Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ብዙ ያልተወራለት አስገድዶ እምነት የማስለወጥ ታሪክ በኢትዮጵያ


ብዙ ያልተወራለት አስገድዶ እምነት የማስለወጥ ታሪክ በኢትዮጵያ
“ርኩስ፣ ዲዮቆሮስን ቅዱስ ይሉታል፡፡ የኬልቆዶን ጉባኤ በኢትዮጵያ የተነቀፈ ነው፡፡ ስለዚህ ኣፄ ዮሃንስ የኬልቄዶንን ጉባኤ ለማጥፋት ደብረ ሊባኖስንም ለማውደም የኢትዮጵያን መኳንንትና ሊቃውንት ሰብስበው በፍየል ኣምባ ጉባኤ ኣደረጉ፡፡ ከዚህ በኋላ ኣዋጅ ኣደረጉ፡፡ እስላምና አሮሞ/ ፓጋን ክርስትና እንዲነሳ ያውም በግድ፡፡ ከአሮሞ ሁሉ ኣስቀድሞ እስላም የሆነ የበርቱማ ነገድ አሮሞ ነው፡፡ አሮሞ ሁሉ ኣስቀድሞ የተጠመቀ የወሎ አሮሞ ሆነ፡፡ የወሎ ባላባቶች ይማሙዎች ተጠመቁ፡፡ ይማሙ ኣባ ዋጠውን ኣመዴን ንጉስ ምኒልክ ኣባት ሁነው ኣስጠመቁ፡፡ ደጃች ሃይለማርያም ኣሰኟቸው፡፡ ይማሙ መሓመድ ኣሊን ኣፄ ዮሃንስ ኣባት ሁነው ኣስጠምቀው ራስ ሚካኤል ኣሰኟቸው፡፡ ከዚህ ህዝቡን በግድ ያጠመቁትና በግድ ያቆርቡት ጀመሩ፡፡ ጉልበት ያለውና በሃይማኖቱ የቆመ ወደ መተማ ከደርቡሽ ሲሆን እኩሉ ወደ ቀቤና ና ወደ ጅማ ወደ ሃረርጌም ተሰደደ፡፡ በየሄዱበት ሃገር ሁሉ ሽፍታ ብቻ ሆነ፡፡ የሃበሻ ኣውራጃዋ ሁሉ ጦርነት ብቻ ሆነ፡፡ በየዥረቷ ሁሉ የሰው ደም ሆነ፡፡ ንጉስ ምኒልክ ወደ ኣፄ ዮሃንስ ቀርበው ጃንሆይ እግዚኣብሄር ይወድልናልን፣ በግድ ቁረብ እያልን ህዝባችንን ብንፈጀው? ብለው ጠየቁ፡፡ ጃንሆይም (ዮሐንስ) ሲመልሱ የኢትዮጵያንን ደም እበቀልላታለሁ፡፡ ግራኝምኢትዮጵያን ሲያሰልማት በግድ በእሳትና በሰይፍ ነው፡፡ እኛስ የማርቆስን ሃይማኖት ካላቀናነውና ካልመሰረትነው ማን ያቀናዋል? አሉ ተብሎ በጊዜው ክበር ሁኖ ይወራ ይነገር ነበረ፡፡ ከዚህ በኋላ ኣፄ ዮሃንስ ወሎ ላይ ከረሙ፤ ሲያቆርቡ፣ ያልቆረበውን ሲፈጁ፡፡ ቦሩ ሜዳ ቤተ ክርስቲያን እያሰሩ፡፡ ራስ ኣዳልም ጎዣም ተሻገሩ፣ ቅብኣት የሚባለውን ሲያጠፉ፣ እስላሙንም ሲያቆርቡ፡፡ ንጉስ ምኒልክ ወደ ኣንኮበር ገቡ. የይፋትን እስላም፣ የኣርጎባንም፣ የኣብቹንና የገላንን [አሮሞ] መላ ትሎማን በግድ ሲያጠምቁ፣ ሲያቆርቡ ከረሙ፡፡"
[የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ ፡ ገ. 686-688]

Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments