አላህን ከአምሳያና ከጉድለት ማጥራት ‘ተንዚህ’
በአህሉሱና እና በአህባሾች እይታ
በአህሉሱና እና በአህባሾች እይታ
አህሉሱና የአላህ ባህሪያትን ሲያፀድቁ ከፍጡራን ጋር ፍፁም አያመሳስሉም። አል-ኢማም አሽ-ሻፊዒ የአህሉሱናን አቋም በጥሩ ቋንቋ ተናግረው አንዳንድ የአላህ ባህሪያት የፀደቁባቸውን ማስረጃዎች በምሳሌነት ከጠቀሱ በኃላ እንዲህ ብለዋል፦
«لكن نُثْبِتُ هَذِهِ الصِّفَاتِ، وَنَنْفِي التَّشْبِيهَ كَمَا نَفَى عَنْ نَفْسِهِ -تعالى ذِكْرُه- فَقَالَ: (لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ»
«..ግን እነኚህን ባህሪያት እናፀድቃለን፤ ማመሳሰልንም (አላህ) እራሱ «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» ብሎ ውድቅ እንዳደረገው ውድቅ እናደርጋለን።»
[ኢብኑ ሐጀር በ“ፈትሁ’ል-ባሪ (13/407) እንደጠቀሱት]
«..ግን እነኚህን ባህሪያት እናፀድቃለን፤ ማመሳሰልንም (አላህ) እራሱ «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» ብሎ ውድቅ እንዳደረገው ውድቅ እናደርጋለን።»
[ኢብኑ ሐጀር በ“ፈትሁ’ል-ባሪ (13/407) እንደጠቀሱት]
አህሉሱና የአላህን ባህሪያት ከአምሳያና ከጉድለት ያጠራሉ። ሆኖም ግን ይህ የተንዚህ አካሄዳቸው በሁለት መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው።
1) አላህን ከአምሳያ ማጥራት (ነፍዩል ሙማሰላህ)፡- አላህን ከፍጥረታት ምንም ነገር በምንም አይነት ባህሪ አይመስለውም፤ አላህም ከፍጥረታቱ ምንንም አይመስልም።
2) አላህን ከጉድለት ማጥራት (ነፍዩ-ነቃኢስ)፡- አላህ ጉድለትን ከሚያመላክቱ ባህሪያት ሁሉ የጠራ ነው። ማንገላጀት፣ እንቅልፍ፣ አቅም ማጣት እና አለማወቅን ከመሳሰሉ የጉድለት ባህሪዎች ሁሉ የጠራ ነው።
ይሁንና፤ አብዛኛዉን ጊዜ በቁርአን ላይ ‘አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጥራት’ ጥቅል በሆነ መልኩ የሚቀርብ ሲሆን፤ የአላህን ባህሪያት ማጽደቅ ግን በዝርዝር ሲቀርብ እናገኛለን። ተከታዩ አንቀጽ ይህንን መርሆ በጉልህ ያሳያል፤
ﻟَﻴْﺲَ ﻛَﻤِﺜْﻠِﻪِ ﺷَﻲْءٌ ۖ ﻭَﻫُﻮَ اﻟﺴَّﻤِﻴﻊُ اﻟْﺒَﺼِﻴﺮُ
«የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡» ሹራ 11
«የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡» ሹራ 11
ይህ አንቀፅ የሚያስረዳው በየትኛውም ሁኔታ በፍጡራንና በፈጣሪ መካከል መመሳሰል እንደሌለና አላህ ሰሚና ተመልካች መሆኑን ነው፡፡
☞ ልብ በል! መስሚያና መመልከቻ የብዙ ፍጡራን መገለጫዎች ቢሆኑም ነገር ግን የአላህ መስሚያና መመልከቻ ከፍጡራኑ ጋር አይመሳሰልም፡፡ በመስሚያና በመመልከቻ አምሳያ እንዳሌለው ሁሉ በሌሎችም ባህሪያቱ አምሳያ የለውም!!
አንቀጹ የጉድለት ባህሪዎችን ጥቅል በሆነ መልኩ ዉድቅ ሲያደርግ ምሉዕ ባህሪዎችን ግን በዝርዝር ያጸድቃል።
ይህ አንቀጽ ሙስሊሞች ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ከመረዳት አንጻር ሊኖራቸው ለሚገባው ትክክለኛ አካሄድና መርሆን ይቀርጻል።
ይህ አንቀጽ ሙስሊሞች ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ከመረዳት አንጻር ሊኖራቸው ለሚገባው ትክክለኛ አካሄድና መርሆን ይቀርጻል።
ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሌሎች አንቀጾችም ይገኛሉ፤
አላህ እንዲህ ብላል፦
አላህ እንዲህ ብላል፦
ﻓَﻼَ ﺗَﻀْﺮِﺑُﻮا ﻟِﻠَّﻪِ اﻷَْﻣْﺜَﺎﻝَ ۚ ﺇِﻥَّ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻭَﺃَﻧﺘُﻢْ ﻻَ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ
«ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡» አን’ነህል 74
አል ኢማም አጦበሪይ ይህን አንቀፅ በማብራራት እንዲህ ብለዋል “አምሳያም ቢጤም የለውምና ለአላህ አምሳያና ቢጤ አታድርጉ” ተፍሲሩ ጦበሪ 7/621
አላህ እንዲህ ብላል፦
ﻭَﻟَﻢْ ﻳَﻜُﻦ ﻟَّﻪُ ﻛُﻔُﻮًا ﺃَﺣَﺪٌ
«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» አል ኢኽላስ 4
ﻭَﻟَﻢْ ﻳَﻜُﻦ ﻟَّﻪُ ﻛُﻔُﻮًا ﺃَﺣَﺪٌ
«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» አል ኢኽላስ 4
ታላቁ የቁርአን ተንታኝ አል ኢማም አጦበሪይ ይህ አንቀፅ ولم يكن له شبيه ولا مثل አላህ አምሳያና አቻ እንደሌለው የሚገልፅ መሆኑን ከታላላቆቹ ሰለፍ የቁርአን ተንታኞች ከጁረይጅ፣ ከአቢልዓሊያህ እና ከኢብኑ ዓባስ አስተላልፈዋል።
አላህ እንዲህ ብላል፦
ﻫَﻞْ ﺗَﻌْﻠَﻢُ ﻟَﻪُ ﺳَﻤِﻴًّﺎ
«ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?» መርየም 65
ﻫَﻞْ ﺗَﻌْﻠَﻢُ ﻟَﻪُ ﺳَﻤِﻴًّﺎ
«ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?» መርየም 65
አል ኢማም አጦበሪ በተፍሲራቸው ላይ እንዳሰፈሩት
ኢብኑ ዓባስ ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፤
هل تعلم للرب مثلا أو شبيها
“ለአላህ አምሳያ ወይም ቢጤን ታውቃለህን?”
ኢብኑ ዓባስ ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፤
هل تعلم للرب مثلا أو شبيها
“ለአላህ አምሳያ ወይም ቢጤን ታውቃለህን?”
አህሉሱና የአላህን ባህሪዎችን ሲቀበሉና ሲያጸድቁ ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ምንም እንደማይመሳሰሉ ቀድመው ያምናሉ። ከላይ በተመለከተው ቁርአናዊ አካሄድ መሰረትም ለአላህ ባህሪያትን በዝርዝር ማጽደቅና ጉድለትና መመሳሰልን በጥቅሉ ውድቅ ማድረግ አህሉሱና ከጥንት ጀምሮ የተጓዙበት አቅጣጫ ነው።
