ከሸዕባን 15 በኋላ መፆም
ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆምን በተመለከተ በዑለማዎች ሁለት አይነት ሀሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡
አንደኛው ወገን፡- መፆሙን የሚከለክሉ ናቸው፡፡ በርካታ ሻፍዕያዎች ይህንን አቋም መርጠዋል፡፡ ማስረጃቸውም፡-
“ሸዕባን ሲጋመስ እንዳትፆሙ” የሚለው ሐዲሥ ነው፡፡ ሐዲሡን አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጃህና ሌሎችም ዘግበውታል፡፡

ሌላኛው ወገን፡- ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም ይቻላል የሚሉ ናቸው፡፡ ይሄኛው ምርጫ የብዙሃን ዑለማዎች ምርጫ ነው፡፡ ማስረጃዎቻቸው፡-
1. አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ረመዳንን በአንድ ቀን ፆም ወይም በሁለት ቀን ፆም አትቀደሙት፡፡ የተለመደን ፆም የሚፆም ሰው ቢሆን እንጂ፡፡ እሱ ግን ይፁም” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይሄ ሐዲሥ ረመዳን ሊገባ አንድና ሁለት ቀን እስከሚቀረው ድረስ መፆም እንደሚቻል ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ ከሸዕባን አጋማሽ ጀምሮ ረመዳን ሊገባ አንድና ሁለት ቀን እስከሚቀረው ድረስ መፆም ይቻላል ማለት ነው፡፡ ቀድሞ ካስለመደው ፆም ጋር የገጠመለት ሰው ግን ከረመዳን በፊት ያለውን አንድና ሁለት ቀንም ጭምር መፆም ይችላል፡፡
2. እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡- “ነብዩ ﷺ ከረመዳን በስተቀር ሙሉ የፆሙት ወር የለም፡፡ እንደ ሸዕባን ፆም ያበዙበት አላየሁም፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] በሌላ የሙስሊም ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብላለች፡- “ሸዕባንን ጥቂት ሲቀር እንዳለ ይፆሙት ነበር፡፡”
3. እናታችን አሙ ሰለማ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡- “ነብዩን ﷺ ሁለት ወሮችን አከታትለው ሲፆሙ አላየሁም፣ ሸዕባንና ረመዳንን ቢሆን እንጂ፡፡” አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1025] እዚህ ላይ የሸዕባንን አብዛኛውን ለማለት እንጂ ሙሉ ለማለት አይደለም፡፡ በዐረብኛ በዚህ መልኩ መግለፅ የተለመደ ነውና ይላሉ ዑለማዎች፡፡
እነዚህ ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም ይቻላል የሚሉ ዓሊሞች የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከተጠቀሱት ውጭ ሌሎችም ማስረጃዎች አሉ፡፡
ግን ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም አይቻልም የሚሉ አካላት ያቀረቡትን “ሸዕባን ሲጋመስ እንዳትፆሙ” የሚለውን ሐዲሥ በተመለከተ “መፆም ይቻላል” የሚሉት ዓሊሞች ምን አሉ?
1. ከፊሎቹ ሐዲሡ ደካማ ነው ሲሉ ዘግተዋል፡፡ ኢማሙ አሕመድ፣ ኢብኑ መዒን፣ አቡ ዙርዐህ፣ ዐብዱርረሕማን ኢብን መህዲ፣ በይሀቂ እና ሌሎችም ሐዲሡ “ሙንከር ነው” በማለት ደካማ እንደሆነ ከገለፁት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
2. ከፊሎቹ መልእክቱ የተገደበ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ሐዲሡን ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ሒባንና ኢብኑ ማጃህ ሶሒሕ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ኢብኑ ሐዝም፣ ኢብኑል ቀይምና ሸይኹል አልባኒ ሐዲሡን ደካማ ነው ያሉትን ጠንከር አድርገው ሞግተዋል፡፡ ሆኖም ግን የሐዲሡ መልእክት ከነጭራሹ ከሸዕባን አጋማሸ በኋላ መፆምን ለመከልከል ሳይሆን ቀድሞ ልምድ ሳይኖረው ወይም በወሩ የመጀመሪያ አጋማሽ ምንም ሳይፆም ከሁለተኛው አጋማሽ በኋላ የሚፆምን ነው የተከለከለው ይላሉ፡፡ ኢብኑ ባዝ፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድና ሌሎችም ይህንን ሀሳብ ከደገፉት ውስጥ ናቸው፡፡
3. ከፊሎች ደግሞ በሐዲሡ ውስጥ የተገለፀው ክልከላ ሐራምነት የሚደርስ ሳይሆን እንደማይበረታታ ለመጠቆም ነው ይላሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለረመዳን ፆም መዳከም እንዳይከተል ለማሳሰብ ነው ይላሉ፡፡ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ሐዲሡ ሶሒሕ እንኳን ቢሆን ክልከላው ሐራምነት አይደርስም ይላሉ፡፡ ቃሪም ይህንን ሀሳብ መርጠዋል፡፡

ሲጠቃለል፡-
1. የሚከለክለውን ሐዲሥ አብዛኞቹ ዑለማዎች ደካማ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ከላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች መነሻ በማድረግ በሁለተኛው የሸዕባን አጋማሽ ውስጥ መፆም እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
2. ነገር ግን የመጀመሪያው አጋማሽ ውስጥ ያልፆመ፣ ሰኞና ሐሙስ ወይም መሰል ልምድ የሌለው እንዲሁ ከሸዕባን አጋማሽ ጀምሮ ለመፆም ባይነሳ የተሻለ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከልካዩን ሐዲሥ “ሶሒሕ ነው” የሚሉ ዓሊሞች ትንታኔ ጠንከር ያለ ስለሆነ ከሸዕባን 15 በኋላ ያለምንም መነሻ ፆም በመጀመር እራሳችንን ኺላፍ ውስጥ ከማስገባት ልንቆጠብ ይገባል፡፡
3. ሰኞና ሐሙስ ወይም ሌላ ያስለመደው ፆም ያለው ሰው፣ በመጀመሪያ የሸዕባን አጋማሽ ውስጥ ሲፆም የነበረ እና መሰል ምክንያቶች ያሉት ሰው ፍላጎቱ ከሆነ በሁለተኛውም አጋማሽ መፆም ይችላል፡፡ ወልላሁ አዕለም።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 26/2010)
0 Comments