Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ የሁሉም ነብያት ተልዕኮ


ተውሂድ የሁሉም ነብያት ተልዕኮ
አምላካችን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በተለየዩ ዘመናት በርካታ ነቢያትን ልኳል፡፡ እነዚያ ነብያትም ሲተገብሩትና ለተላኩላቸው ሕዝቦች ያስተምሩ የነበረው የአላህን ብቸኛ አምላክነት የሚያብራራውንና ባእድ አምልኮን መራቅ እንዳለብን የሚገልፀውን (ተውሂድ አል ኡሉሂያ) የተሰኘውን የተውሂድ ክፍል እንደነበረ በቅዱስ ቃሉ በቁርአን ይነግረናል፡፡
” وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ “
النحل: ٣٦
‹‹ በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ » በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡››
(አል ነህል 36)
በሱረቱል አንቢያ ውስጥም አላህ ወደየህዝቦቻቸው ስለላካቸው መልዕክተኞች ለነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲገልፅላቸው እንዲህ ይላል፡-
” وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ “
الأنبياء: ٢٥
‹‹ ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ ›› ይላል።
(አል አንቢያ 25)
በመሆኑም በየዘመናቱ ወደ ሕዝቦቻቸው የተላኩ ነቢያት ተልእኳቸው የአምልኮ መሰረት በሆነው በአቂዳ ዙሪያ ጠንከር ያለ የፀና አቋምና እምነት እንዲኖራቸው ነው፡፡
እነሱም ሕዝባቸውን ከባዕድ አምልኮ እንዲላቀቁም ሆነ እንዲጠነቀቁ ያስተምሩና ይመክሩ፣ ያስጠነቅቁና ይዘክሩ ነበር፡፡
አብዛኞቹ ህዝቦችግን ጌታቸው ለእነሱ የዋለውን ውለታ አመስግነው መቀበል ሲገባቸው የክብር መልእክትና መልእክተኛውን አስተባበሉ፡፡ በአመፀኝነትም ገፉበት፡፡
ይሁንና በአቂዳ (በእምነት) ዙሪያ ባሉት የዲን ጉዳዮች ማወላወል ወይም መለዘብ የሚባል መገር ፈፅሞ የለም፡፡
የሀቀኞቹ ምዕመናን የአህሉ ሱና ወልጀመዓ የሕይወት መመሪያ የሆነውን ቁርአንንና የነብዩን ሱና ሙሉ በሙሉ መከተል ብቻ እንጂ ለእምቢተኞችም ሆነ ለአማፂያን ሲባል መንሸራተት ተቀባይነት የለውም፡፡ በየዘመናቱ የተላኩ ነቢያትም ያስተማሩት ይህንኑ ነውና፡፡
የአንድ ሙስሊም ሙስሊምነት የሚለካው በሚያራምደው እምነት ስለሆነ አቂዳውን ከባእድ አምልኮ ማጥራት ድርድር የሌለውና ዛሬ ነገ የማያስብል ጉዳይም ነው።
ውዷ እህቴ
አላህ አዝዘ ወጀልለ የተውሂድን አርማ አንግበሽ አቂዳሽን ከሽርኪያት የምትጠብቂ ያድርግሽ።
ተንቢሀት

Post a Comment

0 Comments