Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) ለአንድ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል ...


🖐 ኢብኑ ዑሰይሚን ...
.
🎙 ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) ለአንድ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል ...
.
"የሰው ልጅ በአንድ አይነት ፍጥነት ላይ ሊዘልቅ አይቻለውም። ሶሐቦች እንኳን እንዲህ ብለዋል ...
.
"የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሆይ! እኛ እርስዎ ዘንድ ስንመከርና ስናምን እንቆያለን ወደየ ቤተሰቦቻችን፤ ሚስትና ልጆቻችን ስንሄድ ግን እንረሳለን!" አሉ ...
.
🕐 እሳቸውም እንዲህ አሉዋቸው፦ "ለሁሉም ግዜ ግዜ አለው"
.
የሰው ልጅ በአንድ አይነት ፍጥነት ላይ ሊዘልቅ አይችልም! ነገር ግን ሰው ...
👉 ልቡን በማስተካከል ላይ መጠበቅ አለበት!
👍 ልቡ ከተስተካከለ ሁለመናው ይስተካከላልና!
.
(ይህ ከሆነ) የማይመለከተውን ከማተራመስ ይቆጠባል፤ የማይጠቅመውን ሙግት ይተዋል!
ኡማውን የበታተበውን ቡድንተኝነት ይተውና ወደ አላህ ፊቱን ያዞራል!
.
‼ለዛም ነው አንድ መሐይም ከእነዚያ ...
👊 መያዝና ረድ ማድረግ
👅 አሉባልታ
'ፉላን ምን ትላለህ?'
📙 'በእገሌ ኪታብ ላይ ምን ትላለህ?'
📃 'እገሌ በፃፈው ላይስ ምን ትላለህ?'
📶 ከሚሉት ብዙዎቹ ጧሊበል ዒልሞች(ደረሶች) የተሻለ እምነትና ኢኽላስ ኖሮት ታየዋለህ!
.
💭 ይህ ነው እንግዲህ አንድ ባሪያን የሚያጨናንቀው፣
ልቡንም ከአላህ የሚሰልበው!
.
እንዲህ ሲሆን ሰውየውን አሉባልታ ካልሆነ የሚያሳስበው አይኖርም!
.
👉 ለየትኛውም ሰው የምለግሰው ምክር ሰዎችን ከነልዩነታቸው ትቶ ፊቱን ወደ አላህ እንዲያዞር ነው፤ ይህ ነው የተሻለው ነገር"
.
📚 ሊቃእ ባብ አል-መፍቱሕ 232


Abu Ibrahim Mohammed Ibrahim