የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን መቅራት ይፈቀድላታልን?
በመጀመሪያ “ይፈቀዳል” ወይስ “አይፈቀድም” በሚለው ላይ የዑለማዎች ልዩነት እንዳለ ይታወቅ፡፡ እንዲያውም ብዙሃን ዑለሞች እንደማይፈቀድ ነው የሚገልፁት፡፡ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን መቅራት አትችልም ያሉ ምሁራን ሁለት መነሻዎች አሏቸው፡፡ እነሱም፡-
አንዱ፡- “የወር አበባ ላይ ያለች ሴትና ጀናብተኛ ከቁርኣን ምንም አይቀሩም” የሚለው ሐዲሥ ሲሆን
ሁለተኛው፡- የጀናብተኛን ሁኔታ ቂያስ በማድረግ ነው፡፡ “ሁለቱም ትጥበት ወጅቦባቸዋል፤ ጀናብተኛ መቅራት ካልተፈቀደለት የወር አበባ ላይ ያለችዋም አይፈቀድላትም” የሚል ንፃሬ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት መነሻዎች ጤነኛ ናቸው ወይ? ሌሎችስ ዑለማዎች በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
ይህ አቋም ሚዛን የሚደፋ እንዳልሆነ በመግለፅ “የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን እንዳትቀራ የሚከለክላት የለም” የሚሉ ዑለማዎች ቁጥር አንድና ሁለት አይደለም፡፡ “አይፈቀድም” በሚሉ ዐሊሞች የቀረቡት ማስረጃዎችንም ጥንካሬ የሚጎድላቸው እንደሆኑ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ ዐሊሞች በዚህ ረገድ ከሚያነሷቸው ነጥቦች ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1ኛ፡- ከልካዮች ያቀረቡት የሐዲሥ ማስረጃ ደካማ ነው፡፡ በደካማ ሐዲሥ ተንተርሶ በትክክለኛ ማስረጃ ያልተከለከለን ዒባዳ መከልከል አይቻልም፡፡ ሐዲሡን፡-
1.1. ኢማሙ አሕመድ፡- “ውድቅ ነው” ብለውታል፡፡ [ተህዚቡ አትተህዚብ፡ 1/283]
1.2. ኢማሙል ቡኻሪ፡- ደካማነቱን ገልፀዋል፡፡
1.3. ኢብኑ ተይሚያ፡- ሐዲሡን “በሐዲሥ አዋቂዎች ስምምነት ደካማ ነው” ብለዋል፡፡ [አልመጅሙዕ፡ 21/460]
1.4. ኢብኑል ቀይም፡- “በሐዲሥ አዋቂዎች ስምምነት ድክመት ያለበት ሐዲሥ ነው” ብለዋል፡፡ [ኢዕላሙል ሙወቂዒን፡ 3/25]
1.5. ኢብኑ ሐጀር፡- “በሁሉም መንገዶቹ ደካማ ነው” ብለዋል፡፡ [ፈትሑል ባሪ፡ 1/323-324]
1.6. አልባኒ፡- በብዙ ኪታቦቻቸው ሐዲሡ ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ለምሳሌ፡- [ዶዒፉ ሱነን አትቲርሚዚ፡ ቁ. 98]
1.7. ኢትዮጵያዊው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም በዚህ ርእስ ላይ የሚጠቀሱት ሐዲሦች ለማስረጃነት የሚበጁ አይደሉም ብለዋል፡፡ [ዘኺረቱል ዑቅባ፡ 4/570]
ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚንና ሌሎችም በርካታ ዐሊሞች በተመሳሳይ የሐዲሡን ደካማነት ገልፀዋል፡፡
