┄┄┉┉✽̶»̶̥
አላህ እንዲህ ብሏል፦
} ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺘَّﺒِﻌُﻮﻥَ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲَّ ﺍﻟْﺄُﻣِّﻲَّ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳَﺠِﺪُﻭﻧَﻪُ ﻣَﻜْﺘُﻮﺑًﺎ ﻋِﻨْﺪَﻫُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟﺘَّﻮْﺭَﺍﺓِ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧْﺠِﻴﻞِ ﻳَﺄْﻣُﺮُﻫُﻢْ ﺑِﺎﻟْﻤَﻌْﺮُﻭﻑِ ﻭَﻳَﻨْﻬَﺎﻫُﻢْ ﻋَﻦِ ﺍﻟْﻤُﻨْﻜَﺮِ ﻭَﻳُﺤِﻞُّ ﻟَﻬُﻢُ ﺍﻟﻄَّﻴِّﺒَﺎﺕِ ﻭَﻳُﺤَﺮِّﻡُ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢُ ﺍﻟْﺨَﺒَﺎﺋِﺚَ ﻭَﻳَﻀَﻊُ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﺇِﺻْﺮَﻫُﻢْ ﻭَﺍﻟْﺄَﻏْﻠَﺎﻝَ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﻛَﺎﻧَﺖْ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ { ( ﺍﻷﻋﺮﺍﻑ : 157 )
‹‹ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል፡፡ ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡፡›› (አል አዕራፍ 157)
} ﺇِﻧَّﺎ ﻧَﺤْﻦُ ﻧَﺰَّﻟْﻨَﺎ ﺍﻟﺬِّﻛْﺮَ ﻭَﺇِﻧَّﺎ ﻟَﻪُ ﻟَﺤَﺎﻓِﻈُﻮﻥَ { ( ﺍﻟﺤﺠﺮ : 9 )
‹‹እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡›› (ሂጅር 9)
} ﻟَﺎ ﻳَﺄْﺗِﻴﻪِ ﺍﻟْﺒَﺎﻃِﻞُ ﻣِﻦْ ﺑَﻴْﻦِ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻭَﻟَﺎ ﻣِﻦْ ﺧَﻠْﻔِﻪِ ﺗَﻨْﺰِﻳﻞٌ ﻣِﻦْ ﺣَﻜِﻴﻢٍ ﺣَﻤِﻴﺪٍ { ( ﻓﺼﻠﺖ : 42 )
‹‹ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ው፡፡››
(ፉሲለት 42)
} ﺇِﻥَّ ﻋَﻠَﻴْﻨَﺎ ﺟَﻤْﻌَﻪُ ﻭَﻗُﺮْﺁﻧَﻪُ }{ ﻓَﺈِﺫَﺍ ﻗَﺮَﺃْﻧَﺎﻩُ ﻓَﺎﺗَّﺒِﻊْ ﻗُﺮْﺁﻧَﻪُ }{ ﺛُﻢَّ ﺇِﻥَّ ﻋَﻠَﻴْﻨَﺎ ﺑَﻴَﺎﻧَﻪُ { ( ﺍﻟﻘﻴﺎﻣﺔ : 19-17 )
‹‹(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ ›› (አል ቂያማህ 17-19)
በመጨረሻው አንቀፅ ትርጉም ዙሪያ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ፦
“ቁርአን ከተነበበና ከተሸመደደ በኃላ እናብራራልሃለን ትርጉሙንም በምንፈልገው መልኩ እናሳውቅሃለን፡፡”
አላህ ከነቢዩ ﷺ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቁርአንን በመሸምደድ፣ በመጠበቅ፣ ትርጉሙን በመረዳትና በቁርአን በመስራት ኃላፊነትን በሚገባ የሚወጡ ምሁራንን አመቻችቷል፡፡ እነዚህ ዑለማዎች ቁርአንን ለመንከባከብ የሚያስችሉ መድረኮችን ሁሉ በመጠቀም በቁርአን የተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ መፅሐፎችን ደርሰዋል፡፡ አንዳንዱ በትርጉሙ ዙሪያ ሌላው በንባቡ ዙሪያ፣ ስለ ሙህከምና ሙተሻቢህ፣ መካና መዲና ስለወረዱ ምዕራፎች፣ ስለህግጋቶቹ፣ ስለ ሰራዥና ተሰራዡ፣ አንቀፆቹ ስለወረዱባቸው ምክንያቶች፣ ስለቁርአን ምሳሌዎች፣ ስለቁርአን ተአምራት፣ ስለቃላት ትርጉሞች፣ ስለ ሰዋሰውና ሌሎችም የቁርአን ትምህርቶች በተለያየ መልኩ በመፃፍ አላህ በነዚህ ዑለማዎች ምክንያት ቁርአን የተጠበቀ ሆኖ እንዲቆይ አድርጓል፡፡
•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•
https://t.me/tenbihat
© ተንቢሀት