አህባሾች እና መሰል የቢድዓ አንጃዎች ግን፤ በዚህ ፍጥረተ ዓለም ዉስጥ የሚገኙ ፍጥረታትን እና ባህሪዎቻቸውን በዝርዝር በማውሳት “አላህ ሰማይንና ምድርን አይመስልም፣ ጸሀይንና ጨረቃንም አይመስልም፣ ሰዉንና መላኢካን አይመስልም… ወዘተ” የሚል ዝርዝር የማነጻጸር አካሄድን ይከተላሉ። ሲብስባቸውም እንስሳትና እፅዋትን ይዘረዝራሉ። ነዑዙ ቢላህ!! ይህ ቁርአናዊ አካሄድ እንዳልሆነ ግልፅ ነው።
በቁርአን ላይ ወጥነት ባለው መልኩ ተቀርጾልን የምናገኘው አካሄድ እና መርሆ “አላህን ከአምሳያና ከጉድለት በጥቅሉ ማጥራት እና የአላህን ባህሪያት በዝርዝር ማጽደቅ” ነው።
☞ በእርግጥ ለተለያዩ ምክኒያቶች በቁርአንና በሀዲስ ለአላህ እንደማይገቡ የተነገሩና በዝርዝር ውድቅ የተደረጉ አንዳንድ ባህሪዎችን እናገኛለን። ግዑዝ አካላትን ሳይሆን ባህሪያትን! በቅድሚያ ጥቂቶቹን እንመልከት እና መረጃዎቹ ምን እንደሚያመላከቱ እንገልጻለን።
መመሳሰልን እና የጉድለት ባህሪዎችን በዝርዝር ዉድቅ በማድረግ ለአላህ የተገቡ ምሉእ ባህሪዎችን ከሚያጸድቁ ቁርዓናዊና ሀዲሳዊ መረጃዎች መካከል፤
ﻭَﺗَﻮَﻛَّﻞْ ﻋَﻠَﻰ اﻟْﺤَﻲِّ اﻟَّﺬِﻱ ﻻَ ﻳَﻤُﻮﺕُ
«በዚያም በማይሞተው ‘ሕያው’ አምላክ ላይ ተመካ፡፡» አልፉርቃን 58
«በዚያም በማይሞተው ‘ሕያው’ አምላክ ላይ ተመካ፡፡» አልፉርቃን 58
اﻟﻠَّﻪُ ﻻَ ﺇِﻟَٰﻪَ ﺇِﻻَّ ﻫُﻮَ اﻟْﺤَﻲُّ اﻟْﻘَﻴُّﻮﻡُ ۚ ﻻَ ﺗَﺄْﺧُﺬُﻩُ ﺳِﻨَﺔٌ ﻭَﻻَ ﻧَﻮْﻡٌ ۚ
«አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አይይዘውም፡፡» አል በቀራህ 255
«አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አይይዘውም፡፡» አል በቀራህ 255
ከአቡ ሙሰልአሽዓሪይ እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በጉዞ ላይ እያሉ አንዳንድ ባልደረቦቻቸው ድምጻቸውን በጣም ከፍ አድርገው ተክቢር ሲያደርጉ እንዲህ ብለዋቸዋል፦
(أيها الناس أربعوا على أنفسكم فإنكم لا تدعون أصمَّ ولا غائبا ، إنما تدعون سميعا بصيرا، إن الذي تدعون أقرب إلى أحدكم من عنق راحلته ) رواه البخاري ومسلم
«እናንተ ሰዎች ሆይ! ለነፍሳችሁ እዘኑላት፤ እናንተ የምትጣሩት የማይሰማን አምላክ አይደለም፤ እሩቅም አይደለም። የምትጣሩት፤ ሰሚና ተመልካች የሆነውን አምላክ ነው።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
እነዚህ እና መሰል አንቀጾች ከላይ በተገለፀው መልኩ “ጉድለትን እና መመሳሰልን በጥቅል ዉድቅ የማድረግ እና በዝርዝር የማጽደቅ” ቁርአናዊ አካሄድና መርሆን የሚጻረሩ አይደሉም። ምክኒያቱም፤
1) እነዚህ የጉድለት ባህሪዎች በዝርዝር ውድቅ የተደረጉበት አላማ አብሮ ተገልጿል። የአንቀፆቹም አላማ የነዚህን ተቃራኒ ምሉዕ ባህሪያት ለአላህ ማጽደቅ እንጂ ፍጥረታትን እና ባህሪዎቻቸውን በመዘርዘር ለአላህ እንደማይገቡ መግለፅ አይደለም።
