Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከመፅሐፋቸው ጋር የሚታኮሱ ፃድቃኖች!!



ከመፅሐፋቸው ጋር የሚታኮሱ ፃድቃኖች!!
በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ አራት ሴት የሚያገባበት አግባብ እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ ክርስቲያኖች ይህን መነሻ በማድረግ ኢስላምን ሲያብጠለጥሉ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ይህ አካሄዳቸው ሰዎቹ ምን ያክል ለመፅሐፎቻቸው ወይ ባይተዋር ወይ ደግሞ ሽፍታ እንደሆኑ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡ እንጂ በመፅሐፎቻቸው ይሄ ጉዳይ እጅግ በተጋነነ እና ኢስላም ከሚፈቅደውም በራቀ መልኩ የሚገኝ ነው፡፡ ነብያት ሳይቀሩ ብዙ ሚስቶች እንነበራቸው ተገልጿል፡፡ ለምሳሌ ያክል፡-
1. ”ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፣ አንዲቱም የተጠላች ሁለት #ሚስቶችቢኖሩት…” [ዘዳግም 21:15]2. “ዔሳው ከከነዓን ልጆች #ሚስቶችን አገባ፡፡” [ኦሪት ዘፍጠረት 36፡2] 3. “ላሜሕም #ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው..” [ኦሪት ዘፍጥረት 4፡23]4. “ለጌዴዎንም #ብዙ_ሚስቶች ነበሩትና…” [መፅሃፈ መሳፍንት 8:30]5. “የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራሀም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።” [ኦሪት ዘፍጠረት 16:3]6. “ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን #ቁባቶቹንናሚስቶቹንከእየሩሳሌም ወሰደ፣…” [መፅሐፈ ሳሙኤል ካልእ፡ 5፡13]7. “ያዕቆብም ተነሳ፣ ልጆቹንና #ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፡፡” [ኦሪት ዘ ፍጥረት 31፡ 17]8. 14 ሚስቶች!!! “አብያም ጸና፣ #አስራአራትን #ሚስቶች አገባ…” [መፅሐፈ ዜና መዋእል ካልእ 13፡21]9. “ሮብአምም ከሚስቶቹና ከእቁባቶቹ ሁሉ የአቤሴሎምን ልጅ ሞአብን ወደደ #18ሚስቶች #60እቁባቶች ነበሩት፡፡” [መፅሃፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11:21]10. 700 ሚስቶች እና 300 ቁባቶች ለሰሎሞን!!! “ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ #700ሚስቶች #300ምቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።” [መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11:3] ክርስቲያኖች ሆይ! ይቺ ነገር የሙሐመድ ብትሆን እንዴት እንደምታራግቧት እስኪ ህሊናችሁን ጠይቁ!! እምነታችሁ እንዲህ አይነት ፍርደ ገምድልነትን ያዛችኋልን?

Post a Comment

0 Comments