===> ቁም !!! ተመልከት ምንጨ ገቢህን
ከቆሻሻው ወለድ ማፅዳትህን።‼!
=======> …… ሰርፍ (الصرف) ……=======>
~> በዘመናችን አንገብጋቢ ሆነው ሳለ በቂ ትኩረትን ከተነፈጉ ጉዳዮች መሃከል የግብይት ልውውጥ ሂደት የሆነው ሰርፍ አንዱ ነው። በዚህ ረገድ ከሚከሰት የዕውቀት እጥረት የተነሳ አንድም ሰወች በወለድ መስመር ያልፋሉ ፤ ሁለትም ውድቅ በሆነ የግብይት ወይም ልውውጥ ሂደት ውስጥ ይዘፈቃሉ። እናም ይህ መልዕክት ችግሩን ከመቅረፍ አንፃር የራሱ ሚና እንዲኖረው ይከጀላል።
~> ሰርፍ ምን ማለት ነው?
• ሰርፍ ማለት:- ዓይነታቸው የተዛመዱ አልያም የተለያዩእንደ ወርቅ ፣ብር … ወዘተ ወይንም እነሱን የሚተካ ነገር መሻሻጥ ፣ መለዋወጥ ፣ መገበያየት ሰርፍ ይባላል። ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ፦ ወርቅን በወርቅ ወይም በብር ፣ አልያም ብርን በብር ወይም በወርቅ እንዲሁም በነሱ ምትክ ያሉ የገንዘብ ኖቶች ለምሳሌ የሳዕዲ ሪያል በአሜሪካ ዶላር ወዘተ… መለወጥ ፣ መግዛት ማለት ነው።
~> ለመሆኑ ለዚህ የሰርፍ ልውውጥ የተለየ መስፈርት አለውን?
• አዎን ሂደቱ ጤናማና ትክክለኛ ይሆን ዘንድ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት።
~> 1• ልውውጡ (ግብይቱ) ዓይነታቸው ተመሳሳይ በሆኑ ነገራት ከሆነ ለምሳሌ ወርቅ በወርቅ ፣ ሪያል በሪያል… ከሆነ ሁለት መስፈርቶች ይኖራሉ፦
1ኛው• መጠናው ( ብዛታቸው) ተመሳሳይና እኩል መሆን ሲሆን
2ኛው• በውላቸው ( በስምምነታቸው) ወቅት እዚያው እጅ በእጅ መቀባበል
~> 2• ልውውጡ ዓይነታቸው የተለያየ በሆኑ ነገራት ለምሳሌ ወርቅ በብር አልያም የሳዑዲ ሪያል በአሜሪካ ዶላር ከሆነ ደግሞ፦
1ኛው• መጠንና በዛቱ መበላለጡ ችግር ካለመኖሩ ጋር ፤ እዛው በውሉ ወቅት ግን እጅ በእጅ መቀባበል አለባቸው።
√ በዚህም መሰረት ሰርፍ ሸርጦቹ ከተሟሉ የተፈቀደ የግብይት ዓይነት መሆኑን እንረዳለን። አላህም እንዲህ ይላል፦
"وأحل الله بيع"
"አላህም ግብይትን ፈቀደላችሁ"
~> ምሳሌና መረጃን አስደግፈን በመቀጠል ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እንሞክራለን።
(1) ዘራቸውም ሆነ ዓይነታቸው አንድ ዓይነት ከሆኑ፦ ማለትም ወርቅ በወርቅ ፣ ብር በብር ፣ እንዲሁም በሃዲስ የተዘረዘሩት ገብስ በገብስ ፣ ስንዴ በስንዴ ፣ ተምር በተምር ፣ ጨው ፣ በጨው ከሆነ ሁለቱም የሪባ ዓይነቶች ተጋርጠውበታል። ሪበል ፈድል (ጭማሪ ወለድ) እና ሪበ ነሲኣ (የግዜ ወለድ) ፤ እናም ግብይቱ ከነዚህ ይፀዳ ዘንድ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው ፤ እኩል በእኩል እና እጅ በእጅ መሆን። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
"الذهب بالذهب والفضة بالفضة والبر بالبر والشعير بالشعير والتمر بالتمر والملح بالملح مثلا بمثل سواء بسواء يدا بيد فاءذا اختلف هذه الأصناف فبيعوا كيف شئتهم إذا كان يدا باليد"
