አስተውል!
~ ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።
~ ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።
~ ሰወችን በመውደድ ብቻ ስትጠመድ የጌታህን ውዴታ እንዳትነፈግ ፍራ! ጥላቸው ማለት አይደለም ውዴታህ በልክ ይሁን!
~ እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ እውነተኛ ሁን!
~ የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!
~ ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።
~ ፍርድ ለመስጠት ከመወሰንህ በፊት ዳኛ ለመሆን አቅሙ እንዳለክ እራስክን ጠይቅ።
~ ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!
~ ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!
~ መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።
~ ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!
~ ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።
~ መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ!!
°°°°°^^^^^^^°°°°°°°^^^^^^^^°°°°°°°°°^^^^^^^°°°°°°^^^^
0 Comments