Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውዱእ ሳይኖር ከሞባይል አፕሊኬሽን ቁርኣን መቅራት ይቻላልን?


ውዱእ ሳይኖር ከሞባይል አፕሊኬሽን ቁርኣን መቅራት ይቻላልን?
ሞባይል፣ ታብሌትና ኮምፒዩተር ላይ የተጫኑ የቁርኣን ሶፍትዌሮች የሙስሐፍ (ሀርድ ኮፒ ቁርአን) ብይን እንደሌላቸው ዑለማዎች ይገልፃሉ።
ስለዚህ ቁርኣን ያለ ውዱእ እንዳይነካ የሚለው ሙስሐፍን የሚመለከተው ብይን በነዚህ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን ቁርኣን አይመለከትም። ስለሆነም በነዚህ ዲቫይሶች የሚገኘውን ቁርኣን ተጠቅሞ ውዱእ ባይኖርም መቅራት ይቻላል። የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴትም በነዚህ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን ተጠቅማ ቁርኣን መቅራት ትችላለች።

Post a Comment

0 Comments