አላህ እንቅልፍ እና ማንገላጀት እንደማይዘው መግለጹ፤ በውስጡ ያዘለው፤ የተሟላ ህያዉነት “ሀያት” እና ነገሮችን ሁሉ ማስተናበር “ቀዩሚያህ” አላህ የሚገለጽባቸው ባህሪያት መሆናቸውን ነው። አንድን ባህሪ ዉድቅ ስናደርግ የዚያን ባህሪ ተቃራኒ በተሟላ መልኩ ለአላህ እናጸድቃለን።
አህሉሱና ዘንድ፤ ዉድቅ የሚደረጉ ባህሪዎች ሁሉ በተቀራኒ ምሉእነትን የሚያመላክቱና መልካም ባህሪዎችን ባማረ መልኩ የሚያጸድቁ መረጃዎች ናቸው። ስለዚህ፤ እነዚህ በዝርዝር ዉድቅ የተደረጉ የጉድለት ባህሪያት በተዘዋዋሪ መልካም ባህሪያትን በዝርዝር የማጽደቅ አካል ናቸው።
አህሉሱና ዘንድ፤ ዉድቅ የሚደረጉ ባህሪዎች ሁሉ በተቀራኒ ምሉእነትን የሚያመላክቱና መልካም ባህሪዎችን ባማረ መልኩ የሚያጸድቁ መረጃዎች ናቸው። ስለዚህ፤ እነዚህ በዝርዝር ዉድቅ የተደረጉ የጉድለት ባህሪያት በተዘዋዋሪ መልካም ባህሪያትን በዝርዝር የማጽደቅ አካል ናቸው።
2) የተለያዩ አካላት አላህን ባልተገባ መልኩ ሲገልፁ በእርምት መልክ ይህ ባህሪ እንደማይገባው ትገልፃል።
በምሳሌ ለማብራራት...
☞ የጃሂሊያ ሰዎች፤ “መላዕክት የአላህ ልጆች ናቸው” ሲሉ፤ አላህ ይህ አይነቱ ባህሪ ለእርሱ እንደማይገባው በመግለፅ ውድቅ አድርጎታል።
☞ የጃሂሊያ ሰዎች፤ “መላዕክት የአላህ ልጆች ናቸው” ሲሉ፤ አላህ ይህ አይነቱ ባህሪ ለእርሱ እንደማይገባው በመግለፅ ውድቅ አድርጎታል።
☞ ክርስቲያኖች ጌታ ከሰው ልጅ ተወልዷል ሲሉ፤ መውለድም ይሁን መወለድ የሱ መገለጫ እንዳልሆነ በመግለፅ ውድቅ አደረገው።
☞ አይሁዶች አላህ ፍጥረታትን ካስገኘ በኃላ እረፍት እንዳደረገ ሲሰብኩ፤ ሰማያትና ምድርን በመፍጠሩ ድካም እንዳልነካው ተናገረ። በአየቱል ኩርሲይም ህያውነቱን በመግለጽ እንቅልፍ እና ማንገላጀት እንደማይዘው ተናግሮ የጉድለት ባህሪዎችን ውድቅ አደረገው።
ይህ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት አላህን ከፍጥረታት ጋር በማነፃፀር እና ፍጥረታት ላይ ያሉ ደካማነትን የሚገልፁ ባህሪያትን ሁሉ እየዘረዘሩ ለአላህ እንደማይገቡ የመግለፅ አካሄድ አይደለም። ድክመትን ውድቅ በማድረግ መብቃቃት ሳይሆን በተቃራኒው ምሉእነትን አረጋግጦ ማለፍን ያካትታል።
በቁርአን እና በሀዲስ ውድቅ የተደረጉ የጉድለት ባህሪዎችንና የተገለፁበትን አላማ አስመልክቶ ትክክለኛው የአህሉሱናም አቋም ይኸው ነው።
አህሉሱና ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ውድቅ ሲያደርጉ በተቃራኒው ምሉእ የሆኑ መልካም ባህሪዎችን በማጽደቅ ብቻ ይብቃቃሉ። ምንም አይነት ፍልስፍናን እና ጉዳዩን መለጠጥን አይቀበሉም። አላህ ልጅ እንደሌለው ስለተገለጸ፤ አባትም የለዉም፣ እናት የለዉም፣ ወንድም የለዉም...ወዘተ የሚል አካሄድ የላቸውም።
አህባሾች ግን ለመስማት በሚቀፍ አገላለጽ ብዙ ፍጥረታትን እና ባህሪዎቻቸዉን በመደርደር “አላህ ይህንን አይመስልም ያንንም አይመስልም” ይላሉ።
