Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ክረምቱን እንጠቀምበት

ክረምቱን እንጠቀምበት
ክረምቱን ነፃ የሆናችሁ ተማሪዎችና መምህራን በምትችሉት አቅም ጊዜያችሁን ስለዲናችሁ በመማር አሳልፉት፡፡ የሚያስተምራችሁ ካጣችሁ በድምፅ የተለቀቁ ትምህርቶችን በማዳመጥ፣ ቁርኣን በመሐፈዝ፣ መፃህፍትን በማንበብ እራሳችንን እንለውጥ፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያሳውቀዋል፡፡” ባይሆን የወላጆችን ሐቅ በማይጋፋ መልኩ መሆኑ እየተስተዋለ፡፡
ማስተማር የምትችሉ ደግሞ ያላችሁን በማካፈል ላይ ተጠመዱ፡፡ ቁርኣን በደንብ የያዘ እሱን ያስተምር፡፡ ዛሬ ዛሬ ነብዩ ﷺ “ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው” ማለታቸውን ብዙዎቻችን ትኩረት ነፍገነዋል፡፡ አጫጭር የተውሒድ ኪታቦችን የቀራ ሰው ያንኑ ያካፍል፡፡ ደዕዋ ማድረግ የሚችል በተለይም በገጠር አካባቢ አቅሙ በሚችለው ሰዎችን ያስተምር፡፡
ወላጆች ልጆቻችሁ ክረምቱን ባግባቡ እንዲጠቀሙ አግዙ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚሰጡ መድረሳዎች ካሉ ልጆቻችሁ፣ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻችሁ እዚያ እንዲከታተሉ አድርጓቸው፡፡
አስተማሪዎች አመቱን ሙሉ እንደ ልብ የማታገኙት ሙስሊም እንዳለ አስባችሁ የተሻለ ጥረት ለማድረግ ተንቀሳቀሱ፡፡ ነብዩ ﷺ “ወደ መልካም የሚያመላክት እንደሚተገብረው ሰው ነው” ማለታቸው ይታወስ፡፡ አላህ ሁላችንንም ያግዘን፡፡


Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments