Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቁርኣን መለያዎች 3


 
የቁርኣን መለያዎች
#⃣ 3
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄

📌ቁርአን በማንኛውም ፍጡር አምሳያ ሊመጣ የማይቻል በአገላለፅ ብቃቱ ጣሪያ የነካ በመሆኑ ሰዎችና ጋኔን በአጠቃላይ የቁርአንን አምሳያ ወይም ከፊሉን ከቻሉ እንዲያመጡ በሶስት ደረጃ ሞከራቸው፡፡

በመጀመሪያ
} ﺃَﻡْ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺗَﻘَﻮَّﻟَﻪُ ﺑَﻞْ ﻟَﺎ ﻳُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ }{ ﻓَﻠْﻴَﺄْﺗُﻮﺍ ﺑِﺤَﺪِﻳﺚٍ ﻣِﺜْﻠِﻪِ ﺇِﻥْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﺻَﺎﺩِﻗِﻴﻦَ { ‏( ﺍﻟﻄﻮﺭ 33 : ، 34 ‏)

« ወይም «ቀጠፈው ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡ እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡›› (ጡር 33-34)

በፍፁም የማይችሉት ነገር መሆኑን ደግሞ እንዲህ በማለት አፀና፡፡

} ﻗُﻞْ ﻟَﺌِﻦِ ﺍﺟْﺘَﻤَﻌَﺖِ ﺍﻟْﺈِﻧْﺲُ ﻭَﺍﻟْﺠِﻦُّ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﻥْ ﻳَﺄْﺗُﻮﺍ ﺑِﻤِﺜْﻞِ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥِ ﻟَﺎ ﻳَﺄْﺗُﻮﻥَ ﺑِﻤِﺜْﻠِﻪِ ﻭَﻟَﻮْ ﻛَﺎﻥَ ﺑَﻌْﻀُﻬُﻢْ ﻟِﺒَﻌْﺾٍ ﻇَﻬِﻴﺮًﺍ { ‏( ﺍﻹﺳﺮﺍﺀ : 88 ‏)

«ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርኣን ብጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም» በላቸው፡፡ ››(አል ኢስራእ 88)

በማስከተል አምሳያው የሆኑ አስር ምዕራፎችን እንዲያመጡም ቢሞክራቸው አልቻሉም፡፡

} ﺃَﻡْ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺍﻓْﺘَﺮَﺍﻩُ ﻗُﻞْ ﻓَﺄْﺗُﻮﺍ ﺑِﻌَﺸْﺮِ ﺳُﻮَﺭٍ ﻣِﺜْﻠِﻪِ ﻣُﻔْﺘَﺮَﻳَﺎﺕٍ ﻭَﺍﺩْﻋُﻮﺍ ﻣَﻦِ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺘُﻢْ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺻَﺎﺩِﻗِﻴﻦَ { ‏( ﻫﻮﺩ : 13 ‏)

ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው፡፡ (ሁድ 13)

ከዚያም በሶስተኛው አምሳያው የሆነ አንድ ምዕራፍ እንኳን እንዲያመጡ ቢሞክራቸውም አልቻሉም፡፡

} ﺃَﻡْ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺍﻓْﺘَﺮَﺍﻩُ ﻗُﻞْ ﻓَﺄْﺗُﻮﺍ ﺑِﺴُﻮﺭَﺓٍ ﻣِﺜْﻠِﻪِ ﻭَﺍﺩْﻋُﻮﺍ ﻣَﻦِ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺘُﻢْ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺻَﺎﺩِﻗِﻴﻦَ { ‏( ﻳﻮﻧﺲ : 38 ‏)

በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን᐀ «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)»
በላቸው፡፡ (ዩኑስ 38)

ከቁርአን ትንሹ ምዕራፍ ባለሶስት አንቀፅ ምዕራፍ ሲሆን ይህንን እንኳን ተመሳሳዩን ማምጣት የማይችሉ መሆናቸው የቁርአንን ኃያልነት ያረጋግጣል፡፡

📌 አላህ በቁርአን አማካኝነት ለሰዎች ለሃይማኖታቸውም ሆነ ለአለማዊ ህይወታቸው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ገልጿል፡፡

} ﻭَﻧَﺰَّﻟْﻨَﺎ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺗِﺒْﻴَﺎﻧًﺎ ﻟِﻜُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻭَﻫُﺪًﻯ ﻭَﺭَﺣْﻤَﺔً ﻭَﺑُﺸْﺮَﻯ ﻟِﻠْﻤُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ { ‏( ﺍﻟﻨﺤﻞ 89 : ‏)

‹‹መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡›› ነህል 89
} ﻣَﺎ ﻓَﺮَّﻃْﻨَﺎ ﻓِﻲ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏِ ﻣِﻦْ ﺷَﻲْﺀٍ { ‏( ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ 38 : ‏)

‹‹በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም ›› አል አንዓም 38

ኢብን መስዑድ እንዲህ ይላሉ፦

“በቁርአን ሁሉም እውቀቶች ወርደዋል ማንኛውም ነገር ቁርአን ውስጥ ተዘርዝሮልናል፡፡”

•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•
📲 ለሌሎች በማስተላለፍ በዳእዋ እንሳተፍ⚡️

https://t.me/tenbihat
© ተንቢሀት