2ኛ፡- ከልካይ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ በጉዳዩ ላይ መሰረቱ ፍቁድነት ነው፡፡ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በዚህ ረገድ ከሌሎች ሙስሊሞች የተለየ ብይን የላትም፡፡ እሷን ከሌሎች ለይቶ ከቁርኣን የሚከለክል ሰው ግልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እንደሚታወቀው የሴቶች የወር አበባ ማየት ከነብዩ ﷺ ዘመን በኋላ የመጣ አዲስ ክስተት ሳይሆን ጥንትም የነበረ ነው፡፡ ሆኖም ግን በዚያን ሰዓት ቁርኣን እንዳይቀሩ አልከለከሏቸውም፡፡ “እንዳልተከለከሉ ምን አሳወቀን?” ከተባለ ልክ የወር አበባ ላይ ሲሆን እንዳይፆሙና እንዳይሰግዱ የሚከለክሉ ትክክለኛ ሐዲሦች እንደደረሱን ቁርኣን እንዳይቀሩ ቢከለከሉ ኖሮም በማያሻማ መልኩ ማስረጃ ይደርሰን ነበር ማለት ይቻላል፡፡
3ኛ፡- አላህ ቁርኣንን በመቅራት አዟል፡፡ ለሚቀራውም ሰው ትልቅ ሽልማትን ሊሸልም ቃል ገብቷል፡፡ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ከዚህ ትልቅ የዒባዳ መስክ መከልከል ልክ አይደለም የሚለው ሌላኛው ይህን ሀሳብ የመረጡ ምሁራን መከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡
4ኛ፡- የወር አበባ ላይ ያለችን ሴት ከጀናብተኛ ጋር ማመሳሰልም ልክ አይደለም፡፡ ጀናባ ያለበት ሰው ምርጫው በእጁ ነው፡፡ ከፈለገ ታጥቦ መቅራት ይችላል፡፡ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ግን ደሙ ሲቆም እንጂ ስለፈለገች አትታጠብም፡፡ በዚያ ላይ ከጀናባ በተለየ የወር አበባ ቆይታ ቀናትን የሚፈጅ ነው፡፡ ስለዚህ ከጀናባ ጋር ማመሳሰሉ ጤነኛ ንፅፅር አይደለም፡፡ የወሊድ ደም ሲሆን ደግሞ ቆይታው የበለጠ ይራዘማል፡፡ ኢብኑል ቀይም “የወር አበባ ላይ ያለች ሴትና ጀናብተኛ ከቁርኣን ምንም አይቀሩም” የሚለው ሐዲሥ ለማስረጃነት የማይበቃ ደካማ እንደሆነ በሰፊው ከተነተኑ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “ሐዲሡ ሶሒሕ ካልሆነ ከልካዮች ዘንድ በጀናብተኛ ከማነፃፀር ውጭ ሌላ ማስረጃ አይቀራቸውም፡፡ በሷና በጀናብተኛ መካከል ያለው ትክክለኛ ልዩነት ሁለቱን አንድ አድርጎ ለመበየን የሚከለክል ነው፡፡ ይህም በብዙ መልኩ ነው፡፡ አንዱ ጀናብተኛ በፈለገ ጊዜ በውሃም ሆነ በአፈር መጥራት (መጧሀራት) ይችላል፡፡ ስለዚህ ከነጀናባው የሚቀራበት ምክንያት የለውም፡፡ የወር አበባ ላይ ያለችው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡” ሌሎችም መለያዎችን ዘርዝረዋል፡፡ ከፈለጉ ሙሉውን ይመልከቱት፡፡ [ኢዕላሙል ሙወቂዒን፡ 3/25]
5፡- የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን እንዳትቀራ ማለት በየወሩ ለተወሰኑ ቀናት ቁርኣንን እንዳትማር፣ እንዳታስተምር፣ በመቅራት አጅር እንዳታገኝ መከልከል ነው፡፡ በዚያ ላይ ሒፍዝ ላይ ከሆነች ለመርሳት ልትጋለጥ ትችላለች፡፡
በመጨረሻም “ለመሆኑ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን መቅራት ይፈቀድላታል ያሉ ዑለማዎች እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ ከተነሳ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡-
★ የማሊኪያ መዝሀብ መቅራት ትችላለች የሚል ነው፡፡ [አዝዘኺራ ሊል ቀራፊ፡ 1/379]
★ የዟሂሪያም አቋም ይሄው ነው፡፡ [አልሙሐላ፡ 1/94] [አልመጅሙዕ ሊንነወዊ፡ 2/357]
★ የአሕመድም አንድ ዘገባ ነው፡፡ [አልኢንሷፍ ሊልመርዳዊ፡ 1/249] [አልኢኽቲያራቱል ፊቅህያ ሊብኒ ተይሚያ፡ 27]
★ ከኢማሙ ሻፊዒይ በዚህ ላይ የሚፈቅድና የሚከለክል ሁለት የተለያዩ እይታዎች የተላለፉ ሲሆን አንዳንዶች የሚፈቅደው የቀድሞ አቋማቸው ነው ብለዋል፡፡
★ የኢብኑ ጀሪር አጥጦበሪ ምርጫም መቅራት ትችላለች የሚለው ነው፡፡ [ሸርሑ ሶሒሕ አልቡኻሪ ሊብኒ በጥጧል፡ 1/423-424] ቡኻሪ፣ ኢብኑል ሙንዚርና ሸውካኒም ይህንኑ መርጠዋል፡፡ የኢብኑ ተይሚያና የኢብኑል ቀይም አቋም ይሄው እንደሆነም አሳልፌያለሁ፡፡
ከዘመናችን ታላላቅ ዑለማዎች ውስጥ የጥቂቱን ንግግር ላቅርብ፡-
★ ኢብኑ ባዝ፡- “የወር አበባ ላይ ላለች ሴት ቁርኣን መቅራት ይፈቀድላታል፡፡ ከዚህ የሚከለክል ግልፅ ማስረጃ ስለሌለ፡፡ ነገር ግን ሙሥሐፍ (ቁርኣን) ሳትነካ ነው፡፡ ‘የወር አበባ ላይ ያለች ሴትና ጀናብተኛ ከቁርኣን ምንም አይቀሩም’ የሚለው ሐዲሥ ደካማ ነው” ብለዋል። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ባዝ፡ 16/127]
★ ኢብኑ ዑሠይሚን፡- “የወር አበባ ላይ ላለች ሴት ሐጃ ሲኖር ካልሆነ በስተቀር በአንደበቷ ባትቀራ #በላጭ ነው፡፡ ለምሳሌ አስተማሪ ሆና ተማሪዎችን የምታቀራ ከሆነች ወይም በፈተና ጊዜ ተማሪዋ ለፈተናዋ መቅራት ካስፈለጋትና መሰል ጉዳዮች” ብለዋል። [መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል ኢብን ዑሠይሚን፡ 11/234] ልብ በሉ! ከውዝግብ ለመራቅ ያክል የሰጡት ምክር እንጂ መከልከላቸው አይደለም፡፡ “ባትቀራ #በላጭ ነው” አሉ እንጂ “መቅራቷ ሐራም ነው” አላሉም፡፡
★ የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ዑለማዎች፡- “የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ሙስሐፍ ሳትነካ ቁርኣን መቅራቷን በተመለከተ ከሁለቱ የዑለማዎች አቋም ትክክለኛው ችግር የለበትም የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ይህንን የሚከለክል በተጨባጭ አልተገኘምና” ብለዋል፡፡ [ፈታወልለጅነቲ አድዳኢማህ፡ ቁ. 3713] ፈትዋዉን የሰጡት ኢብኑ ባዝ፣ ዐብደላህ ኢብን ቀዑድ እና ዐብዱርረዛቅ ዐፊፊ ናቸው፡፡
★ ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ፡- “የወር አበባ ላይ ያለችን ሴት ከሒፍዟ ቁርኣን እንዳትቀራ የሚከለከል ማስረጃ አናውቅም” ብለዋል፡፡ [ሸርሑ ሱነን አቢ ዳውድ]
★ ኢትዮጵያዊው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም እንዲሁ መቅራት እንደምትችል አስፍረዋል፡፡ [ዘኺረቱል ዑቅባ፡ 4/570-571]
★ አልባኒና ፈርኩስም ይህንኑ መቅራት ትችላለች የሚለውን ሀሳብ ከመረጡ ዐሊሞች ውስጥ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
እስካሁን የተወራው ቁርኣንን በእጅ ሳይነኩ በቃል መቅራትን እንጂ ሙስሐፍ መንካትን የሚመለከት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እንደ ሞባይል ካሉ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን የቁርኣን አፕሊኬሽን ተጠቅሞ መቅራት እንደሚቻል በርካታ የዘመናችን ዑለማዎች ገልፀዋል፡፡ ወልላሁ አዕለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 19/2010)

0 Comments