ለምሳሌ፤ አላህ መላእክትን አይመስልም፣ ጂንንም አይመስልም፣ሰው አይመስልም፣ አካል አይመስልም፣ ብርሀንን፣ድንጋይን፣ ዛፍን አይመስልም…ወዘተ በማለት ደጋግመው መናገራቸው የተለመደ ነው። የዚህ ግሩፕ መስራችና መሪ አብዱላህ አልሀረሪ “አሸርሁል ቀዊም” በሚለው መጽሀፉ ገጽ 107 / “አሲራጡልሙስተቂም ገጽ 28 እና በብዙ ጽሁፎቹ ይህን አይነት ዝርዝር አስቀምጧል።
“አልዓቂደቱል ኢስላሚያህ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ሙሀደራ እንዲህ ብሎ ነበር፤ «በቁርአን እንደመጣው፤ ‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡» የአንቀጹ ትርጉም፤ አላህን ከፍጥረታት ምንም የሚመስለው የለም፣ከባድ አካልም ይሁን ቀላል አካል አይመስለዉም፣ አላህ ሰውን አይመስልም፣ መላእክትንም፣ መንፈስንም፣ አይመስልም፣ ብርሀንንም ይሁን ጨለማን አይመስልም፣ ተጨባጭ ከሆኑ ግዑዝ አካላትም እንደ ድንጋይ እና ዛፍንም አይመስልም»
ይህ አካሄድ ከላይ ለመመልከት የሞከርነዉን ቁርአናዊ አካሄድ የሚጻረር የጥመት መንገድ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።
“አልዓቂደቱል ኢስላሚያህ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ሙሀደራ እንዲህ ብሎ ነበር፤ «በቁርአን እንደመጣው፤ ‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡» የአንቀጹ ትርጉም፤ አላህን ከፍጥረታት ምንም የሚመስለው የለም፣ከባድ አካልም ይሁን ቀላል አካል አይመስለዉም፣ አላህ ሰውን አይመስልም፣ መላእክትንም፣ መንፈስንም፣ አይመስልም፣ ብርሀንንም ይሁን ጨለማን አይመስልም፣ ተጨባጭ ከሆኑ ግዑዝ አካላትም እንደ ድንጋይ እና ዛፍንም አይመስልም»
ይህ አካሄድ ከላይ ለመመልከት የሞከርነዉን ቁርአናዊ አካሄድ የሚጻረር የጥመት መንገድ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።
ውድ አንባቢ፤ አንድ ሰው ሊያወድስህ እና ሊያሞካሽህ አስቦ፤ “አንተ እኮ ሌባ አይደለህም፣ ማጅራት መቺ ቀማኛም አይደለህም፣ መልከ ጥፉ አይደለህም፣ ዝንጀሮንም ይሁን ከርከሮን አትመስልም...ወዘተ” ቢልህ ደስታን ይፈጥርልሀልን? በእርግጠኝነት መልስህ የሚሆነው “እንዲህ አይነቱ ሰው ተገቢዉን ክብር አልሰጠኝም" የሚል ነው። ይህ ቢድዓና ፍልስፍናዎች አይምሮዉን ለበረዙት ሰው ካልሆነ በቀር ለማንም ግልጽ ነገር ነው።
የሰይፍን ስለታማነት ለማድነቅ ከዱላ ጋር ያነጻጸረ በተቃራኒው ዱልዱምነቱን እየገለጸ ለመሆኑ አያጠራጥርም። አላህ ከጥፋት እና ከመደናበር ይጠብቀን።
የሰይፍን ስለታማነት ለማድነቅ ከዱላ ጋር ያነጻጸረ በተቃራኒው ዱልዱምነቱን እየገለጸ ለመሆኑ አያጠራጥርም። አላህ ከጥፋት እና ከመደናበር ይጠብቀን።
والحمد لله رب العالمين, أخوكم أبو جنيد
© አስማዕ ወሲፋት ፔጅ
http://www.facebook.com/asmaewesifat
http://www.facebook.com/asmaewesifat
1 Comments
it is good jop
ReplyDelete