Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ማልታ መጠጥ


ስለ ማልታ መጠጥ
ማልታ ስለሚባለው መጠጥ ብይን የሚጠይቁ ሰዎች በዝተዋል። በእርግጥ እኔ ብይኑን አላውቅም። ተቀራራቢ በሆነ መጠጥ ላይ የተለያየ ይዘት ያላቸው ጥቂት የዑለማዎች ፈትዋ ባገኝም እንደራሴ እይታ በቂ ስላልመሰለኝ ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻልኩም። ብቻ ፋብሪካውን ከመንግስት በመግዛት ይህን መጠጥ የሚያመርተው ዲያጆ ኩባንያ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የአልኮል መጠጥ አከፋፋይ ነው። ለምሳሌ ያክል የሚከተሉት መጠጦች በዚህ ኩባንያ የሚመረቱ እንደሆኑ መረጃዎችን ሳስስ አግኝቻለሁ:–
① ጆኒ ዎከር፣
② ክራውን ሮያል፣
③ ጄብ፣
④ ቡኬነንስ፣
⑤ ዊንድሶርና ቡሽሚልስ ውስኪ፣
⑥ እስሚርኖፍ፣
⑦ ሰሮክ፣
⑧ ኬቴል ዋን ቮድካ፣
⑨ ቤይሊስ፣
①0 ካፒቴን ሞርጋን፣
①① ታንክሬይ

በኢትዮጵያ ደግሞ
① ሜታ ቢራ እና
② ጊነስ ናቸው።
ከእነዚህ በተጨማሪ ነው እንግዲህ ማልታ የተሰኘውን ከአልኮል "ነፃ ነው" የሚለውን መጠጥ በማምረት ማስተዋወቅ የጀመረው።
ሌሎች ነገሮችን ለጊዜው ይቅሩና
① የእውነት ማልታ ከአልኮል ነፃ ነው ወይ?
② ማንስ ተጨባጭ ጥናት አድርጎበታል?
③ ኩባንያው "ከአልኮል ነፃ" እያለ በሚለቀው ማስታወቂያ ምን ያክል ይታመናል?
④ አዘገጃጀቱስ ምን ያክል ጤናማ ነው?
⑤ ኩባንያው ማልታን የሚያመርተው ከሌሎች አስካሪ መጠጥ ንግድ ከሚያገኘው ገቢ ነው ወይስ ከሌላ?
⑥ የሚያዘጋጀው በአልኮል ምርቶቹ ትርፍ ከሆነ ሐራም በሆነ ገንዘብ የተዘጋጀን ምግብና መጠጥ አስገዳጅ ችግር በሌለበት መመገብ ብይኑ ምንድን ነው?
እነዚህና መሰል ጥያቄዎች በቂ መልስ የሚሹ ይመስለኛል። ፈትዋ እየሰጠሁ እንዳልሆነ ይሰመርልኝ። ሆኖም ግን እንደ ግል እይታ ቁርጥ ያለ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ብንርቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በሐዲሥ:
– "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደማያጠራጥርህ ሁን!!"
– "አሻሚ ነገሮች ላይ የወደቀ ሐራም ላይ ወድቋል" እንደተባለ ይታወስ።
በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ፈትዋ ያጋጠማችሁ ከስር ብታሰፍሩት ለብዙ ሰዎች ይጠቅማል ብየ አስባለሁ። ስለዚህ መጠጥ ተጨማሪ መረጃ ያላችሁ ከኖራችሁም እንዲሁ ማጣራት ለሚሹ ሰዎች ግብአት ይሆናልና ያላችሁን ብንለዋወጥ ደስ ይለኛል። ጀዛኩሙላሁ ኸይራ።

Ibnu Munewor