Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ንግስናና ስልጣን የአላህ ወይስ የወልዮች?

ንግስናና ስልጣን የአላህ ወይስ የወልዮች?
ሱፍዮች የአላህ ወዳጅ (ወሊዮች) ናቸው ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች በእጅጉ ያጋንናሉ። ድንበርም ያልፋሉ!!
ይህ ድንበር ማለፋቸውም በብዙ መልኩ ይገለፃል፤
ከአላህ ውጭ ወልዮችን መመኪያ ማድረጋቸው፣ የነገሮች ሁሉ ሰጪና ነሽነት ሹመት በመለገስ እጃቸውን ወደ ወሊዮች መዘርጋታቸው፣ በችግር ጊዜ ድረሱልን ማለታቸው ለዚህም የምስጋና እና የመቃረብ ስለት ማስገባታቸው። ለወልዮች ድንበር ያለፈ ሙገሳና ውዳሴ ማድረጋቸው። ለትንሹም ለትልቁም ሸህ የአላህን ክብርና ስልጣን ሸራርፈው በስጠት ክርስቲያኖችን መፎካከራቸው፣ በሽርክ የተሞሉ የግጥም ስንኞች መድብሎችን ማዘጋጀታቸውና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።
ለዚህ ሁሉ ጥመት መሰረት የሆነው ፍጥረተ አለሙን የማስተዳደር፣ የፈለጉትን የመፈፀም ስልጣን ተሰጥቷቸዋል በማለት ወሊዮችን የጌትነት ባለድርሻ ማድረጋቸው ነው።
በዚህ አጭር ቪድዮ እንደምትመለከቱት የአንሷረሱና ተማሪው የተውሂድ ወታደር ከሱፍዩ "ሁሉን ቻይ ወሊይ" ተብዬ ሸህ ጋር ባደረገው ድንቅ ውይይት ይህንን ወሳኝ አጀንዳ በመዳሰስ የተውሂድን ብርሀን በቁርአን እና በሎጂክ አጭርና ግልፅ በሆነ መልኩ አብራርቷል።
ንግግሩ ይህንን ይመስላል፤
የሱፍያ ሸይኾች ፍጥረተ አለሙን ያስተናብራሉ ትለኛለህን?
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
የነብያቶች፣ የመልእክተኞች የአላህ ወዳጅ ወሊዮች፣ የፍጥረታት ሁሉ የበላይ ከመሆናቸው ጋር አላህ ግን ከንግስናውና ከስልጣኑ ምንም እንደሌላቸው ገልጿል።
لَيْسَ لَكَ مِنَ الْأَمْرِ شَيْءٌ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ أَوْ يُعَذِّبَهُمْ فَإِنَّهُمْ ظَالِمُونَ
(አላህ) በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ላንተ ከነገሩ ምንም የለህም፡፡»
አል ዒምራን 128
በሌላ አንቀፅም፤
لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ الذُّكُورَ
«የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡» ሹራ 49
አዎን ስልጣኑ የአላህ ብቻ ነው። ማንም ሰው ስልጣን የለውም!!
አላህ እንዲህ ብሏል፤
وَمَا لَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ مِنْ وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
«ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከወዳጅም (መልካምን የሚለግስ ‘ወሊይ’)
ከረዳትም (ቅጣትን የሚያርቅ) ምንም የላችሁም፡፡» ሹራ 31
አላህ ነብዩን «ከነገሩ ምንም የለህም» ካላቸው አንድ የሱፍዮች ሸህ ፍጥረተአለሙን ሁሉ እንደፈለገ ያስተናብራል ይባላል?
ያጀማዓ ይህ ከቁርአን ነው!
እስቲ አይምሯችሁን አሰሩት፦
ለምሳሌ ይህ ሸህ እዚህ እንድናወራ ፍላጎት አልነበረውም። እዛ ጋር ታጅቦ ነበር ነገር ግን መንጥረን አወጣንና አመጣነው። ይኸው በመካከላችን ተቀምጧል። ልክ ነኝ ወይስ አይደለሁም? ይህ ትልቅ መረጃ ነው!
አይፈልገንም አይደል!! እስቲ የፈለከውን የማድረግ ስልጣን ካለህ አባረን!! ይኸው ተደላድዬ ተቀምጫለው.. ትችላለህ?? አትችልም!!
ሸህ ቡረዒም ሊነቀንቀኝ አይችልም። ከባሺ፣ ሳቡላኒ፣ ሙካሽፊ አንተም ጭምር ማንም በኔ ላይ ስልጣን የለውም። በፍፁም!!! እዚሁ እንቀመጣለን!!
ይኸው ነው አትገቱኝም፤ ቂያማ እስኪቆም ያንተና የመል ሱፍዮች ተቃራኒ ነኝ ሆኜ ወደፊት እቀጥላለሁ።
ተውሂድ ተውሂድ ተውሂድ!!!
አጂብ ነው የተውሂድ ተጣሪዎች እንዲህ ያስደስታሉ።
ሀቅ ሲነገር ሀሰት ቦታ አይኖረውም። ይንኮታከታል!!!
‘ነባሩ እስልምና’ የሚል ሽፋን በማልበስ በሀገራችን ይስፋፋ ዘንድ በተቀናጀ መልኩ ደፋ ቀና የሚባልለት የሱፍያ አካሄድ እንዲህ በሽርክ የታጀበ ነው!!! አዑዙ ቢላህ!!
አላህን ትተን ወልዪችን እና ቀብሮቻቸውን እንድናመልክ፣ ተውሂድን በሽርክ እንድንቀይር ይከጀላልና ነቅተን እናንቃ!!
የአላህ ወዳጅ ወሊይ መሆን የፈለገ ተውሂዱን ያጠንክር፣ አላህን ይፍራ ድንበሮቹን ያክብር።
أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ
(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡
لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۚ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
አቡ ጁነይድ 18/01/2009