"ወርቅ በወርቅ ፣ ብር በብር ፣ ስንዴ በስንዴ ፣ ገብስ በገብስ ፣ ተምር በተምር ፣ ጨው ፣ በጨው እኩል በእኩልና እጅ በእጅ በማድረግ ተገበያዩ ፤ እነዚህ ነገሮች ከተለያዩ ግን እጅ በእጅ ከመሆኑ ጋር እንዳሻችሁ ተገበያዩ"
• በመሆኑም 1 ግራም የተሻለ ደረጃ ያለውን ወርቅ በ2 ግራም የወረደ ወርቅ መገበያየት አይቻልም። ባይሆን ፍላጎቱ ካለ 2 ግራም ደካማውን ወርቅ በመሸጥ በገንዘቡ 1 ግራሙን የተሻለ ወርቅ መግዛት ይቻላል። ይበልጥ ግልፅ እንዲሆን የኛ አገር መገበያያ የሆነውን የገንዘብ ኖት ብናይ 1 አዲስ ብር በ2 አሮጌ ብር መለወጥ አይፈቀድም። ሌሎችንም በዚህ መሰረት ማስኬድ ያስፈልጋል።
(2) ዘራቸው አንድ ሆኖ በዓይነት ከተለያዩ፦
ለምሳሌ ብር በወርቅ ፣ ገብስ በስንዴ ፣ ወዘተ… ሪበል ፈድል ባይኖርበትም ረበ ነሲኣ ስላለበት እጅ በእጅ መረካከብ ያስፈልጋል። ስለሆነም 1 ግራም ወርቅ በ30 ግራም ብር ወይም 5 ኪሎ ገብስ በ15 ኪሎ ስንዴ መገበያየት ይቻላል ግን እጅ በእጅ መሆን አለበት። ተቃቡድ (እጅ በእጅ) መለዋወጡ ኢጅማዕ እንዳለበት ኡብኑል ሙንዚር (ዐለይሂ ረህመቱላህ) ገልፀዋል፦
"وأجمعوا ان المتصارفين إذا تفرقا قبل ان يتقابضا ان الصرف فاسد"
" ሁለቱ ተገበያዮች ( ተለዋዋጮች) እጅ በእጅ ሳይረካከቡ ከተለያዩ ልውውጡ(ግብይቱ) ፋሲድ ነው"
እናም ይህን መቃረን በሃራምነቱ ኢጅማዕ ወዳለበት ሪበ ነሲኣ (የግዜ ወለድ) ይወስዳል።
(3) በዘርም ሆነ በዓይነት የተለያዩ ከሆኑ፦ ለምሳሌ ብር በገብስ ወይም ወርቅ በስንዴ ወዘተ ከሆነ ሁለቱም የሪባ ዓይነት የለበትም። ስለሆነም ገበያ አምርተው 20 ኪሎ ስንዴ ቢያሰፍሩና ክፍያውን በቀጠሮ ቢያደርጉትና ቢስማሙ ከልካይ የለብዎትም።
ማስታወሻ፦ በት/ቱ ላይ በብዛት ወርቅና ብር እንደ ምሳሌ ቢነሱም ቅሉ በዚህ ዘመን እነሱን ተክተው ለግብይት ሚያገለግሉ የተለያዩ የገንዘብ ኖቶችም ይካተታሉ።
~> *_ቁም_* !!! ተመልከት ምንጨ ገቢህን
ከቆሻሻው ወለድ ማፅዳትህን ።
ብዙዎቻችን ገንዘብ ለመመንዘር ስንሻ የማናስተውለው ስህተት ፤ ይኸውም እንበልና መቶ ብር ለመፈንከት የጎረቤት ሱቅ አቀናን እንበል ባለ ሱቁም ለግዜው 70 ብር ብቻ እንዳለውና ቀሪውን ሌላ ግዜ ውሰዱ ቢለን ሳናቅማማ እንስማማለን። ይህ ደግሞ አስቀድመን ከተማርነው የሰርፍ ህግ ጋር ይጣረዛል። መዘግየት ስላለበት የግዜ ወለድ ውስጥ ይገባልና!
س: رجل معه خمسمائة ريال، يريد أن يصرفها، ولم يجد عند صاحب البقالة سوى ثلاثمائة ريال، وسيأخذ الباقي فيما بعد، وقد اعترض شخص آخر، وقال: هذا نوع من الربا. نرجو الإفادة، وفقكم الله وسدد خطاكم. والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته .
ج : لا يجوز للمتصارفين أن يتفرقا إلا بعد استلام كل منهما كامل مبلغ الصرافة، وعلى ذلك فلا يجوز لمن دفع لشخص خمسمائة ريال لصرفها أن يأخذ ثلاثمائة في الحال، والباقي بعد الافتراق بزمن ولو قصر.
