Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

 
 
#ሙስሊሞች ሆይ #ጽኑ
#ዲናችሁ ላይ #ቀጥ በሉ
★ዲን ልብስና ስም ብቻ አይደለም
★ሐይማኖታችን እምነትና ተግባር ነው
★ዘመናችን ኣኺር ዘመን በመሆኑ በሁሉም የህይወታችን መስኮች ላይ ፈተናዎች
እየበዙ ነው
★ሐቅን/መብትን እንኳ ለማግኘት ካልዋሸህ/ሽ እና ካላጭበረበርክ/ሽ መኖር አይቻልም የሚሉ በርካቶች ናቸው
★ትክክለኛ አማኝ እዚህ ጋር ነው የሚፈተነው በሰላም ጊዜ ሁሉም ዲኑን ሊያከብር ይችላል
ሲቸገሩ ዲንን መጠበቅ ግን ጥቂት የአላህ ባሮች እንጂ ብዙዎች የማይደርሱት
ማዕረግ ነው
★እውነተኛ ሙእሚን ነገሮች ቢደራረቡበትና በሮች ሁሉ ቢዘጋጉበትም እምነቱ የማይፈቅደውንና ጌታው የሚጠላውን ነገር
አይዳፈርም አስተዋይ ሙእሚን ጉዳዮቹ ሲወሳሰቡበትና በሮች ሲዘጋጉበትም ወደ ጌታው እንጂ የሚጮኸው ዲኑ የማይፈቅደውን ነገር በማድረግ ከችግሮቹ
ለመውጣት አያስብም!
★ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ( "የትም ብትሆን አላህን ፍራ") ብለዋል፣በሁሉም ሁኔታ፣ቦታና ዘመን ላይ አላህን ከልባችን ልንፈራ ባመንበት ነገር ላይ ልንጸና ይገባናል
★ኣኺር ዘመን ላይ (በዲኑ ላይ የጸና የ50 ሰሓባ አጅር እንደሚሰጠው) ነቢያችን የተናገሩት በእንዲህ ዓይነቱ ዘመን ላይ ሁሉን ነገር ተቋቁሞ ዲን ላይ ቀጥ ማለት እሳትን የመያዝ ያክል ስለሚከብድ ነው::
አሕመድ ሼኽ ኣደም
ሸዋል 17/1439 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

Post a Comment

0 Comments