የቁርኣን መለያዎች 4
┄┄┉┉✽̶»̶̥


} ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﻳَﺴَّﺮْﻧَﺎ ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥَ ﻟِﻠﺬِّﻛْﺮِ ﻓَﻬَﻞْ ﻣِﻦْ ﻣُﺪَّﻛِﺮٍ { ( ﺍﻟﻘﻤﺮ : 17 )
‹‹ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?›› አል ቀመር 17
} ﻛِﺘَﺎﺏٌ ﺃَﻧْﺰَﻟْﻨَﺎﻩُ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﻣُﺒَﺎﺭَﻙٌ ﻟِﻴَﺪَّﺑَّﺮُﻭﺍ ﺁﻳَﺎﺗِﻪِ ﻭَﻟِﻴَﺘَﺬَﻛَّﺮَ ﺃُﻭﻟُﻮ ﺍﻟْﺄَﻟْﺒَﺎﺏِ { ( ﺹ 29 : )
‹‹(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡›› ሷድ 29
ሙጃሂድ የመጀመሪያውን አንቀፅ ስያብራሩ እንዲህ ይላሉ :-
“የቁርአን አነባብ ገር አደረግን ማለት ነው፡፡”
ሱድይም እንዲህ ብለዋል:-
“ አነባቡን ምላስ ላይ ቀለል እንዲል አደረግን፡፡”
ኢብኑ ዓባስም እንዲህ ይላሉ :-
“አላህ የቁርአን አነባብን ለሰዎች ምላስ እንዲቀል ባያደርግ ኖሮ የትኛውም ፍጡር የአላህን ንግግር ማንበብ አይችልም ነበር፡፡”
ጠበሪይና ሌሎችም የቁርአን ተርጓሚዎች እንዳሉት የቁርአን ገር መሆን አነባቡንም ትርጉሙንም የሚመለከት ነው፡፡ ሲነበብ ለምላስ ቀለል እንዲል ትርጉሙንም ለማስተንተንና በትርጉሙም ለመመከር የተገራ ነው፡፡

} ﻭَﺃَﻧْﺰَﻟْﻨَﺎ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻣُﺼَﺪِّﻗًﺎ ﻟِﻤَﺎ ﺑَﻴْﻦَ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏِ ﻭَﻣُﻬَﻴْﻤِﻨًﺎ ﻋَﻠَﻴْﻪِ { ( ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ 48 : )
‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› (አል ማኢዳህ 48)
} ﺷَﺮَﻉَ ﻟَﻜُﻢْ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺪِّﻳﻦِ ﻣَﺎ ﻭَﺻَّﻰ ﺑِﻪِ ﻧُﻮﺣًﺎ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃَﻭْﺣَﻴْﻨَﺎ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﺻَّﻴْﻨَﺎ ﺑِﻪِ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻭَﻣُﻮﺳَﻰ ﻭَﻋِﻴﺴَﻰ ﺃَﻥْ ﺃَﻗِﻴﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﺘَﻔَﺮَّﻗُﻮﺍ ﻓِﻴﻪِ { ( ﺍﻟﺸﻮﺭﻯ 13 : )
‹‹ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡›› (ሹራ: 13)

} ﻭَﻛُﻠًّﺎ ﻧَﻘُﺺُّ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﻣِﻦْ ﺃَﻧْﺒَﺎﺀِ ﺍﻟﺮُّﺳُﻞِ ﻣَﺎ ﻧُﺜَﺒِّﺖُ ﺑِﻪِ ﻓُﺆَﺍﺩَﻙَ { ( ﻫﻮﺩ : 120 )
‹‹ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡››(ሁድ 12ዐ)
} ﺫَﻟِﻚَ ﻣِﻦْ ﺃَﻧْﺒَﺎﺀِ ﺍﻟْﻘُﺮَﻯ ﻧَﻘُﺼُّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﻣِﻨْﻬَﺎ ﻗَﺎﺋِﻢٌ ﻭَﺣَﺼِﻴﺪٌ { ( ﻫﻮﺩ : 100 )
‹‹ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው፡፡ ባንተ ላይ እንተርከዋለን፡፡ ከእርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ አለ፡፡›› (ሁድ 1ዐዐ)
} ﻛَﺬَﻟِﻚَ ﻧَﻘُﺺُّ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﻣِﻦْ ﺃَﻧْﺒَﺎﺀِ ﻣَﺎ ﻗَﺪْ ﺳَﺒَﻖَ ﻭَﻗَﺪْ ﺁﺗَﻴْﻨَﺎﻙَ ﻣِﻦْ ﻟَﺪُﻧَّﺎ ﺫِﻛْﺮًﺍ { ( ﻃﻪ 99 : )
‹‹እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፡፡ ከእኛም ዘንድ ቁረኣንን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡›› (ጣሃ 99)

} ﻧَﺰَّﻝَ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻣُﺼَﺪِّﻗًﺎ ﻟِﻤَﺎ ﺑَﻴْﻦَ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻭَﺃَﻧْﺰَﻝَ ﺍﻟﺘَّﻮْﺭَﺍﺓَ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧْﺠِﻴﻞَ }{ ﻣِﻦْ ﻗَﺒْﻞُ ﻫُﺪًﻯ ﻟِﻠﻨَّﺎﺱِ ﻭَﺃَﻧْﺰَﻝَ ﺍﻟْﻔُﺮْﻗَﺎﻥَ { ( ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ : 3 ، 4 )
‹‹ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡ (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)፡፡ ፉርቃንንም አወረደ ፡፡›› (አል ዒምራን 3-4)
} ﻭَﺃَﻧْﺰَﻟْﻨَﺎ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻣُﺼَﺪِّﻗًﺎ ﻟِﻤَﺎ ﺑَﻴْﻦَ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏِ ﻭَﻣُﻬَﻴْﻤِﻨًﺎ ﻋَﻠَﻴْﻪِ { ( ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ : 48 )
‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› (አል ማኢዳህ 48)
እነዚህ ከፊል ቁርአንን ከሌሎች መፃህፍት የሚለይ መለያዎቹ ሲሆኑ በቁርአን ላይ ያለን እምነት እንዲረጋገጥ ወሳኝ ነጥቦች ናቸው፡፡
•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•


https://t.me/tenbihat
© ተንቢሀት
0 Comments