وبالله التوفيق وصلى الله على نبينا محمد وآله وصحبه وسلم.
اللجنة الدائمة للبحوث العلمية والإفتاء
عضو ... عضو ... عضو ... عضو ... نائب الرئيس ... الرئيس
بكر أبو زيد ... عبد العزيز آل الشيخ ... صالح الفوزان ... عبد الله بن غديان ... عبد الرزاق عفيفي ... عبد العزيز بن عبد الله بن باز
ወደ ፈትዋው ስንመለስ የጥያቄው ጭብጥ፦ አንድ ሰው ወደ በቃላ (ሱቅ) በመሄድ 500 ሪያል እንዲመነዝርለት ሲጠይቀው ለግዜው 300 ሪያል ብቻ እንዳለውና ቀሪው በቀጣይ ለመውሰድ ቢስማማ ሌላ ሰው ድንገት እግር ጥሎት መጣና ይህ የሪባ ዓይነት ውስጥ ሚካተት ግብይት መሆኑን ነገረው ፤ በዚህ ላይ ማብራሪያ ቢሰጡን ••••?
ምላሽ፦ ሁለቱ ተለዋዋጮች ሙሉ ገንዘባቸውን ሳይቀባበሉ በፍፁም መለያየት አይፈቀድላቸውም። በዚህም መሰረት ዝርዝር ፈላጊው 300 ሪያል ተቀብሎ ቀሪውን ከተለያዩ ጥቂት ቆይታ በኋላም ቢሆን እንኳን ማዘግየቱ አይበቃለትም።
የታላላቅ ዑለሞች የምርምር የዕውቀትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ።
√? ገንዘብህን ስትልክ እንዴት ነው?
~> ሰወች ወደ ዘመድ ወዳጆቻቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሆነ ገንዘብ ጣል ማድረጋቸው አይቀርምና በሚከተለው መልኩ ከሆነ አሁኑኑ ያስቡበት ፣ ላለፈው ከጌታዎ ምህረትን በመከጀል ለቀጣዩ እርምትያድርጉ።
وقد سئل الشيخ ابن عثيمين رحمه الله :
بالنسبة للحوالة ، إذا أعطى رجلٌ رجلاً مبلغاً لكي يستلمه الرجل الآخر في بلدة أخرى بعملة تلك البلدة ، ويُشكل عليه اختلاف هذه العملة بالريالات ، فهل هذا يدخل في ربا الفضل ، أم أنه لا بأس به ؟ .
فأجاب :
"هذا يدخل في ربا النسيئة ؛ لأنه مع اختلاف العملة لا يوجد ربا فضل ؛ لكن يدخل فيه ربا النسيئة
والمصارفة بدون قبض لا تجوز" انتهى .
" لقاءات الباب المفتوح " ( لقاء رقم 44 / سؤال رقم 6 ) .
ዕውቁ የተከበሩ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ተጠየቁ፦ ሃዋላን አስመልክቶ አንድ ሰው በአገሩ ላለ ሰው በዛ አገር የገንዘብ ኖት እንዲሰጠው እዚህ ለሚገኝ ሌላ ሰው በዚህ አገር የገንዘብ ኖት ቢሰጠው ይህ ድርጊት ሪበል ፈድል ውስጥ ይካተታልን? አልያስ ምንም ችግር የለውም?
ምላሽ፦ የተለያዩ የገንዘብ ኖቶች በመሆናቸው ሪበል ፈድል ሳይሆን ሪበ ነሲኣ ውስጥ ይገባል። እጅ በእጅ ሳይለዋወጡ የሚከናወን ልውውጥ አይፈቀድም።
~> ወዳጄ ሆይ ተመመሳይ ይዘት ያላቸው ፈትዋዎች ብዙ ቢሆኑም ግዜህን በሌላም ጠቃሚ ነገር ማሳለፍ ስላለብህ በዚሁ ስገደብ በቀጣይ የአላህ ፈቃድ ከሆነ ስለ ሰርፍ እና ሃዋላ ቁርኝትና ልዩነት እንዲሁም ከባንክ ጋር ስለሚደረገውም ሙዓመላ እንመለከታለን።
_ኢንሻ አላህ በዚህ አላበቃም ይቀጥላል።_
አል ዒልሙ ኑሩን Al ilmu Nurun
https://www.facebook.com/alilmuunurun/