የትዳር ግንኙነት ሚስጥሮችን ስለማባከን እና ይህንን በሚመለከት ሸሪአዊ እይታ
حكم افشاء الأزواج للأسرار الزوجية
ምስጋና ለአላህ ይገባው የአላህ ሰላትና ሰላም በመጨረሻው ነብይ በሙሀመድ ላይ ይስፈን
በባልና በሚስት መካከል ስለሚፈፀም የሩካቤ ስጋ ግንኙነትን የመሰለ ጉዳይ ማውራትና ማሰራጨት ክልክል ስለመሆኑ በሸሪአ ውስጥ የተለያዩ ማስረጃዎችን እናገኛለን።
... سَمِعْتُ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ يَقُولُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: ((إِنَّ مِنْ أَشَرِّ النَّاسِ عِنْدَ اللَّهِ مَنْزِلَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ الرَّجُلَ يُفْضِي إِلَى امْرَأَتِهِ وَتُفْضِي إِلَيْهِ ثُمَّ يَنْشُرُ سِرَّهَا)). صحيح مسلم
አቢ ሰኢድ አልኹድርይን እንዲህ ሲል ሰምቸዋለሁ በሚል በተላለፈ ሀዲስ ፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰ·ዐ·ወ·) እንዲህ ይላሉ:– "በትንሳኤ ቀን ከአላህ ዘንድ ከሰወች በደረጃ መጥፎው ሰው አንድ ወንድ በሚስቱ ይደርስና እርሷም ወደርሱ ትደርስና ከዚያም ሚስጥሯን የሚበትን ነው።" ሶሂህ ሙስሊም
ኢማሙ አነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:– ‘በዚህ ሀዲስ ውስጥ አንድ ሰው በርሱና በሚስቱ መካከል ስለሚፈፀም ስሜትን የማርካት ጉዳይ ማሰራጨትን፣ የዚህን ድርጊት ዝርዝር መግለፅ፣ ከሴቷ የሚወጣን ቃል ወይም ድርጊት የመሳሰሉትን ዝርዝር ማውራት መከልከሉን እንገነዘባለን።’ ሶሂህ ሙስሊም ሸርህ
ነገር ግን ሸሪአዊ ለሆነ ህግጋት ብይን ማብራሪያ ለመፈለግ፤ ምክርን ለመፈለግ ወይም በባልና ሚስት መካከል የተከሰተን አለመግባባት ለመከላከልና መሰል ሁኔታዎች ካስገደዱ መግለፁ ምንም አይነት ችግር አይኖረውም። ሆኖም ለዚህም ቢሆን በግልፅ ከመናገር ይልቅ ስልታዊ በሆነ መልኩ (በማግደምደም) መጠቀሙ እጅግ የተሻለ ይሆናል። በተጨማሪም ጉዳዩን ወይንም ሁኔታውን በጥቅሉ መግለፅ ከተቻለ በዝርዝር ማቅረቡ ተገቢ አይሆንም።
ይህንን የሚያስረዳንም:–
عَنْ عَائِشَةَ زَوْجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَتْ إِنَّ رَجُلاً سَأَلَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الرَّجُلِ يُجَامِعُ أَهْلَهُ ثُمَّ يُكْسِلُ هَلْ عَلَيْهِمَا الْغُسْلُ وَعَائِشَةُ جَالِسَةٌ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: ((إِنِّي لأَفْعَلُ ذَلِكَ أَنَا وَهَذِهِ ثُمَّ نَغْتَسِلُ)). مسلم
ከእናታችን አኢሻህ አላህ ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች ‘አንድ ሰው የአላህን መልእክተኛ (ሰ·ዐ·ወ·) :– አንድ ሰው ሚስቱን ተገናኝቶ ቸል ቢል(የዘር ፈሳሽ ባይወጣው) በሁለቱ ለይ መታጠብ አለባቸውን? ሲል ይጠይቃቸዋል፤ (አኢሻህ ተቀምጣ ነበር) ፣ የአላህን መልእክተኛም (ሰ·ዐ·ወ·) እንዲህ አሉ:– "እኔ ይህንን አደርጋለሁ፣ እኔና ይህች፣ ከዚያም እንታጠባለን" ሙስሊም
ኢማሙ አነወውይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:– በዚህ ሀዲስ ውስጥ ሚስት ባለችበት ቦታ ይህንን የመሰለ ነገር መጥቀስ እንደሚቻል እንረዳለን። ይህም ችግር የማያመጣና ሸሪአዊ ጥቅም(ሸሪአዊ ብይን) ያለው ከሆነ ነው ፣ ነብዩም (ሰ·ዐ·ወ·) ይህንን በዚህ አይነት አገላለፅ የመለሱለት በነፍሱ እንዲሰርፅና እንዲረጋጋ ነው። (ሙስሊም ሸርህ)
ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና በቡሉግ አልመራም ከላይ የተገለፀውን የአቢ ሰኢድ አልኺድሪይ ሀዲስ ሸርህ ሲያደርጉ እንዲህ ይላሉ:– "............ሀዲሱ ይህንን ድርጊት እንደሚከለክል ማለትም አንድ ሰው በእርሱና በሚስቱ መካከል ያለን ሚስጥር ማውጣትን የሚከለክልና እንዲያውም በውስጡ ዛቻ ያለበት በመሆኑ ከታላላቅ ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን ያመለክታል። ከዚህ ውስጥ ተለይቶ ሊወጣ የሚችለው ሸሩአዊ ድንጋጌን ግልፅ ለማድረግ (ማብራራት) ሁኔታዎች ካስገደዱ የሚለው ብቻ ይሆናል።......ከዚያም እንዲህ አሉ:– በዚህ መሰረት መገለፅ የሌለበትን ጉዳይ ሸሪአዊ ለሆነ ጥቅም መግለፁ አስገዳጅ ከሆነ መግለፁ ችግር አይኖረውም፤ የሚፈቀድም ይሆናል። ነገር ግን ለመቀለድ ወይም ለኩራትና ለመደነቅ ከሆነ ክልክል ይሆናል።"
በእርግጥ በባልና ሚስት መካከል የሚካሄድን ስሜትን የማርካትና መሰል ጉዳይ ሚስጥሩ ሊጠበቅና መሰራጨት ከማይገባቸው ከአማና (አደራ) የሚመደብ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከላይ የተጠቀሰው ሀዲስ ይህን ያመላክታል፤ በሌላ ዘገባም
سَمِعْتُ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ يَقُولُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: ((إِنَّ مِنْ أَعْظَمِ الأَمَانَةِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ الرَّجُلَ يُفْضِي إِلَى امْرَأَتِهِ وَتُفْضِي إِلَيْهِ ثُمَّ يَنْشُرُ سِرَّهَا)). صحيح مسلم
አቢ ሰኢድ አልኹድርይን እንዲህ ሲል ሰምቸዋለሁ በሚል በተላለፈ ሀዲስ ፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰ·ዐ·ወ·) እንዲህ ይላሉ:– "በትንሳኤ ቀን ከአላህ ዘንድ ከአደራዎች(አማናን ከመብላት) የከበደው (መጥፎው) አንድ ወንድ በሚስቱ ይደርስና እርሷም ወደርሱ ትደርስና ከዚያም ሚስጥሯን የሚበትን ነው።" (ሶሂህ ሙስሊም)
አልመናዊ በፈይድ አልቀዲር መፅሀፍ እንዲህ ይላሉ:– በግልፅ እንደምንገነዘበው በሴትም (ሚስት) ላይ በአርግጥ ሚስጥርን በማባከን ላይ ልክ እንደ ወንዱ የተከለከለና እርም ይሆናል።
اللهم اجعلنا ممن إذا اؤتمن أدى الأمانة، اللهم إنا نعوذ بك من الخيانة وسائر الصفات الذميمة، اللهم احفظنا من بين أيدينا ومن خلفنا، وعن أيماننا وعن شمائلنا، واجعلنا من الراشدين.
والحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
አላህ ሆይ አደራ ሲሰጠውና ሲታመን አደራውን ከሚወጣ አድርገን፤ አላህ ሆይ ከከዳተኝነትና ከማንኛውም የተነወረ በህሪ ባንተ እንጠበቃለን፤ አላህ ሆይ ከበስተፊታችን፣ ከበስተኃላችን ከበስተቀኛችንና ከበስተግራችን ጠብቀን፤ ቅኑን ከተመሩትም አድርገን።
ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ይገባው፣ የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን በሙሀመድ (ሰ·ዐ·ወ·)፣ በቤተሰቦቻቸውና ባጠቃላይ በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን!
indris abu mus'ab
© ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት Tenbihat - Rulings Pertaining to Muslim Women



