Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጫት የዱኣ መሳሪያም የእስልምና አካል አይደለም

ጫት የዱኣ መሳሪያም የእስልምና አካል አይደለም፡፡
ያ ምርጡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የመጡበት ውብ ሃይማኖት እስልምና በሰርጎ ገቦች ብዙ መጥፎ ነገሮችን የኢስላም አካል አስመስለው ሰግስገውበታል፡፡ የኢስላም ምርጥ ሊቃውንትም በየጊዜው እነዚህ ሰርጎ ገብ እምነቶች እና መጥፎ ተግባራት ከኢስላም አካል አለመሆናቸውን የተቃወመ ቢቃወማቸውም አብራርተው አስረድተዋል፡፡
ጫት እንደሚታወቀው ሙስሊሙን አሽመድምዶ ከጌታው ጋር ያለንም ይሁን ከፍጡራን ጋር ያለውን መብት አንድ ቃሚ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነ አደገኛ መጥፎ ቅጠል ነው፡፡ አሳዛኙ እውቀት አላቸው ተብለው ሙስሊሙን ኡማ የሚቅመው በርትቶ እንዲቅም፣ የማይቅመው እንዲቅም ጫትን የኢስላም አካል እና የዱኣ መሳሪያ አድርገው የሚሰብኩ ሆድ አደሩዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በመንዙማቸው፣ ሌላኛዎቹ ባገኙት መድረክ ላይ ጫትን እንደጥሩ ነገር ለሙስሊሙ ያስተዋውቃሉ፡፡ ሙስሊሞች ሊረዱ የሚገባቸው ጫት በጣም አደገኛ ነው፡፡ ይህም በተግባር የምናየው የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዳሮች ሲበተኑ፣ የት ይደርሳሉ የተባሉ ወንድም እና እህቶች ተበለሻሽታ ማየታችን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡
በመንዙማዎች ላይ ስለ ጫት ከተሰበኩ አደገኛ ስንኞች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

 “ጁሉሱ ሰኣቲን ጥቂት ቃቅምና (ጫት ቃምና ትንሽ ተቀመጥ)
ንገረው ለመውላህ እበሩ ቁምና”
 “እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት፣ እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት”
 “ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ”
 “ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣ የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ”
 ከ አስር ሺህ መትረየስ አጥምዶ ከቆመ፣
ከሺህ ፈረሰኛ ተባብሮ ለቆመ፣
ይበልጣል ደግበል አጥብቆ የቃመ፣
ጠላቱንም ጎድቶ ወዳጁን ጠቀመ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በዚህ ሱስ የተያዙትን በጠቅላላ እንዲያወጣቸው ዱኣ እና ምክር አይለያቸው፡፡ ጫት የምትቅሙ ወንድም እና እህቶች ሆይ! አላህ የውመል ቂያማ ጊዜያችንን በምን እንዳሳለፍነው ይጠይቀናል፡፡ ከዚህ ጊዜን እና ስብእናን ከሚገድል እርኩስ ቅጠል አላህን ለምናችሁ ለእሱ ስትሉ አቁሙ፡፡

Sadat Kemal Abu Meryem