Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ልጆቻችሁን የካርቱን ምስል ቪዲዮዎችን እንዲመለከቱ የምትፈቅዱ

ልጆቻችሁን የካርቱን ምስል ቪዲዮዎችን እንዲመለከቱ የምትፈቅዱ ቤተሰቦች ደግማችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት። አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ብዙዎቹ ታዋቂ የካርቱን ምስል ቪዲዮ ካምፓኒዎች አንደነ Walt Disney, Cartoon Network, DreamWorks Animation የመሳሰሉት ግዙፍ ድርጅቶች የካርቱን ገጸ ባሕሪውን እንዲስሉ፥ እንዲተውኑ፥ ዳይሬክት እንዲያደርጉ የሚቀጥሯቸው ባለ ሙያዎች ግብረ ሶዶማውያን፥ ኃይማኖት አልባዎች፥ ኮንስፓይራሲ ቲዮሪ አራማጆች ከመሆናቸውም ጋር ለሕጻናት የሚያዘጋጁት የካርቱን ፊልም ላይ የግላቸውን አስተሳሰብና እምነት እንዲንጸባረቅበት በማድረግ መጪውን ትውልድ የነርሱን የተዛባ መርዝ አስተሳሰብ ይዞ እንዲያድግ ጥረት እያደረጉ ይገኛል። ይህ የአስተሳሰብ ወረራ ነው። እንደምታውቁት የልጅ ጭንቅላት ልክ እንደ ነጭ ወረቀት ነው። አሁን ላይ በአፍላ እድሜያቸው በሚመለከቷቸው ቪድዮዎች ይህን መሰል አጥፊ አስተሳሰብ ይዘው ካደጉ ምን አይነት ትውልድ ሊቀረጽ እንደሚችል ከወዲሁ ገምቱት። ለልጆች አኒሜሽን ፊልሞችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለከቱ ፈቅደን ነገ ላይ ልጆቻችን ሰቅጣጭ ቃላትን ሲተፉ ስናደምጥ፥ እኛው ቤተሰቦቻቸውን ላይ ለመማታት እጃቸው ሲዘረጉ ስንመለከት፥ የፈጣሪን መኖር ተጠራጥረው በጥያቄ ምልክት ውስጥ ሆነው ስናገኛቸው፥ ብልግናን ሲተገብሩ ስናይ መውቀስ ያለብን ራሳችንን እንጂ ሌላን አይደለም።

  Abu Aisha