Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በቁርአን ማመን እና መለያዎቹ! 1

በቁርአን ማመን እና መለያዎቹ!
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄

ቁርአን የአላህ ንግግር ሲሆን ቃሉም ትርጉሙም ከአላህ የመነጨና ጂብሪል ከአላህ በመስማት ወደ ነቢዩ ﷺ ያስተላለፈው ከብረዛና ከመዛባት የተጠበቀ መፅሐፍ ነው::

📚የቁርአን መለያዎች

በአላህ መፃህፍት ማመን ከኢማን ማፅዘናት አንዱ ነው፡፡ ይሁንና ቁርአን ሌሎችን መፃህፍት የሚሰርዝ የሁሉም የበላይ ፈራጅና ነቢዩ ﷺ ከተላኩ በኃላ የሁሉም ሰውና ጋኔን መመሪያ በመሆኑ ከአላህ ዘንድ በወረዱና ከመበረዛቸው በፊት ባሉበት ሁኔታ በሁሉም መፃህፍት ማመን እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ቁርአንን ከሌሎች የምንለይባቸው እምነቶች አሉ ከነዚህ መለያዎቹ መካከል ፦

📌 የቁርአን ጥሪና ህግጋቶቹ ሁሉንም ሰውና ጋኔን የሚያካትትና ማንም ቢሆን ቁርአንን መመሪያ ሳያደርግ አላህን በሌላ ህግጋት ማምለክ እንደማይፈቀድለት ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

} ﺗَﺒَﺎﺭَﻙَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻧَﺰَّﻝَ ﺍﻟْﻔُﺮْﻗَﺎﻥَ ﻋَﻠَﻰ ﻋَﺒْﺪِﻩِ ﻟِﻴَﻜُﻮﻥَ ﻟِﻠْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦَ ﻧَﺬِﻳﺮًﺍ { ‏( ﺍﻟﻔﺮﻗﺎﻥ : 1 ‏)

‹‹ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡›› (ፉርቃን 1)

በሌላም የቁርኣን አያት ለነብያችን ﷺ እንዲህ እንዲሉ አዟቸዋል፡-

} ﻭَﺃُﻭﺣِﻲَ ﺇِﻟَﻲَّ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥُ ﻟِﺄُﻧْﺬِﺭَﻛُﻢْ ﺑِﻪِ ﻭَﻣَﻦْ ﺑَﻠَﻎَ { ‏( ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ : 19 ‏)

‹‹ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስጠነቅቅበት ወደኔ ተወረደ (በላቸው)››
(አል አንዓም 19)

ስለጋኔኖችም ሲናገር እንዲህ ይላል
} ﺇِﻧَّﺎ ﺳَﻤِﻌْﻨَﺎ ﻗُﺮْﺁﻧًﺎ ﻋَﺠَﺒًﺎ }{ ﻳَﻬْﺪِﻱ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﺮُّﺷْﺪِ ﻓَﺂﻣَﻨَّﺎ ﺑِﻪِ { ‏( ﺍﻟﺠﻦ : 1 ، 2 ‏)

‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም፤ ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ ›› (አል ጂን 1-2)

📌 ከፊቱ የነበሩትን መፃህፍት የሰረዘ መሆኑን ማመን፡፡ የመፅሐፍ ባለቤቶችም ሆኑ ሌሎች ቁርአን ከወረደ በኃላ በሌላ መመሪያ አላህን ማምለክ እንደማይችሉ፣ ቁርአን ሐላል ያደረገው እንጂ ሐላል እንደሌለ ቁርአን ሐራም ካደረገው ውጭ ሐራም እንደሌለ ማመን፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፦
} ﻭَﻣَﻦْ ﻳَﺒْﺘَﻎِ ﻏَﻴْﺮَ ﺍﻟْﺈِﺳْﻠَﺎﻡِ ﺩِﻳﻨًﺎ ﻓَﻠَﻦْ ﻳُﻘْﺒَﻞَ ﻣِﻨْﻪُ { ‏( ﺁﻝ ﻋﻤﺮﺍﻥ : 85 ‏)

‹‹ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም›› (አል ዒምራን 85)

} ﺇِﻧَّﺎ ﺃَﻧْﺰَﻟْﻨَﺎ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻟِﺘَﺤْﻜُﻢَ ﺑَﻴْﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺑِﻤَﺎ ﺃَﺭَﺍﻙَ ﺍﻟﻠَّﻪُ { ‏( ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : 105 ‏)

‹‹እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ኒሳእ 1ዐ5

ቀደም ብሎ በተጠቀሰውም የአህሉል ኪታቦችን መፅሐፍ ማንበብ በሚከለክለው የጃቢር ሀዲሰ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

‏( . . . ‏« ﻭﺍﻟﺬﻱ ﻧﻔﺴﻲ ﺑﻴﺪﻩ ﻟﻮ ﺃﻥ ﻣﻮﺳﻰ ﻛﺎﻥ ﺣﻴًّﺎ ﻣﺎ ﻭﺳﻌﻪ ﺇﻻ ﺃﻥ ﻳﺘﺒﻌﻨﻲ ‏» ﻭﺍﻩ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﺴﻨﺪ : 3 / 387 ، ﻭﻏﻴﺮﻩ )

“ነፍሴ በእጁ ባለው ጌታ እምላለሁ ሙሳ እንኳን ህያው ቢሆን እኔን ከመከተል ውጭ አማራጭ የለውም፡፡” (ሙስነድ አህመድ 3/387 )

🔜 በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•
📲 ለሌሎች በማስተላለፍ በዳእዋ እንሳተፍ⚡️
https://t.me/tenbihat

© ተንቢሀት