራ ከሆነ በቢድዓው ልክ እንደሚጠላ ሆኖም ቢድዓውን ወደ ንፁሀን እንዳያጋባ እንደሚገለል ዓሊሞች ያስቀምጣሉ።
.
ወደ ቢድዓው የማይጣራ፣ የማያዳንቅ ከሆነ ወይም ቢድዓውን የማያስተዋውቅ ከሆነ ግን እንደማይገለል ይመክራሉ።
.
.
አሁን አሁን ግን ነገሮች በተቃራኒያቸው እየሄዱ ነው። ሰዎች ሌሎችን የሚወዱት ለኢማናቸው ሲሉ ሳይሆን ለዱኒያ ሲሉ ሆኗል። አንዳቸው ሌላቸውን የሚወዱት የነርሱ ዘር ስለሆነ፣ የሚወዱትን ፓለቲካ ስለሚያራምድ፣ በገንዘብ ስለሚደግፋቸው፣ በሙያው ስለሚያስፈልጋቸው፣ ባህሪውን ስለወደዱለት ወይም ለሌላ ጥቅማ ጥቅም እንጂ ስለ እምነቱ ቅንጣት ማሰብ አቁመዋል። ጥቂት ጥንቁቆች ሲቀሩ!
.
እንዳውም ዛሬ ብዙዎች በኳስ፣ በፊልም፣ በዘፈን እና መሰል ጊዜ ገዳይ እና ሐራም ተግባራት የሚሸነግላቸውን ካፊር በመጥላት ፈንታ መውደድ ስራቸው አርገውታል።
.
ከሙስሊም መሀል ወደዱ ከተባለም በቢድዓ የተነከረውንና የነቢዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱና ገሸሽ አድርጎ በስሜቱ የሚነጉደውን እንጂ ማንን በምን ልክ መውደድ እንዳለባቸው እንኳ አያስተውሉም።
.
ይህ ግን ዋጋ ያስከፍላል፤ አስከፍሏልም። ያለቦታ የተቀመጠው ውዴታው በራሱ ወንጀልነቱ ከባድ ሆኖ ሳለ እርሱን ተከትሎ የሚመጣው ጥፋት እንጥፍጣፊ ኢማን እስከማይቀር ድረስ ሰውየውን ከመንገድ ሊያወጣው ይችላል።
.
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ (-) هَا أَنتُمْ أُولَاءِ تُحِبُّونَهُمْ وَلَا يُحِبُّونَكُمْ وَتُؤْمِنُونَ بِالْكِتَابِ كُلِّهِ وَإِذَا لَقُوكُمْ قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا عَضُّوا عَلَيْكُمُ الْأَنَامِلَ مِنَ الْغَيْظِ ۚ قُلْ مُوتُوا بِغَيْظِكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ (-) إِن تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا بِهَا ۖ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ إِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ (ال عمران 118-120)
.
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ። ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። በልቦቻቸዉ የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን (-) ..."
.....
"እነሆ እናንተ እነዚያ የምትወዱዋቸዉ ናችሁ። (እነሱ) ግን አይወዷችሁም ..."
.....
"በመፅሐፉም በሁሉም ታምናላችሁ፤ ባገኙዋችሁም ጊዜ አምነናል ይላሉ። ባገለሉም ጊዜ ከቁጭታቸዉ የተነሳ በናንተ ላይ ዐጥቆቻቸዉን ይነክሳሉ፤ በቁጭታችሁ ሙቱ፤ አላህ ልቦች የቋጠሩትን ዐዋቂ ነዉና በላቸዉ (-) ..."
....
"ደግ ነገር ብትነካችሁ ታስከፋቸዋለች። መጥፎም ነገር ብታገኛችሁ በርሷ ይደሰታሉ። ብትታገሡና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸዉ ምንም አይጐዳችሁም። አላህ በሚሠሩት ሁሉ (በዕዉቀቱ) ከባቢ ነዉና"
አሉ ዒምራን 118-120
.
#ሱብሐን አላህ! ግን ከአላህ በላይ አሳምሮ መካሪ ማን አለ?
.
የሚገርመው መጥላት ያለብንን ጠልተን የእምነት አጥራችንን እንደማጠንከር ዛሬ በጥላቻ የምንበረታበት ሙስሊሙን ያውም ፈተና በበዛበት ግዜ ዲኑ ላይ የተገኘውን ሁኗል። እንኳን ወደነው ሀቁን ልናሟላ ይቅርና ውገናችን ለመጤ እሳቤና ቢድዓ ሁኗል።
.
የእምነት አጥራችንም ሳስቶ ትንሽ ነው እያልን ሲገቡ በታገስናቸው የቢድዓ ቡችላዎች ተከፋፍቶ ዛሬ በተቦዳደሰ አጥር ተከበን ቁጭ ብለናል።
.
ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንዲሉ እነሆ በትንሽ በትልቁ ሲበሳሳ የከረመው አጥራችን ያገጠጠ ኩፍር አስሾልኮ ከደጃፋችን አቁሟል። ገና በእንቁላሉ ሳለ ሀግ ካላልነው ነገ በሬ እየጎተተ ሲመጣ ታፍሰን መከተታችን ነውና እንንቃ!
.
.
[#መንቃት አለብን! ከነቃን በኋላስ?
ትክክለኛው ወዳጅነት በምን ይገለፃል? የተከለከለውስ?
#ለመሆኑ ከካፊሮች ጋር አብረን ስንንኖር መጠንቀቅና መፈፀም ያለብንስ ምን ምንድን ነው? ....
#በቀጣይ ክፍሎች ኢንሻአላህ!]
.
.
Share ማድረግ አይዘንጉ!
 

Post a Comment

0 Comments