

① የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች
②ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች
③ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች
④ቤትና ንብረቱን እንዲሁም ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች
⑤እሱ የማይፈልገውን ሰው አትጠጋም አታስጠጋምም
⑥ ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም ከቤትም አትወጣም
⑦ የባሏንና የቤቷን ሚስጥር በሚገባ ትጠብቃለች
⑧ ባሏን በመልካም ነገር ላይ ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣ ሲረሳ ታስታውሳለች
⑨ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች
①∅ ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥ እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም
①①በሚያደርግላት ነገር በሙሉ ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች
①② ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!
①③ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች በቃ

"ሁላችንም አላህ ሳሊሖች ያድርገን"

6/8/1439ዓሂ
@ዛዱል መዓድ
0 Comments